Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    አምላክ እንደሚቀበላቸው ማረጋገጫ ለሚሹ የተሰጠ ምክር፡፡

    አምላክ እንደሚቀበልህ እንደምን ልታውቅ ነው? በጸሎት ቃሉን አጥና፡፡ እንደ ሌላው መጽሐፍ ነው ብለህ ወዲያ ጣል አታድርገው፡፡ ይህ መጽሐፍ ስለ ኃጦአት ያስረዳል፡፡ የደህንነትንም መንገድ በይፋ ይገልፃል፡፡ ብሩህና የተከበረ ዋጋ ያስገኛል፡፡ ፍጹም ስለሆነው መድኅኅ ይገልጽልሃል ወሰን በሌለውም ምሕረቱ ብቻ ደህንነትን ተስፋ ልታደርግ የምትችል መሆንህንም ያስተምርሃል፡፡CCh 99.2

    ምሥጢራዊ (የስውር) ጸሎት ማድረግን ችላ አትብ ሃይማኖት ነፍስ ነውና፡፡ ከልብ ከሆነው የጋለ ጸሎት ለነፍስ ንጽህና ለምን፡፡ ሟቹ ሕይወትህ በአሥጊ ሁኔታ ላ ቢሆን ኑሮ እንደምታደርግለት ከልብ በናፍቆት ለምነ ለደህንነት የማይነገረው ናፍቆት በውስጥህ እስኪሳተፍና ይቅርታ ላገኘህ ኃጢአትህ ጣፋጭ የሆነ ማስረጃ እስክታገኝ በአምላክ ፊት ቆይ፡፡ ፲፬141X163;CCh 99.3

    የሱስ በሚገጥሙህ ፈተናዎችና ችግሮች እንዲደነቅብህ እተወህም፡፡ እርሱ ስለነሱ ሁሉንም ነግሮሃል ፈተናዎች ሲገጥሙህ የማትጣልና የማትጨቆን መሆንህንም ደግሞ ነግሮሃል፡፡ ወደ አዳኝህ ወደ የሱስ ተመልከት ደስ ያለህ ሁን ፈንድቅም፡፡ ለመቻል እጅግ የጠነከሩት ፈተናዎች ከወንድሞቻችን ከዕውቅ ወዳጆቻችን የሚመጡብን ናቸው እነዚህን ፈተናዎች እንኳ በትዕግሥት መቻል ይቻለናል፡፡ የሱስ በዮሴፍ በአዲሱ መቃብር ውስት ያለ አይደለም፡፡ እርሱ ተነስቷል ወደ ሰማም አርጓል እዚያ ለኛ ይጸልይልን ዘንድ፡፡ ለና በመሞቱ እንዲህ የወደደን መድኅን አለን በርሱ አማካይነት ተስፋ ኃይልና ድፍረት እንዲኖረንና ከርሱ ጋር በዙፋኑ ላይ ስፍራ እናገኝ ዘንድ፡፡ በጠራኸው ቁጥር ሊረዳህ የሚችልና ፈቃደኛ ነው፡፡CCh 99.4

    በተሰጠህ የእምነት ሥራ ላይ ሆነህ የማትበቃ መሆንህ ይሰማሃልን? ለዚህ እግዚአብሔር ይመስገን ደካማነትህ ይበልጡን ሲሰማህ ረዳትን ለመሻት በልጥ የምታዘነብል ትሆናለህ፡፡ ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ እርሱም ወደ እላንት ይቀርባልና›› (ያዕቆብ ፬፣፰)፡፡ የሱስ ደስ እንዲልህ እንድትፈነድቅ ይፈልጋል፡፡ እግዚብሔር በሰጠህ ችሎታ የተቻለህን ያህል አድርገህ ከዚያ በኋላ ሸክሞችን በመሸከም ረገድ ረዳቶችህ የሆኑትን ጌታ እንዲረዳህና እንዲያስነሣልህ ትታመንበት ዘንድ ይፈልግሃል፡፡CCh 99.5

    ሰዎች የሚናገሩት ክፉ ንግግሮች አይጉዳህ፡፡ ሰዎች ክፉ ነገር ስለ የሱስ አልተናገሩምን? መሳሳትህ ነው አንዳንድ ጊዜ ለክፉ አነጋገር ምክንያት ትሰጥ ይሆናል የሱስ ከቶ እንዲህ አላደረገም፡፡ እርሱ ንጹህ ነውር የሌለበት እርኩሰትም የሌለበት ነበር፡፡ የክብር መሥፍን ከነበረው በዚህ ሕይወት የተሻለ ድርሻ እንዳለህ ተስፋ አታድርግ፡፡ ጠላቶች የተጎዳህ መሆንህ እንዲሰማህ ሊያደርጉህ እንደሚችሉ ሲያዩ ይደሰታሉ ሰይጣንም ይደሰታል፡፡ ወደ የሱስ ተመልከት ለክብሩ ብቻ በሚመለከት ዓይን ሥራ፡፡ በእግዚአብሔርም ፍቅር ልብህን ጠብቅ፡፡ ፲፭158T128; 129;CCh 99.6

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents