Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ ፲፩—የተቀደሰ ሕይወት፡፡

    መድኃኒታችን ከኛ ያለውን ሁሉ ይፈልጋል፡፡ የመጀመሪያውንና የተቀደሰውን ሐሳባችንን ንጹሕና እጅግ የጋለ ፍቅራችንን ይጠይቃል፡፡ በውነቱ የመለኮታዊ ባሕር ተካፋዮች ከሆን ምሥጋናው ዘወትር በልባችንና በከንፈሮቻችን ይሆናል፡፡ ደህንነታችን ለርሱ ሁሉን መስጠትና በጸጋና በእውነት ዕውቀት ዘወትር ማደግ ነው፡፡ ፩1SL95;CCh 93.1

    በቅዱሣት መጻሕፍት በተገለጸው ቅድስና በመላ ሰውነት መንፈስ ነፍስና አካል መሰራጨት አለበት፡፡ እውነተና የሆነ የመላ ቅድስና ሐሳብ እዚህ ነው፡፡ ጳውሎስ በተሰሎንቄ ያለችው ቤተ ክርስቲያን ይህን ትልቅ በረከት ትደሰትበት ዘንድ ይጸልያል፡፡ ‹‹እግዚአብሄርም ራሱ የሰላም አምላክ ሁላችሁን ፈጽሞ ይቀድሳችሁ፡፡ መንፈሳችሁም ነፍሳችሁም ሥጋችሁም ሁለንተናው ያለ ነውር ይጠበቅ ጌታችን የሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ›› (፩ ተሰሎንቄ ፭፣፳፫)፡፡CCh 93.2

    በራሱ አሰት የሆነና በአርአያነቱ አሥጊ የሆነ የልብ ወለድ ቅድስና በሃይማኖታዊ ዓለም ውስጥ አለ፡፡ በብዙ ነገር ቅድስና አለን የሚሉ ዓይነተኛ የሆነው ነገር የላቸውም ቅድስናቸው በንግግርና በፈቃዳቸው ስግደት (አምልኮ) ላይ የተመረኮዘ ነው፡፡CCh 93.3

    ማሰብንና ፍርድን አስወግደው በስሜቶቻቸው ላይ ፈጽመው ይታመናሉ አንድ ጊዜ በተለማመዱት ስሜቶች ላይ ሆነው ፍላጎታቸውን በቅድስና ላይ ይመሠረታሉ፡፡ ብዙ ቀላት እየሰጡለትና ጽኑ የሆነውን የቅድስና ፍላጎታቸውን በማቅረባቸው ገታሮችና ጠማሞች ናቸው ለማስረጃ ግን የከበረ ፍሬ የሚያፈሩ አይደሉም፡፡ እነዚህ አፍዓውያን የተቀደሱ ሰዎቸ በማስመሰላቸው ነፍሳቸውን ብቻ የሚያታልሉ አይደለም ነገር ግን ከአምላክ ፈቃድ ጋር ለመስማማት ከልብ የሚፈልጉትን ብዙዎችን ከመንገድ ለማጥፋት አርአያቸውን ያሳትፋሉ፡፡ ‹‹እግዚአብሔር ይመራኛል ! እግዚአብሔር ያስተምረኛል! ያለ ኃጢአት እኖለሁ›› ሲሉ እየደጋገሙ ሲናገሩ ይሰሙ ይሆናል፡፡ ብዙዎች ከዚህ መንፈስ ጋር ግንኙነት የሚያደርጉ እነሱ ሊያስተውሉ ከማይችሉት አንዳች ጨለማ ከሆነው ምሥጢራዊ ነገር ጋር ግንኙነት ማድረጋቸው ነው፡፡ ነገር ግን እውነተኛ ምሳሌ የሆነውን ክርስቶ ጨርሶ የማይመስል ነው፡፡ ፪2SL 7— 10;CCh 93.4

    ቅድስና የሚቀጥል ሥራ ነው፡፡ ተከታታ እርምጃዎች በጴጥሮስ ቃላት ውስጥ እፊታችን ቀርቦልናል ‹‹ስለዚህም ጥረትን ሁሉ አቅርባችሁ በኃይማኖታችሁ በጎነትን ጨምሩ፡፡ በበጉነትም ዕውቀትን፡፡ በውቀትም መሻትን መግዛት በመሻትም መግዛት ትዕግሥትን፡፡ በትዕግሥትም አምልኮን፡፡ በአምልኮም ወንድሞችን መውደድን፡፡ ወንድሞንም በመውደድ ፍቅርን፡፡ ይህም በላንት ቢሆን ቢበዛም ታካቾችን ያለ ፍሬ አያደርጋችሁም ጌታችን የሱስ ክርስቶስን በማወቅ፡፡ ›› (፪ ጴጥሮስ ፩፣፭—፰)፡፡ ‹‹ስለዚህም እላንት ወንድሞች አብዝታችሁ ተጠ በቁ መጸራታችሁ መመረጻችሁም ትጸና ዘንድ፡፡ ይህንን ብታድረጉት ከቶ አትሰናከሉም፡፡ እንዲሁም በባለጠግነት መግቢያው ይሰጣችኋል ወደ ጌታችንና ወደ መድኃኒታችን ወደ የሱስ ክርስቶስ ወደ ዘላለሙ መንግሥት››፡፡ (ቁጥር ፲ ፡ ፲፩)፡፡ ከቶ የማንወድቅ መሆናችንን የምናረጋግጥበት እርምጃ የኸውና፡፡ ክርስቲያናዊ ጸጋዎች በማግኘት ረገድ በመጨመር ሐሳብ መሠረት የሚሠሩ፤ እግዚአብሔር የመንፈሱን ሥጦታዎች ሲያበረክትላቸው በማብዛት ሐሳብ መሠረት የሚሠራ መሆኑን ማረጋገጫ አላቸው፡፡ ፫3SL94; 95;CCh 93.5

    ቅድስና የአንዳፍታ፤ የአንድ ሰዓት ወይም የአንድ ቀን ሥራ አይደለም፡፡ በጸጋ እየቀጠሉ ዘወትር ማደግ ነው፡፡ በሚቀጥለው ያንዱ ቀን ተጋድሎዋችን እንደምን ብርቱ እንደሆኑ አናውቅም፡፡ ሰይጣን የኖራል፤ ቀልጣፋም ነው፤ እርሱን እንቃወም ዘንድ ለእርዳታና ለኃይል ማግኛ በየቀኑ ወደ እግዚአብሔር ከልብ መጮህ ያስፈልገናል፡፡ ሰይጣን እስከሚገዛበት ጊዜ ራስን ማሸነፍ፤ የሚያይልብንን ኃጢአት ማሸነፍ አለብን፤ ልንመጣበት የሚቻለንን መድረሻውን በምሉ ደርሰንበታል ብለን የምንቆምበት ሥፍራ የለም፡፡CCh 94.1

    ክርስቲያናዊ ሕይወት ዘወትር የመቀጠል ጉዞ ነው፡፡ የሱስ የሕዝቡ እንጣሪና የሚያነጻ ሆኖ ተቀምጧል፤ የርሱ ምሳሌ ፍጹም ሆኖ በውስጣቸው ሲያንጸባርቅ፤ እነሱ ፍጹማንና ቅዱሣን ናቸው፤ ለመወሰድም የተዘጋጁ ይሆናሉ፡፡ ከክርስቲያኑ ትልቅ ሥራ ይፈለጋል፡፡ በፈርሀ እግዚአብሔር ቅድስናን እየፈጸምን ከሥጋና ከመንፈስ እርኩሰት ሁሉ ራሳችንን እንድናነጻ ተመክረናል፡፡ እዚህ ላይ ታላቁ ሥራ የሚያርፍበትን እናያለን፡፡ ለክርስቲያኑ የሚያደርገው የዘወትር ሥራ አለ፡፡ በወላጁ ወይን ጉንድ ያለው ቅርንጫፍ ሁሉ ፍሬ ያፈራ ዘንድ ከዚያው የወይን ጉንድ ሕይወትንና ኃይልን መቅሠም አለበት፡፡ ፬41T340;CCh 94.2

    ማንም ከፍላጎቶቹ ባንዱ ላይ ሲረግጡ እግዚአብሔር ይቅርታ እንደሚሰጣቸውና እንደሚባርካቸው ባላቸው እምነት ራሳቸውን አያታልሉ፡፡ የታወቀውን ኃጢአት ፈቅደው መሥራት የሚመሰክረውን የመንፈስ ቅዱስ ድምጽ ዝም ያሰኝና ነፍስን ከአምላክ ይለያል፡፡ በሃይማኖታዊ ስሜት መፈንደቅ ምንም ይሁን፤ የሱስ የመለኮታዊ ሕግን ቸል በሚለው ልብ ውስጥ ሊኖር አይችልም፡፡ እግዚአብሔር የሚያከብሩትን ብቻ ያከብራል፡፡ ፭5SL92;CCh 94.3

    ጳውሎስ ‹‹እግዚአብሔር ራሱ የሰላም አምላክ ሁላችንም ፈጽሞ ይቀድሳችሁ›› ሲል ጻፈ (፩ ተሰሎንቄ ፭ ፡ ፳፫)፡፡ ሊደርሱበት ወደማይቻለው ደረጃ ያነጣጥሩ ዘንድ ወንድሞቹን አልመከረም፤ ለመስጠትም ያአምላክ ፈቃድ ያልሆነውን በረከቶች ያገኙ ዘንድ አልጸለየም፡፡ ክርስቶስን በሰላ ለመገናኘት ተገቢዎች የሚሆኑ ሁሉ ንጹሕና የተቀደሰ ጠባይ ሊኖራቸው እንደሚገባቸው አወቀ፤ (፩ ቆሮንቶስ ፱ ፡ ፳፭-፳፯፤ ፩ ቆሮንቶስ ፮ ፡ ፩፱ ፡ ፳)፡፡CCh 94.4

    የእውነተኛ ክርስቲያን ፕሪንሲፕል ውጤቶቹን ለማመዛዘን አይቆምም፡፡ ይህን ባደርግ ሰዎች ስለ እኔ ምን ያስባሉ? ወይም ያን ባደርግ የዓለማዊ ዓላማዎቼን እንደምን የሚነካ ነው? ብሎ አይጠይቅም፡፡ እጅግ ጥብቅ በሆነው ናፍቆት የእግዚአብሔር ልጆች ሥራቸው ያስከብረው ዘንድ ምን ሊያደርጉ እንደሚፈለግባቸው ማወቅን ይፈልጋሉ፡፡ ጌታ በዓለም የሚቃጠሉና የሚያበሩ ብርሃናት እንዲሆኑ የተከታዮቹ ልቦችና ሕይወት በመለኮታዊ ጸጋ የተገቱ ይሆኑ ዘንድ ሰፊ መሰናዶ አድርጎዋል፡፡ ፮6SL26; 39;CCh 94.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents