Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ ፲፬—የእግዚአብሔር ቤት፡፡

    ለትሑቱ አማኝ ነፍስ በምድር ያለችው የእግዚአብሔር ቤት የሰማይ ደጅ ነው፡፡ የምስጋና መዝሙር ጸሎት በክርስቶስ እንደራሴዎችም የተነገሩት ቃላት ለላይኛዋ ቤተ ክርስቲያን ሚያረክሰው ነገር ሊገባበት ለማይችል ለዚየኛው እጅግ ከፍ ላለው ጸሎት (ስግደት) ሕዝብን ለማዘጋጀት የተቋቋሙ የአምላክ አማካዮች ናቸው፡፡CCh 113.1

    ቤት ለቤተሰብ መቅደስ ነው፡፡ እልፍኝ ወይም ጫካ ለሰው የጸሎት ጽሞና ሥፍራ ነው ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን ለጉባዔ ቤተ መቅደስ ነው፡፡ ስለ ጊዜው ለሥፍራው የጸሎትም ማድረጊያ ደንቦች ሊኖሩት ይገባል፡፡ የተቀደሰው ለእግዚአብሄር ስግደት የሆነ ነገር ያለ መጠንቀቅና በቸልተኝነት መካሔድ የለበትም፡፡ ሰዎች ለእግዚአብሔር ምስጋና በማቅረብ የተቻላቸውን ሥራ እንዲያደርጉ ሕብረተ ሰብነታቸው በሐሳባቸው ውስጥ የተቀደሰውን ከተራው የተለየ አድርጎ የሚጠብቅ መሆን አለበት፡፡ ሰፊ ሐሳቦች የተከበሩ እቅዶችና ናፍቆቶ ያላቸው የመለኮታዊ ነገሮችን ሐሳቦች ሁሉ የሚያጠነክር ኅብረተሰብ ያላቸው ናቸው፡፡ ቤተ መቅደስ ከፍ ያለ ዝቅም ያለ ቢሆን በከተማ ወይም በሸረፍራፋዎቹ የተራራ ዋሻዎች መኻከል ቢሆን በዝቅተኛውም ጎጆ ውስጥ ወይም በምድረ በዳም ቢሆን መቅደስ ያላቸው ደስ ያላቸው ናቸው፡፡ ለጌታ የተሻለ ሆኖ ሊያገኙ የሚችሉ ከሆነ እዚያ በመገኘቱ ሥፍራውን ይቀድሰዋል ለሠራዊት ጌታም የተቀደሰ ይሆናል፡፡CCh 113.2