Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ‹‹ባለጠግነታችሁ ቢበዛ ልባችሁን አትጣሉበት››፡፡

    የተለየ የአሥራት አከፋፈል ደንብ (ሲስተም) እንደ እግዚአብሔር ሕግ በጸናው ኘሪንሲኘል ላይ ነበር የተመሠረተው ይህ የአሥራት አከፋፈል ሲስተም ለአይሁዶች በረከት ነበር ያለበለዚያ አምላክ ባልሰጣቸውም ነበር እንደዚሁም እስከ ጊዜው ፍጻሜ ለሚያካሄዱትም በረከት ነው፡፡CCh 80.4

    ያምላክን ጉዳይ በመደገፍ ረገድ በጣም ደንበኞችና ለጋሶች የሆኑ ቤተክርስቲያህት በመንፈሳዊነት እጅግ የተከናወነላቸው ናቸው፡፡ በክርስቶስ ተከታይ የሚገለጸው እውነተኛ ልግሥና ሐሳቡን (ጥቅሙን) ከጌታ ጋር ያዋሕዳል፡፡ ሐብት ያላቸው ሁሉ ለሚያወጡት ብር ሁሉ እግዚአብሔር የሚቆጣጠራቸው መሆኑን ቢገነዘቡ የታሰበው ፍላጎታቸው በጣም ያነሰ ይሆን ነበር፡፡ ሕሊናቸው ንቁ ቢሆን ኑሮ ለፍትወት ለትዕቢት ለከንቱነትና ለመደሰቻ ፍቅር ለሆነው ቅምጥልና የማያስፈልገውን ይዞታ ይመሰክር ነበር፡፡ ለጉዳዩም ሊሰጥ ይገባ የነበረውን የጌታን ገንዘብ ስለ ማባከናቸው ይወራ ነበር፡፡ የጌታቸውን ዕቃዎች የሚያባክኑ ጥቂት በጥቂት ለጌታ የርምጃቸውን ሂሣብ ማቅረብ አለባቸው፡፡CCh 80.5

    ስመ ክርስቲያኖች የሆኑ አካልን በማኔጥና ቤቶቻቸውን በማሳመር ረገድ ሐብታቸውን በአነስተኛው ቢጠቀሙበት ለቅምጥልና በጠረቤዛቸው (በማዕዳቸው) ላይ በሚያበላሽ በተንበሸበሸ ምግብ ላይ በአነስተኛው ቢያወጡ በአምላክ ግምጃ ቤት እጅግ ብዙ ገንዘብ ማስቀመጥ ይችሉ ነበር፡፡ እንዲሁም ሰማይን ሐብቱን ክብሩን ትቶ የዘለዓለምን ሐብት እናገኝ ዘንድ ለኛ ሲል ድሀ የሆነውን መድኃኒታቸውን በተከተሉ ነበር፡፡CCh 81.1

    ዳሩ ግን ብዙዎች ምድራዊ ሐብትን መሰብሰብ ሲጀምሩ የተለየውን የገንዘብ ልክ እንደምን አድርገው በእጅ ለማድረግ ከመቻላቸው በፊት ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድ ሊገምቱ ይጀምራሉ፡፡ ለራሳቸው ሐብትን ለማከማቸት ናፍቆት አድሮባቸው በእግዚአብሔር ዘንድ ሐብታሞች ሳይሆኑ ይቀራሉ፡፡ ልግሥናቸው ከገንዘብ ማከማቸታቸው ጋር ሚዛን ለሚዛን አይደለም፡፡ ለሐብት ምኞታቸው እየበካ ሲሔድ ፍቅራቸው ከመዝገባቸው ላይ ይጣበቃል ለጌታ አሥረኛውን (አሥረትን) መስጠት የጠነከረና የግፍ ግብር እንደሆነ አንዳንዶች እስኪያስቡ ድረስ ንብረታቸው ሲጨማመርላቸው ብዙ ለማግኘት አጥብቀው እንዲመኙ ምኞታቸውን ያጠነክራል፡፡CCh 81.2

    በመንፈስ የተጻፈው ጽሑፍ “ባለጠግነታችሁ ቢበዛ ልባችሁን አትጣሉበት” ብሎአል ብዙዎችም “እንደዚያኛው ሐብታም ሆኜ ብሆን ኑሮ ሥጦታዎቼን በእግዚአብሔር ግምጃ ቤት እሞላ ነበር ሐብቴን ለእግዚአብሔር ከነዚሁ አንዳንዶቹን ሐብት ለነሱ በመስጠት ፈትኖአቸዋል ግን ከሐብቱ ጋር ብርቱ ፈተና መጣባቸው ልግሥናቸው በድህነታቸው ከነበሩበት ቀናት ይልቅ እጅግ ያነሰ ነበር፡፡ ለታላቅ ሐብት የጨበጣቸው ምኞት ሐሳባቸውን ልባቸውን መሠጠባቸው ጣዖትንም አመለኩ፡፡ ፳፩213T401-405;CCh 81.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents