Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ለያንዳንዱ የቤተሰብ አባል የተሰጠው ሥፍራ፡፡

    ወንዶችም ሆነ ሴቶች እውነትን ሊሠራ ከሚችልበትና ሊገለጽ ከሚቻልበት ሥፍራ በመሸጐጥ (በማሳተፍ) ሥራ ሊጠሩ ይችላሉ፡፡ በዚህ ቆርጠው በመሥራት ሥራቸውን ሊወስዱ ይችላሉ ፤ ጌታም በነሱ አማካይነት ይሠራል፡፡ ለተግባራቸው በማሰብ የተቀቡ ከሆኑና በእግዚአብሔር መንፈስ አነቃቂነት ቢሰሩ ፤ ለዚህ ጊዜ የሚያስፈልገው ራስን መግታት ይኖራቸዋል፡፡ መድኃኒታችን ራስን ሠዊዮች ሴቶች ላይ የፊቱን ብርሃን ያንፀባርቅባቸዋል፤ ይህም ከወንዶች የበለጠ ኃይል ይሰጣቸዋል፡፡ እነሱም በቤተሰቦች ውስጥ ወንዶች ሊያደርጉ የማይችሉትን ሥራ ወደ ውስጠኛው ሕይወት የሚደርሰውን ሥራ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ወንዶች ሊደርሱባቸው ወደማይችሉ ልቦች ሊቀርቡ ይችላሉ፡፡ ሥራቸው ተፈላጊ ነው፤ ጥንቁቆችና ትሁታት ሴቶች በቤቶቻቸው ለሰዎች እውነትን በመግለጽ መልካም ሥራ ሊሠሩ ይችላሉ፡፡ በእንዲህ የተገለጸው ያምላክ ቃል የሚያገራ ሥራውን ይሠራል፤ በርሱም አነቃቂነት መላዎቹ ቤተሰቦች ይመለሳሉ፡፡ ፲፫139T128, 129; CCh 58.1

    ሁሉም አንዳች ነገር ሊሠሩ ይችላሉ፡፡ ስለ ራሳቸው ለማመኻኘት ጥረት በማድረግ አንዳንዶች የቤቴ ተግባሮች ፤ ልጆቹ ጊዜየንና ችሎታዬን (ገንዘቤን) የሚፈልጉብኝ ናቸው” ይላሉ፡፡ እናንተ ወላጆች ለጌታ ትሠሩ ዘንድ በኃይላችሁና በችሎታችሁ ፤ ተጨምረው ለልጆቻችሁ ረዳት እጅ ሊሆኑ ይገባል፡፡ ልጆች የጌታ ቤተሰብ ወጣቶች አባሎች ናቸው፡፡ በመፈጠራቸውና ደህንነት በማግኘት የርሱ የሆኑት ራሳቸውን ለአምላክ ቀድሰው ይሰጡ ዘንድ ሊመሩ ይገባል፡፡ የአካል ፤ የሐሳብና የነፍስ ኃይላቸው ሁሉ የርሱ እንደሆነ ሊማሩ ይገባል፡፡ ራስን ባለመውደድ አገልግሎት በልዩ ልዩ መስመሮች ይረዱ ዘንድ ሊሠለጥኑ ይገባል፡፡ ልጆችህ ዕንቅፋቶች እንዲሆኑ አትፍቀድ፡፡ የሥጋዊም ሆነ የመነፈሳዊ ሸክም ካንተ ጋር ልጆቹ መሳተፍ አለባቸው፡፡ ሌሎችን በመርዳት ደስታቸውንና ጠቀሜታቸውን ይጨምራሉ፡፡ ፲፬147T63; CCh 58.2

    ለክርስቶስ የምናደርገው ሥራችን በቤት ላሉት ሊጀመር ይገባል፡፡ የወጣቶች ዕውቀት ባለፈው ሲሰጣቸው ከነበረው በተለየው ሥርዓት ሊሆን ይገባል፡፡ በጎ አድራጎታቸውም ሲሰጣቸው ከነበረው እጅግ ልፋት የሚጠይቅ ነው፡፡ ከዚህ የበለጠ ዋና የሆነ ወንጌላዊ ሥራ የለም በሕግና በምሳሌ ወላጆች ላልተመለሱት እንዲሠሩ ልጆቻቸውን ማስተማር አለባቸው፡፡ ልጆቹ ለሽማግሎችና ለታመሙት እንዲራሩና ለድሆችና ለተቸገሩት ችግራቸውን ያቀሉላቸው ዘንድ መማር አለባቸው፡፡ በወንጌላዊ ሥራ ትጉዎች እንዲሆኑ መማር አለባቸው ፤ በልጅነታቸው ዓመታት ለሌሎች ጥቅምና ለክርስቶስ ጉዳይ ማስፋፊያ ራስን መካድና መሠዋትን መማር አለባቸው፤ ከአምላክ ጋር ባንድነት የሚሠሩ ሰራተኞች ይሆኑ ዘንድ፡፡ ፲፭156T429;CCh 58.3