Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ ፲፫—የቤተ ክርስቲያን ድርጅት፡፡

    አንዱ የክርስቶስን መልእክት መፈጸም አለበት፣ አንዱ እርሱ በምድር ሊያደርግ የጀመረውን ሥራ ማካሔድ አለበት፣ ቤተ ክርስቲያኒቱም ይህ መብት ተሰጥቷታል፡፡ የተቋቋመችውም ለዚሁ ሐሳብ ነው፡፡ 16T295; CCh 107.1

    ሰባኮች ሥርዓትን መውደድ አለባቸው፣ እራሳቸወንም በዲሲፕሊን መምራት አለባቸው፣በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን በክንውን በዲሲፕሊን ሊመሩና ደህና እንደ ሰለጠነው የወታደሮች ጭፍራ በስምምነት እንዲሰሩ ሊያስተምሩዋቸው ይችላሉ፡፡ ዲሲፕሊንና ሥርዓት በዘመቻ ቦታ ለክንውን ሥራ የሚያስፈልጉ ከሆነ የምናገኘው ነገር ዋጋው በዘመቻ ቦታ ተቃዋሚዎቹ ኃይሎች ከሚታገሉበት የበለጠ ስለሆነና በጠባዩም ይበልጥ ከፍ ያለ ስለሆነ እኛም የምንጋጠመው ጦርነት እንደዚሁ በይበልጥ የሚያስፈልገው ነው፡፡ እኛም በምነጋጠመው ጦርነት (ተጋድሎ) ዘላለማዊ ሐሳባችን (ጥቅማችን) እክል ያገኘዋል፡፡CCh 107.2

    መላእክት በስምምነት ይሰራሉ፡፡ በእንቅስቃሴዎቻቸው ሁሉ ፍጹም የሆነ ሥርዓት አላቸው፡፡ የመልአክን ጭፍራ ስምምነትና ሥርዓት በይበልጥ በመቀራረብ ስንከታተል ለኛ ሲሉ እነዚህ ሰማያዊ ወኪሎች የሚደርጉት ጥረት በይበልጥ የተከናወነ ይሆናል፡፡ ከላይ ከፍ ባለው ቅብዓ ቅዱስ ያላቸው በጥረቶቻቸው ሁሉ ሥርዓትን ዲሲፕሊንና በሥራ መተባበርን ያጠብቃሉ፣ በዚያን ጊዜ ያምላክ መላእክት ከነሱ ጋር ተባበረው መሥራት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን እነዚህ ሰማያዊ መልእክተኞች በሥርዓተቢስነት በድርጅት አልባና በዘረክራካነት ላይ ምስክርነታቸውን ከቶ አያቀርቡመ፡፡ እነዚህ ክፉ ሥራዎች ሁሉ ሰይጣን ኃይሎቻችንን ለማድከም ድፍረትን ለማሳጣትና ተከናዋኙን ሥራ ለማገድ የሚያደርጋቸው የጥረቶቹ ውጤት ናቸው፡፡CCh 107.3

    ሰይጣን በሥርዓትና በስሙሙ ስራ ብቻ ክንውን ሊገኝ እንደሚቻል ደህና አድርጎ ያውቃል፡፡ ከሰማ ነክ የሆነ ነገር ሁሉ ፍጹም በሆነው ሥርዓት ላይ መሆኑን ተገዢነታቸውና የተሟላ ዲሲፕሊናቸው የመልአክን ጭፍራ እንቅስቃሴዎች ያመለክታል፡፡ በተቻለው ሁሉ አፍዓውያን ክርስቲያኖችን ከሰማ ሥርዓት የራቁ አድርጎ ይመራቸው ዘንድ የተጠና ጥረቱ ነው ስለዚህ ዓፍዓውያን የሆኑትን ያምላክ ሕዝብ ያታልላል፣ ሥርዓትንና ዲሲፕሊን ለመንፈሳዊነት ጠላቶች እንደሆኑ እያንዳንዱ የገዛ እርምጃውን እንዲከተልና በተለይም ከተባበሩት የክርስቲያኖች አካሎች ዲሲፕሊንና የሥራ ስምመነትን ለማቋቋም (ለማደርጀት) ከሚሰሩት የተለዩ መሆን ለነሱ ደህንነታቸው እንደሆነ እንዲያምኑ ያደርጋቸዋል፡፡ ሥርዓትን ለማቋቋም የተደረጉት ጥረቶች አሥጊ እንደሆነና የመብታዊ ነፃነት ክልከላ እንደሆነ ይታሰባሉ እንግዲህ ግፈኝነት እንደሆነም ይፈራል፡፡ እነዚህ የተታለሉት ነፍሳት ስለ ነጻነታቸው ሊጀነኑና ተነጥለው ማሰብነ መሥራት በጎ ሥራ እንደሆነ ያስባሉ፡፡ ሰው እንደዚህ ይላል የሚሏቸውን ማንኛውንም አይቀበሉም፡፡ ማንኛውንም ሰው የሚቀበሉም አይደሉም፡፡ ለራሳቸውም ፈልስፈው የገዛ ራሳቸውን እርምጃ መርጠው ከወንድሞቻቸው ተነጣይ በመሆን ሰዎች ያማላክ ሥርዓት እንደሆነ እንዲሰማቸው መምራት የሰይጣን ልዩ ሥራ መሆኑ ታየኝ፡፡ 2IT649, 650;CCh 107.4

    እግዚአብሔር በምድር ያለችውን ቤተ ክርስቲኑን የብርሃን መገናኚያ አድርጎአታል፣ በርሷም አማካይነት ሐሳቦቹንና ፈቃዱን ይናገራል፡፡ ከአገልጋዮቹ አንዱ በተነጣይነት በራሱ የሚያድር እንዲሆንና ለቤተ ክርስቲያንም ለራስዋ አቋም ተቃዋሚ የሚሆንበትን ሥራ አይሰጠውም፡፡ ወይንም ቤተ ክርስቲያኒቱ የክርስቶስ አካል በጨለማ ውስጥ ስትሆን ሳለ፣ ላንዱ ሰው የፈቃዱን ዕውቀት ለመላዋ ቤተ ክርስቲያን ብሎ የሚሰጠው አይደለም፡፡ እርሱ በቸርነቱ፣ በራሳቸው ያነሰ እምነት እንዲኖራቸውና ስራውን ለማስፋፋት በሚመራቸው በሌሎቹ ላይ ታላቅ እምነት ይኖራቸው ዘንድ አገልጋዮቹን ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጋር አቀራርቦ ያገናኛቸዋል፡፡ 3AA163;CCh 108.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents