Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ከዓለማዊ ሥራዎች የዕረፍት ቀን፡፡

    የራሱን ትናንሽ የሆኑ ሥጋዊ ጥቅሞች ያገኝ ዘንድ ሁሉን የሚችል አምላክን ለማሳዘን መድፈር ለሟች ሰው እጅግ ድፍረት ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ለራስ ምቾት መተላለፉ ነውና በየጊዜው ሰንበትን ለግል ሥራ መጠቀም የእግዚአብሔርን ሕግ ጨርሶ እንደ መተላለፍ መጠን ፈጽሞ ችላ እንደ ማለት ነው፡፡ «እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና” ሲል ከሲና ነጐድጓድ ተንጐደጐደ፡፡ የአባቶችን ኃጢአት በሚጠሉት ልጆች ላይ እስከ ሦስት እስከ አራትም ትውልድ ድረስ የሚመራመርና ለሚወዱተና ትእዛዛቱን ለሚጠብቁ ለብዙ ሺህ ምሕረት የሚያደርግ መሆኑን የሚናገረው አምላክ የከፊል የተከፋፈለም ውዴታ አይቀበልም፡፡ ጐረቤትን (ባልንጀራን) መቀማት ትንሽ ነገር አይደለም ፤ እንዲህ ያለውን ሲሠራ ዓመፀኛ ሁኖ የሚገኝ ትልቅ ኃፍረት ይሆንበታል፡፡ ሆኖም ባልንጀራውን ያታልል ዘንድ የሚያፌዝ ያለ ኃፍረት እርሱ የባረከውንና በልዩ ሐሳብ ለብቻ የለየውን ጊዜ ከሰማይ አባቱ ይቀማል፡፡ ፲፭154T249.250;CCh 52.2

    በምንናገረው ቃላትና በሐሳባችን ልንጠነቀቅ አለብን፡፡ በሰንበት ስለ ሥራ ጉዳይ የሚነጋገሩና ፕላን የሚያቅዱ በእግዚአብሔር ዘንድ በእርግጥ ሥራ እንደሰሩ ይቆጠራሉ፡፡ ሰንበትን በቅድስና ስንጠብቅ ሐሳባችን ዓለማዊ ጠባይ በሆኑት ነገሮች ላይ እንዲያርፍ እንኳ መፍቀድ አይገባንም፡፡ ፲፮162T1185; CCh 52.3

    እግዚአብሔር ተናግሮአልና ሰው እንዲታዘዘው ማለቱ ነው፡፡ ይህን እንዲያደርግ ይመቸው እንደሆነ እያለ የሚጠይቅ አይደለም፡፡ የሕይወትና የክብር ጌታ የጻር ሰው በደዌም የተፈተነ ይሆን ዘንድ ከፍ ያለውን የአዛዢነት ፍሬ ሊያድነው ኃፍረትንና ሞትን ተቀበለ፡፡ የሱስ የሞተው ሰውን በኃጢአቱ ለማዳን አይደለም ከኃጢአቱ ለማደን ነው እንጂ፡፡ ስለዚህ ሰው የስህተት ጐዳናውን ትቶ የክርስቶስን ምሳሌ ተከትሎ መስቀሉን ተሸክሞ እመከተል አለበት፤ ራሱንም ክዶ በማንኛውም ሆነ እግዚአብሐርን መከተለ አለበት፡፡CCh 52.4

    ለዓለማዊ ጥቅም ተብሎ በሰንበት ዕለት እንዲሰራ ለማንም ነገሮቹ (ጉዳዮቹ) ሁሉ የሚያመጻድቁለት አይደለም፡፡ እግዚአበሐር ላንዱ ሰው የሚፈቅድለት ከሆነ ለሁሉም ይፈቅድ ነበር፡፡ ምስኪን ሰው ወንድም ኤል እንዲህ በማድረግ ቤተሰቡን ይበልጥ ለመደገፍ የሚችል ሲሆን ለኑሮው ገንዘብን ያተርፍ ዘንድ በሰንበት ዕለት የማይሰራው ለምን ይሆን? ሌሎችስ ወንድሞች ወይም ሁላችን እንዲሁ ለማድረግ ምቹ ጊዜ ሲኖረን ብዠ ሰንበትን የማንጠብቀው ስለ ምንድነው? ከሲና የመጣ ድምፅ «ስድስት ቀን ስራ ተግባርኸንም ሁሉን አድርግ ሰባተኛው ቀን የእግዚአብሔር ያምላክኸ ሰንበት ነው»፡፡ ሲል መልሱን ይሰጠናል፡፡ ዘፀዓት ፳፡፱፡፲ ፡፡CCh 52.5

    ዕድሜህ መለኮታዊ ትእዛዛትን እንዳትታዘዝ የሚፈቅድልህ (የሚያመኻኝልህ) አይደለም፡፡ አብርሃም በስተ እርጅናው በኃይል ተፈተነ፡፡ ለተንከራተተው ሽማግሌ ሰው የእግዚአብሔር ቃላት አስፈሪና ምንም መልስ የማይገኝለት መስሎት ነበር፤ ሆኖም እርሱ ለትክክለኛ ፍርዳቸው ምንም አልጠየቀም፤ ወይም በመታዘዙ ላይ አላመነታም፡፡ ሽማግሌና ደካማ እንደሆነና የሕይወቱ ደስታ የነበረው ልጁን ሊሠዋ የማይችል መሆኑን ሊከራከር በቻለ ነበር፡፡ ስለዚሁ ልጅ ከተሰጡት ተስፋዎች ጋር ይህ ትእዛዝ የሚቃወስ መሆኑን ለጌታ ባሳሰበው ነበር፡፡ ግን የአብርሃም መታዘዝ ያለ ማጉረምረም ወይም ያለ ወቀሳ ነበር፡፡ በእግዚአብሔር ያደረገው እምነት ፍጹም ነበር፡፡ ፲፯፤174T250—253;CCh 53.1

    የየሱስ ሰባኮች (አገልጋዮች) ሰንበትን በቅድስና ለመጠበቅ ለማያስቡት ገሣጺዎች ሆነው መቆም አለባቸው፡፡ በሰንበት ዕለት ዓለማዊ ጭውውት እየተናገሩ በዚያኑ ጊዜም የሰንበት ጠባቂዎች እንደሆኑ የሚናገሩትን በቸርነትና በጥብቅ መገሠጽ አለባቸው፡፡ በተቀደሰው ቀኑ እግዚአብሔርን በጸሎት የሚያመልኩበት ቀን መሆኑን ማደፋፈር አለባቸው፡፡ በሰንበት ዕለት አብዛኛውን ጊዜ ሰንበት ጠባቂዎች በእንቅልፍ ማሳለፋቸውን እግዚአብሔር አይደሰትበትም፡፡ እንዲህ በማድረጋቸው ፈጣሪያቸውን አያከብሩም፤ በምሳሌያቸውም ስድስቱን ቀናት በዕረፍት ለማሳለፍ ለነሱ እጅግ ክቡር ነው ይላሉ፡፡ የሚያስፈልጋቸውን እንቅልፍ ራሳቸውን መንፈግ ቢሆንባቸውም ቅሉ ገንዘብ ለትረፍ ስላለባቸው ይህንኑ እንቅልፍ በተቀደሰው ቀኑ በመተኛት ይሞላሉ፡፡ ከዚያ በኋላ እንዲህ በማለት ለራሳቸው መመኻኛ ያቀርባሉ፤ «ሰንበት የተሰጠው ለዕረፍት ቀን ነው፤ ዕረፍት ያስፈልገኛልና ወደ ጸሎት ስብሰባ ሔጄ ራሴን ዕረፍት አልነፍግም» እንዲህ ያሉት የተቀደሰውን ቀን በስህተት ይጠቀሙበታል፡፡ በዚያን ቀን በተለይ ቤተሰቦቻቸውን በቤተ ጸሎት ከጥቂቶች ጋር ወይም ከብዙዎች ጋር ቢሆን ይጠብቁት ዘንድ ማነቃቃትና ማሰብሰብ አለባቸው፡፡ በሰንበት ዕለት የሚያርፍባቸው መለኮታዊ ኃይል በሳምንቱ ውስጥ እንዲከተላቸው ጊዜያቸውንና ኃይላቸውን ለመንፈሳዊ ልምምድ ቀድሰው መስጠት አለባቸው፡፡ በሳምነቱ ቀናት ሁሉ እንደ ሰንበት ቀን ያለ ለጸሎት ሐሳብና ስሜት የተወደደ (የሚያስደስት) ቀን የለም፡፡CCh 53.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents