Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ለእግዚአብሔር የተደረገው ስለት የጸናና የተቀደሰ ነው፡፡

    ሁሉም የራሱ መካሪ መሆን አለበት በልቡም የሚያስበው ያህል እንዲሰጥ ያርፍበታል፡፡ ነገር ግን አሥራትን በመክፈል ደንብ (ሲስተም) ረገድ እግዚአብሔር የሚፈልገውን ቢያስቀሩ ወንድሞች ከቶ የማያውቁት የሚመስላቸው እንደ ሐናኒያና ሰጲራ በዚያው ኃጢአት በደለኞተ የሆኑ አሉ፡፡ ምሳሌያቸው ማስጠንቀቂያ ሆኖ የተሰጠን በደለኞች የሆኑ ባልና ሚስት እንዲሁ አሰቡ፡፡ እግዚአብሔር በዚህ ጉዳይ ልብን እንደሚመረምር ያስረዳል፡፡ የሰው ምክንያቶችና ሐሳቦች ከርሱ ሊሠወሩ አይቻልም፡፡ የሰው ልቦች ዘወትር ስለ አከነበሉበት ኃጢአት እንዲጠነቀቁ በዘመናቱ ሁሉ ላሉት ክርስቲያኖች የዘወትር ማስጠንቀቂያ ትቶላቸዋል፡፡ ለጐረቤትም እንደተሰጠው የተጻፈው ኖት (ማስታወቂያ) ነው፡፡ ለእግዚአብሔር ስለት ከመሳል የበለጠ ለገንዘብ አከፋፈል በክርስቲያኑ ላይ የጸና ሕጋዊ ውል የለም፡፡CCh 81.4

    እንደዚሁም ለባልንጀሮቻቸው ተስፋ የሚያደርጉ ሰዎች ወትሮውንም ከተስፋቸው ነጻ ይወጡ ዘንድ ለመጠየቅ አያስቡም የሁሉ ሞገሶች ሰጪ ለሆነው አምላክ የተደረገው ስለት ከዚህ የበለጠ ዋና ነገር ነው እንግዲያውስ ሰው ለእግዚአብሔር ተስፋ ስላደረገ በትንሹ የጸና እንደሆነ ያስበዋልን የተሳለው ስለቱ በፍርድ ቤቶች ለምርመራ የማይቀርብ ስለሆነ እምብዛም የማይጸና ነውን? ወሰን በሌለው በየሱስ ክርስቶስ ደም እድናለሁ የሚለው ሰው “እግዚአብሔርን የሚጋፋ” ይሆናልን ስለቶቹን አድራጎቶቹ በሰማያዊ ፍርድ ቤቶች በፍርድ ሚዛኖች ላይ የሚመዘኑ አይደለምን?CCh 82.1

    ቤተ ክርስቲያኒቱ ለየአባሎቹ ስለቶች አላፊ ናት ስለቶቹን ለመፈጸም ችላ የሚል ወንድም መኖሩን ቢያዩ በቸርነት ለርሱ መሥራት አለባቸው ግን በግልጽ መሆን አለበት፡፡ ስለቱን ይከፍል ዘንድ ከሚቻለው ሁናቴ ላይ ባይሆንና ተገቢ አባል ሁኖ ፈቃደኛ ልብ ቢኖረው በዚያን ጊዜ ቤተ ክርስቲያኒቱ በርህራኄ ትርዳው እንዲሁም ችግሩን አስወግደውለት ራሳቸው በረከትን ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ ፳፪224T469-476;CCh 82.2