Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መለያየትን (ፀብን) መጋጠም፡፡

    በየሩሳሌም ከአንጾኪያ የመቱ መልእክተኞች ለጠቅላላ ስብሰባ የተሰበሰቡትን ከልዩ ልዩ ቤተ ክርስቲያናት የሆኑትን ወንድሞች ተገናኙዋቸው፣ በአሕ ዛቦችም መኻከል ባደረጉት አገልግሎት የተገኘውን ክንውን ነገሩዋቸው፡፡ እነሱም ከዚያ በኋላ የታወቁ አማኞች ፈሪሳውያን ለመዳን አማኞች አሕዘቦች መገዘርና የሙሴን ሕግ መተበቅ እንደሚገባቸው ወደ አንጾኪያ ሔደው ስለ ተናገሩ ብጥብጥ መነሳቱን ገልጸው የብጥብጡን አስተዋጽዖ ሰጡ፡፡ ይህን ጥያቄ በጉባዔው በጋለ አኳኋን ተከራከሩበት፡፡CCh 108.5

    በመንፈስ ቅዱስ በአሕዛብ ምዕመናን ላይ የሜዳዊውን ሕግ እንዳይጭኑባቸው መልካም መሆኑን አየ፣ የሐዋርትም ሐሳብ ስለዚህ ነገር እንደ እግዚአብሔር መንፈስ ሐሳብ ነበር፡፡ ያዕቆብ የምክር ቤቱ አለቃ ሆኖ ሲመራ የመጨረሳ ውሳኔው፣ ‹‹ስለዚህም እኔ እፈርዳለሁ ከአሕዛብ ወደ እግዚአብሄር የተመለሱትን እንዳታደክሙ›› የሚል ነበር፡፡ ይህም ክርክሩን ከፍጻሜ አደረሰው፡፡CCh 109.1

    በዚህን ጊዜ ያዕቆብ በምክር ቤቱ የተወሰነውን ውሳኔ ለመናገር የተመረጠ ይመስላል፡፡ የአሕዛብ ምዕመናን ከክርስቲያንነት ፕሪንሲፕል ጋር የሚቃወሱትን ልማዶች እንዲተው ነበር፡፡ ሐዋርያትና ሽማግሎች ስለዚህ ለጣዖታት የቀረበውን መብል ዝሙትን፣ የታነቀውንም፣ ደምንም መብላት እንዲተው ለአሕዛቦች በደብዳቤ እንዲያስታውቋቸው ተስማሙ፡፡ ትእዛዛትን እንዲጠብቁና በተቀደሰው አኗኗር እንዲመሩ እንዲነገራቸው ነበር፡፡ መገዘር የሚጸናባቸው መሆኑን የተናገሩ ሰዎች ይህን ለማድረግ በሐዋርያት የተፈቀደላቸው አለመሆኑንም ደግሞ እንዲረጋገጥላቸው ነበር፡፡6AAI90 -195;CCh 109.2

    ይህ ጉዳይ የወሰነው ምክር ቤት ከልዩ ልዩ ሥፍራዎች የተመረጡትን መልእክተኞ ጭምር የኤሁድንና የአሕዛብን ክርስቲያናዊት ቤተ ክርስቲያን ያቋቋሙ ከፍ ያሉ ሐዋርያትና መምሕራን ነበሩበት፡፡ ከየሩሳሌም ሽማግሎች ከአንጾኪያም መልእክተኞች እዚያ ነበሩ፡፡ እጅግ አነቃቂዎች የሆነ የቤተ ክርስቲያናት እንደራሴዎች ነበሩ፡፡ ምክር ቤቱ በተብራራላቸው ፍርድ መሠረትና በመለኮታዊ ፈቃድ በተቋቋመችው በቤተ ክርስቲን አክብሮት (ማዕረግ) በመመራ አካሔደው፡፡ ነገሩን ከማመዛዘናቸው የተነሳ እግዚአብሄር ራሱ ለአሕዛቦች መንፈስ ቅዱስን በመስጠት ጥያቄውን እንደመለሰላቸው ሁላቸውም አዩ የመንፈስ ቅዱስንም መሪነት መከተል ፈንታቸው እንደሆነ ተገነዘቡ፡፡CCh 109.3

    ክርስቲያኖች በሙሉ በጥያቄው ላይ ምርጫ ያደርጉ ዘንድ አልተጠሩም ነበር፡፡ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ተሰሚ የሆኑና የፍርድ ሰዎች የሚነገረውን አዋጅ ሰውነው አወጡ፡፡ ይህነንም ቤተ ክርስቲያናት በጠቅላላው ተቀበሉት፡፡ ነገር ግን በውኔው የተደሰቱት ሁሉም አይደሉም፣ ዕብሪተኞችና በራስ የሚታመኑ ወንድሞች በዚህ ያልተስማሙ ቅሬታ ነበረባቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች በራሳቸው ኃላፊነት መስራት ጀመሩ፡፡ አዳዲስ ሐሳቦች እያቀዱና እግዚአብሔር የወንጌልን መልእክት እንዲያስተምሩ ያዘዛቸውን ሰዎች ሥራቸውን ለማፍረስ ሲሹ በብዙ በማጉረምረምና ስሕተት በመፈለግ ላይ አዘነበሉ፡፡ ከመጀመሪያው ቤተ ክርስቲያኒቱ የምትጋጠማቸው እንቅፋቶች ነበሩዋት፣ እስከ ጊዜውም ፍጻሜ ድረስ ዘወትር ገጥማታል፡፡7AA196, 197;CCh 109.4