Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ቤተ ክርስቲያን የተጎናጸፈችው ሥልጣን፡፡

    ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን ድምጽ ኃይል (ሥልጣን) ይሰጣል፡፡ ‹‹እውነት እላችኋለሁ፡፡ በምድር ያሠራችሁት ሁሉ በሰማ የታሠረ ይሆናል በምድርም የፈታችሁት በሰማይ የተፈታ ይሆናል፡፡ ማቴ ((፣((፡፡ አንዱ ሰው በግል ኃላፊነቱ ተነስቶ የቤተ ክርስቲያንን ሐሳብ (ፍርድ) ሳያከብር የሚመርጠውን ሐሳብ አንዲያካሔድ እንዲህ ያለ ነገር አልተፈቀደለትም፡፡ እግዚአብሔር ከሰማይ በታች ለቤተ ክርስቲያኑ እጅግ ከፍ ያለ ሥልጣን ሰጥቷታል፡፡ በቤተ ክርስቲን ውስጥ በተባበረው ሕዝቡ ችሎታ የሚነገረው ያምላክ ድምጽ ሚከበር ነው፡፡ 53T450, 4561;CCh 103.4

    ያምላክ ቃል አንድ ሰው የቤተ ክርስቲያንን ሐሳብ (ፍርድ) በመቃወም ሐሳቡን እንዲያካሔድ አይፈቅድለትም ወይም በቤተ ክርስቲያን ሐሳቦች ላይ የራሱን ሐሳቦች ሊመሠርት (ሊያስገድድ) አይፈቅድለትም፡፡ የቤተ ክርስቲን ዲሲፕሊንና አስተዳደር ባይኖር ቤተ ክርስቲያኒቱ ትፈራርሳለች አንድ አካል ሆና በአንድነት ልትጣመር አይቻላትም፡፡ ልክ እንደሆኑ እግዚአብሔር በተለይ እንዳስተማራቸውና እንዳሳሰባቸው እንደ መራቸውም የተናገሩ በራሳቸው ሐሳብ ያደሩ ሰዎች ካሁን ቀደም ነበሩ፡፡ እያንዳንዳቸው የገዛ ራሳቸውን ልብ ወለድ ታሪክ ለየራሳቸውም የተለዩ አስተያየቶች አሏቸው እያንዳንዳቸውም ሐሳባቸው ከአምላክ ጋር የሚስማማ መሆኑንም ይናገራሉ፡፡ እያንዳንዳቸው የተለያዩ የልብ ወለድ ታሪክና ሃይማኖት አላቸው ሆኖም የተለየ ብርሃን ከአምላክ አለን ይላሉ፡፡ እነዚህ ከአካል የሚነጠሉ ናቸው እያንዳንዳቸውም በየራሳቸው የተለያየች ቤተ ክርስቲን ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ ልክ ሊሆኑ አይችሉም ሆኖም ሁላቸው በጌታ የሚመሩ እንደሆኑ ይናገራሉ፡፡CCh 103.5

    መድኃኒታችን ሁለት ወይም ሶስት ሆነው ከአምላክ ማናቸውንም ነገር በመለመን ቢተባበሩ እንደሚሰጣቸው ተስፋ በመስጠት የምክር ትምህርቶቹን ያከታትላል፡፡ ክርስቶስ ከዚህ ከሌሎች ጋር ኅብረት ሊኖረን ለተሰጠን ነገር (ዓላማ) እንኳ በምንመኘው ምኞት እንኳ ቢሆን ኅብረት ሊኖረን እንደሚገባን ሳየናል፡፡ ተባብረን ከምንጸልየው ጸሎት ከሐሳባችንም ኅብረት ጋር ታላቅ ቁምነገረኝነት (ጠቃሚነት) ተያይዞአል፡፡ እግዚአብሔር የእያንዳንዳችንን ጸሎት ይሰማል ነገር ግን በዚህን ጊዜ የሱስ በአዲስነትዋ በምድር በምትቋቋመው ቤተ ክርስቲኑ ላይ የተለየ ዓላማ ያሏቸውን የተለዩና ጠቃሚ ትምህርቶች ተሰጥተውት ነበር፡፡ ለሚመኙትና ለሚጸልዩት ነገሮች ስምምነት ሊኖራቸው ይገባል፡፡ የአንዱ አእምሮ የሚያስባቸው ሐሳቦችና አድራጎቶች ወደ ማታለል ሚያደላውን ሳይሆን ነገር ግን የሚያቀርቡት ልመና የአያሌዎቹ ሐሳቦች በዚያው ሐሳብ ላይ የተነጣጠረ ከልብ የሆነ ምኞታቸው እንዲሆን ነበር፡፡ 63T428, 429;CCh 104.1

    ቤተ ክርስቲያኒቱ ለሰዎች ደህንነት የተሸመች የአምላክ ወኪል ናት፡፡ ለማገልገል የተቋቋመች ናት ሥራዋም ወንጌልን ለዓለም ለማድረስ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያኑ አማካይነት ምላቱና ብቁነቱ (ችሎታው) ለዓለም እንዲብራራ ከመጀመሪያው የአምላክ እቅድ ኑርዋል፡፡ የቤተ ክርስቲያን አባሎች እርሱ ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃኑ የጠራቸው ክብሩን ማሳየት ይኖርባቸዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ የክርስቶስ ጸጋ ብልጽግናዎች መከማቻ ናት፣ በቤተ ክርስቲያኒቱም አማካይነት ‹‹በሰማያዊ ሥፍራዎች ላሉ ገዥዎችና ሥልጣናት›› እንኳ የመጨረሻውና በሙሉ የሚገለጸው የእግዚአብሔር ፍቅር በመደምደሚያው ላይ ይገለጻል፡፡ 7AA9;CCh 104.2