Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ ፱—ከክርስቶስ ጋር መተባበርና የወንድማማችነት ፍቅር፡፡

    ልጆቹ በፍቅር ይጣመሩ ዘንድ የእግዚአብሑር ሐሳብ ነው፡፡ በዚያው ሰማይ ባንድነት ለመኖር ተስፋ የሚያደርጉ አይደለምን; ክርስቶስ በራሱ ላይ የተከፋፈለ ነውን; ክፉውን ሐሳብና የጥልን ጉድፍ ጠርገው ከማስወገዳቸው በፊት፣ ሰራተኞቹ በሐሳብ በመተባበር በአምላክ ፊት በጣም የተቀደሰ ለሆነው ሥራው ልብንነ ሐሳብን፣ ኃይልንም ቀድሰው ከመስጠታቸው በፊት ለሕዝቡ ክንውንን ይሰጣልን? ኅብረት ብርታትን ያመጣል፣ አለመተባበርም ድክመትን፡፡ እርስ በርሳችን ስንተባበር ለሰዎችም ደህንነት በስምምነት ባንድነት ስንሰራ በእውነቱ ‹‹የእግዚአብሔር ሰራተኞች ነን ከርሱም ገር እንሰራለን›› በስምምነት ለመስራት የማይፈቅዱ እግዚአብሔርን በጣም ሳፍሩታል፡፡ የነፍሳት ጠላት ለእርስ በርሳቸው በመጨካከን ሐሳብ ሲሰሩ ሊያያቸው ይደሰታል፡፡ እንዲህ ያሉ የወንድማማች ፍቅርና የልብ ርህራኄ እንዲኖራቸው ያስፈልጋቸዋል፡፡ የወደፊቱን የሚጋርድባቸውን መጋረጃ ገለጥ ለማድረግ ቢችሉና የአለመተባበራቸውን ውጤት ቢያዩ ኑሮ በእርግጥ ንስሐ ወደ መግባት ይመሩ ነበር፡፡ ፩18T240;CCh 85.1