Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    እጅግ የተቀደሱት የቤተሰብ ሰዓታት፡፡

    የሰንበት ትምህርትና የጸሎት ስብሰባው የሰንበቱን ክፍል ብቻ የሚጠቀልሉ ናቸው፡፡ ለቤተሰብ የተቀረው ድርሻ ከሰንበት ሰዓታት ሁሉ እጅግ የተቀደሰና የተከበረ ጊዜ ነው፤ አብዛኛውን ከዚህ ጊዜ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ሊውሉበት ይገባል፡፡ በብዙዎቹ ቤተሰቦች ዘንድ እንደ ተቻላቸው መጠን ወጣቶቹ ልጆች ጨዋታ እንዲጫወቱ በራሳቸው ይተውዋቸዋል፡፡ ብቻቸውን ሲተውዋቸው ልጆች ወዲያው ዕረፍተ ቢሶች ይሆኑና መጫወት ወይም አንዳች ዓይነት ክፋት ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ በእንዲህ ሰንበት ለነሱ ሁኖ ከቁም ነገር አይቆጠርም፡፡CCh 46.6

    በሚያስደስት ቀን ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር በመስኮትና በደኖች ውስጥ ይንሸራሸሩ፡፡ ከሚያምሩት የተፈጥሮ ነገሮች መኻከል ሰንበት የተደነገገበትን ምክንያት ንገሩዋቸው፡፡ ስለ ታላቁ የእግዚአብሐር የፍጥረት ሥራው አስታውቋቸው፡፡ ምድሩ ከእጁ ብቅ ባለ ጊዜ የተቀደሰና ውብ እንደ ነበረ ንገሩዋቸው፡፡ አበባ ሁሉ ቁጥቋጦ ሁሉ ዛፍ ሁሉ ለፈጣሪያቸው ሐሳብ መልስ ሰጥተዋል፡፡ ዓይን ያረፈበት ነገር ሁሉ ውብ፤ አእምሮም በእግዚአብሔር ፍቅር ሐሳብ የመላ ነበር፡፡ ድምፅ ሁሉ ከአምላክ ድምፅ ጋር ስሙሙ የሆነ አስደሳች ሙዚቃ እንደ ነበረ ንገሩዋቸው፡፡ የእግዚአብሔርን ፍጹሙን ሥራ ያበላሸ ኃጢአት እንደሆነ ፤ እሾሆችና አሜኬላዎች ሐዘንና ሕመም ሞትም ሁላቸውም ለአምላክ ባለመታዘዝ ውጤቱ መሆኑን አሳዩዋቸው፡፡ ምድሩ በኃጢአት እርግማን ቢበላሽም አሁንም የእግዚአብሔርን ቸርነት የሚገልጽ መሆኑን እንዲያዩ አድርጉዋቸው፡፡ ለምለሞዡ መስኮች ፤ ረዣዥሞቹ ዛፎች አስደሳቹ የጸሐይ ብርሃን ፤ ደመናዎች ፤ ጤዛው ፤ የሌሊት ጸጥታነት ፤ ኮከቦች የመሉባቸው የሰማያት ክብር ጨረቃም በውበቱ ሁሉም ስለ ፈጣሪ ይመሰክራሉ፡፡ ስለ እግዚአብሔር ትዕግሥትና ፍቅር የሚመሰክር በመሆኑ ነው እንጂ በማያመሰግን አለማችን ላይ አንድም የዝናብ ነጠብጣብ ባልወደቀም ፤ አንድም የብርሃን ጮራ ባለበራበትም ነበር፡፡CCh 46.7

    «እግዚአብሔር እንዴሁ ዓለምን ወድዋልና አንድ ልጁን እስኪለውጥ ድረስ በርሱ ያመነ ሁሉ እንዳይጠፋ የዘላለም ሕይወት ትሆንለት ዘንድ እንጂ” ፤ እያላችሁ ስለ ደህንነት መንገድ ንገሩቸዋው፡፡ ዮሐንስ 3 16፡፡ ጣፋጩን የቤተልሔም ታሪክ ደጋግሙላቸው፡፡ የሱሱ በልጁነቱ ለወላጆቹ ታዛዥ በወጣትነቱ ታማኝና ትጉ፤ ቤተሰብን ለመደገፍ ይረዳ እንደ ነበረ በልጆቹ ፊት አቅርቡላቸው፡፡ እንዲሁም መድኃኒታችን የወጣቶችን ሙከራዎች ብስጭትና ፈተናዎች ተስፋቸውንና ደስታቸውን እንደሚያውቅና ርኅራኄ ሊያደርግላቸውና እርዳታ ሊሰጣቸው እንደሚችለ ንገሩዋቸው፡፡ በየጊዜው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉትን አስደሳች ታሪኮች አብራችሁ አንብቡ፡፡ በሰንበት ትምህርት የተማሩትን ጠይቋቸው ፤ ቀጥሎም ስላለው የሰንበት ትምህርት የተማሩትን ጠይቋቸው ቀጥሎም ስላለው የሰንበት ትምሀርት አብራችሁ አጥኑ፡፡ ፭56 T358—359;CCh 47.1

    በሰንበት ዕለት ቤተሰብ ፈጽሞ ለእግዚአብሔር መቀደስ አለበት፡፡ ትእዛዙ በደጆቻችን ውስጥ ያለውን ሁሉ ይጠቀልላል ፤ የቤት ነዋሪዎች ሁሉ ዓለማዊ ሥራቸውን ወዲያ መጣል አለባቸው ፤ በተቀደሱት ሰዓታት በጸሎት መዋል ነው፡፡ ሁሉም እግዚአብሔርን በተቀደሰው ቀኑ በደስታ አገልግሎት ያከብሩ ዘንድ ይተባበሩ፡፡ ፮62TT185;CCh 47.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents