Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    በሚገባ ንብረትን ማበርከት

    ወላጆች ደሀና አእምሮና መልካም ሐሳብ (ፍርድ) ሳላቸው በጸሎት ሐሳቢነትና እውነትንና የመለኮታዊ ፈቃድን በማወቅ ልምምድ ባላቸው በተገቡ የመካሪዮች እርዳታ ንብረታቸውን ማበርከት አለባቸው፡፡CCh 79.4

    የተቸገሩ ወይም በድኀነት የሚታገሉ ልጆች ቢኖሩዋቸው ገንዘባቸውን በሐሳቢነት (በመጠንቀቅ) የሚጠቀሙ እነሱ ሊታሰቡ ይገባል፡፡ ነገር ግን ብዙ ሐብት ያላቸውና የማያምኑ ልጆች ዓለምን የሚያገለግሉ ያሏቸው እንደሆን ልጆቻቸው ስለሆኑ በእጆቻቸው ውስጥ ገንዘብን በማቀበላቸው መጋቢዎቹ ባደረጋቸው ጌታ ላይ ኃጢአት መሥራታቸው ነው፡፡ ያምላክን ፍላጎት በቀላሉ መመልከት የለባቸውም፡፡CCh 79.5

    ወላጆች ፈቃዳቸው ስለሆነ በሕይወታቸው ላሉ ይህ ለአምላክ ጉዳይ ገንዘብ (እርዳታ) ከመስጠት የሚከለክላቸው መሆኑን ደግሞ በግልጽ ያስተውሉ ዘንድ የሚገባ ነው፡፡ ይህን ማድረግ አለባቸው፡፡ እዚሁ ደስታ ሊኖራቸው ይገባል በሕይወታቸው ሳሉ ከተጨማሪ ገንዘባቸው አበርክተው ከዚህ በኋላ ዋጋ ማግኘት አለባቸው ያምላክን ጉዳይ ለማስፋፋት ፈንታቸውን መሥራት አለባቸው፡፡ በወይን ቦታው ውስጥ ሊደረግ የሚያስፈልገውን ሥራ ያካሒዱ ዘንድ ጌታ ያበደራቸውን ገንዘብ መጠቀም አለባቸው፡፡ ፲፱193X121;CCh 80.1

    ከእግዚአብሔር ግምጃ ቤት አስቀርተኀው ገንዘበቸውን ለልጆቻቸው የሚያከማቹ ለልጆቻቸው መንፈሳዊ ጥቅም የሚያሠጋ ነው፡፡ ወደ ጥፋት እንዲደናቀፉበት ለራሳቸው እንቀፋት የሆነው ንብረታቸውን በልጆቻቸው ጐዳና ላይ ያደርጋሉ፡፡ በዚህ ህይወት ነገሮች ረገድ ብዙዎች ብዙ ስህተት ያደርጋሉ አምላክ ያበደራቸውን ገንዘብ ቀና በመጠቀም የሚያገኙትን ጥቅም ራሳቸውንና ሌሎችን እየነፈጉ ይቆጥባሉ ራስንም ወዳዶችና ስስታሞች ይሆናሉ፡፡ ሐሳባቸውን በመፈንሳዊ ነገር ላይ መጣልን ችላ ይላሉ በኃይማኖታዊም እድገት ቀጫጮች ይሆናሉ ይህ ሁሉ ሊጠቀሙበት የማይቻላቸውን ሐብት ለማከማቸት ነው፡፡ ንብረታቸውን ለልጆቻቸው ይተዋሉ ከራሳቸው ይልቅ የበለጠውን ለወራሾቹ ከአሥሩ ዘጠኝ ጊዜያት ታላቅ እርግማን ይሆናባቸዋል፡፡ ልጆች በወላጆቻቸው ንብረት ታምነው በዚህ ሕይወት ክንውንን ያገኙ ዘንድ ብዙ ጊዜ ሳያሳካላቸው ይቀራል እንዲያውም መጪውንም ሕይወት ፈጽሞ አያገኙትም፡፡CCh 80.2

    ወላጆች ለልጆቻቸው የሚተውላቸው የተሻለው ርስት ጠቃሚውን ሥራ የማወቅ ዕውቀትና ራስን ባለመውደድ የሆነ የልግሥና (የቸርነት) አርአያ በማሳየት ነው፡፡ በእንዲህ ያለ ሕይወት እውነተኛውን የገንዘብ ዋጋነት ይኸውም የራሳቸውን ፍላጎትና የሌሎችን ፍላጎቶች በመርዳት ያምላክን ጉዳይ በማስፋፋት ረገድ ለሚሰጠው ጥቅም ብቻ የሚወደድ መሆኑን ያሳያሉ፡፡ ፳203T399;CCh 80.3