Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    መሥዋዕት በማቅረብ በሚገለጸው ፍቅር አምላክ ሥጦታዎች ይገምታል፡፡

    በቤተ መቅደሱ ምዛኖች ውስጥ ለክርስቶስ በፍቅር የተሰጡት የድሆቹ ሥጦታዎች በተሰጡት በገንዘቡ ብዛት መሠረት የሚገመቱ አይደለም መሥዋዕቱን በማቅረብ በሚገለጸው ፍቅር መሠረት ነው እንጂ፡፡ ሐብታም ሰው ካለው ብዛት በሚሰጠው መጠን ትንሽ ብቻ ያለው ድሀው ሰው ያንኑ ትንሹን ወዶ (በነጻ) በሚሰጠው በለጋሱ ስጦታ መሠረት የየሱስ ተስፋዎች በው ነቱ የሚረጋገጥለት ነው፡፡ ድሀው ሰው የሚሰማውን ያህል ካለው ከትንሹ መሥዋዕት ያደርጋል፡፡ ሐብታሙ ሰው ካለው ብዛት ሲሰጥና ምንም እጦት የማይሰማው በውነቱ የሚያስፈልገውን ራሱን ምንም ነገር ራሱን በእርግጥ ይነፍጋል ሐብታሞች ከሐብታቸው ነውና የሚሰጡ ስለዚህ በሐብታሙ ሰው ስጦታ ውስጥ የማይገኘው በድሀው ሰው ስጦታ ውስጥ ቅድስና አለበት፡፡ እግዚአብሔር በቸርነቱ ለሰው ጥቅም የተሟላ ደንበኛ የሆነ (የሲስተማቲክ) የልግሥና ኘላን አደራጅቷል፡፡ ቸርነቱ ከቶ የሚቋረጥ አይደለም፡፡ የእግዚአብሔር አገልጋዮች የሚያፈልቅላቸውን ቸርነቱን ቢቀበሉ ሁሉም ትጉዎች ሰራተኞች ይሆኑ ነበር፡፡ ፲፭153T398, 399;CCh 78.4

    የትንንሽ ልጆች ሥጦታዎች እግዚአብሔር የሚቀበላቸውና የሚደሰትባቸው ናቸው፡፡ ሥጦታዎቹ በሚሰጡት መንፈስ መሠረት የሥጦታው ዋጋ ይሆናል፡፡ ድሆች የሐዋረያውን ደንብ በመከተልና በጥቂቱ በየሳምንቱ በማከማቸት ግምጃ ቤቱን ለመሙላት ይረዳሉ እግዚአብሔርም ሥጦታዎቻቸውን ሁሉ የሚቀበላቸው ነው የነሱን ያህል እንዲያውም ከነሱ ይበልጥ ከበለጸጉት ወንድሞቻቸው ይልቅ አብዝተው መሥዋዕት የሚያቀርቡ ናቸውና፡፡ ደንበኛ የሆነ የልግሥና ኘላን በማያስፈልጉ ነገሮች ገንዘብን በማባከን በሚገጥማቸው ፈተናዎች ላይ ለየቤተሰቡ መጠበቂያ መሆኑን ያስረዳል በተለይም ለሐብታሞች በብኩንነት (በቅብጠት) እንዳይቀማጠሉ በመጠበቅ ረገድ በረከት መሆኑን ያስረዳል፡፡ ፲፮163T412;CCh 79.1

    ከልብ የተለገሠ ልግሥና ዋጋው ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የጠበቀ ኀብረት እንዲያገኝ ሐሳብና ልብን የሚመራ ነው፡፡ ፲፯176T390;CCh 79.2

    ጳውሎስ ለእግዚአብሔር ጉዳ ስለ መስጠት ደንብ አውጥቶ ለራሳችንና ለአምላክ ውጤቱ ምን እንደሚሆን ይነግረናል “እያንዳንዱ በልቡ እንደ ተዘጋጀ ያድርግ፡፡ በልብ ችጋርም በግድም እንደሚሆን አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ወዶ የሚሰጠውን ይወዳልና”፡፡ ‹‹በንፍገት የዘራ በንፍገትም ያጭዳልና፡፡ በበረከትም የዘራ በበረከትም ያጭዳል››፡፡ “እግዚአብሔርም ከሃሊ ነው ጸጋን ሁሉ ያበዛላችሁ ዘንድ ሁሉ የተሰጣችሁ እስክትሆኑ ድረስ ትተርፉምላችሁ በመልካም ሥራ ሁሉ (. . . ዘርንም ለሚዘራ የሚሰጥ እንጀራንም ለመብል ይስጣችሁ ዘራችሁንም ያብዛ የጽድቃችሁንም ፍሬ ያሳድገው) በሁሉ ባለጠጎች ትሆኑ ዘንድ በልግሥና ሁሉ ምሥጋና በኛ የምታስነሣ ለእግዚአብሔር”፡፡ ፪ ቆሮንቶስ ፱፡ ፯-፲፩፡፡ ፲፰185T735;CCh 79.3