Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    በሚታይ አምላክ ፊት እንዳለህ አድርገህ ሥራ፡፡

    ለአምላክ ከበሬታ መስጠት ወሰን የሌለው ታላቅነቱ ሊሰማንና አብሮን መሆኑን ስንገነዘብ የተነቃቃ ይሆናል፡፡ የማይታየው አብሮን መሆኑን በሚሰማን በዚሁ ስሜት ልብ ሁሉ በጠለቀ ሐሳብ ሊሳተፍ ይገባል፡፡ የጸሎት ሰዓትና ሥፍራ የተቀደሱ ናቸው፡፡ አምላክ እዚያ ነውና ከበሬታም በአስተያየትና በአካሔድ ሲገለጽ የሚያነቃቃው ስሜት የጠለቀ ይሆናል፡፡ ባለመዝሙሩ ‹‹ስሙ የተቀደሰ የተፈራ ነው›› ሲል ይናገራል፡፡ (መዝሙር (((፡ ()3GW 176-178; CCh 114.3

    ስብሰባው በጸሎት ሲከፈት ጉልበት ሁሉ በቅዱስ አምላክ ፊት መንበርከክ አለበት ልብም ሁሉ በጽሞና ጸሎት ወደ አምላክ መቅረብ አለበት፡፡ የታመኑት ሰጋጆች ጸሎታቸው ይሰማል የቃሉም ስብከት ፍሬያማ መሆኑን ያስረዳል፡፡ በቤተ እግዚአብሔር ያሉ የሰጋጆቹ ሕይወት የሌለው ሁናቴ ስብከት አገልግሎቱ ይበልጥ ፍሬ ያለው ጥቅም የማይሰጥ መሆኑ ስለምን እንደሆነ አንደኛው ታላቁ ምክንያት ነው፡፡ የመዝሙር ዜማ ዕውቅ በሆነውና ግልጽ በሆነው አነጋገር ከብዙ ልቦች የሚፈሰው ነፍሳትን በማዳን ሥራ ረገድ ከአምላክ መሣሪያዎች አንዱ ነው፡፡ አገልግሎቱ ሁሉ በጉባዔዎቹ ጌታ ፊት የሚታይ ሁኖ በከበሬታና በፈርሃ እግዚአብሔር ሊካሔድ ይገባል፡፡ ቃሉ ሲነገር በተላከው አገልጋዩ አማካይነት ያምላክን ድምጽ የምትሰሙ እንደ ሆናችሁ ወንድሞቼ ሆይ ማሰብ ይገባችኋል፡፡ ተጠንቅቃችሁ አዳምጡ፡፡ አንዳፍታ እንኳ አታንቀላፉ በዚህ እንቅልፍ የተነሳ ያንኑ አብዝታችሁ የምትፈልጓቸውን ቃላት ማለት እነዚያኑ ቃላት ብትቀበሏቸው ወደ ስህተት ጎዳናዎች ከመቅበዝበዝ እግሮቻችሁን የሚያድኑላችሁን ታጣላችሁና፡፡ ሰይጣንና መላእክቱ የተሰጡትን ማስጠንቀቂያዎች ግሣጼዎችና ምክሮች እንዳሰሙ ወይም ቢሰሙም በልብ ውስጥ ፍሬ አግኝተው ሕይወትን እንዳያሻሽሉ ለስሜቶችም የደነዘዘ ሁኔታ በመፍጠር ላይ ትጉዎች ናቸው፡፡ ተወዳጁ ዘር በመልካም መሬት ላይ ወድቆ ፍሬ እንዳያፈራ አንዳንድ ጊዜ ትንሹ ልጅ የሰሚዎችን ሐሳብ ይስብ ይሆናል፡፡ አንዳንድ ጊዜም ወጣቶቹ ወንዶችና ሴቶች በስብከት ጊዜ እርስበርሳቸው ንግግር በመቀጠላቸው ለእግዚአብሔር ቤትና ለአምላካዊ አምልኮት ትንሽ ከበሬታ የሚያደርጉ ናቸው፡፡ እነዚህ የእግዚብሔር መላእክት እየተመለከቷቸው አድራጎታቸውን ምልክት የሚያደርጉበት መሆናቸውን ለማየት ብችሉ ኑሮ በኃፍረት ራሳቸውንም በመጥላት በተመሉ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ጥንቁቆች ሰሚዎችን ይፈልጋል፡፡ ሰይጣን እንክርዳዶቹን የዘራ ሰዎች ተኝተው (አንቀላፍተው) ሳሉ ነው፡፡CCh 114.4

    የማሳረጊያ ጸሎት ሲደረግ የክርስቶስን ፊት እንዳያጡ በመፍራት ሁሉም እንግዲህ በጸጥታ መሆን አለባቸው፡፡ ሁሉም ያለ ግፊያ ወይም የጫጫታ ንግግር ሳያደርጉ በአምላክ ፊት እንደሆኑ ዓይኑም እንደሚያርፍባቸውና በሚታየው አምላክ ፊት እንደሆኑ አድርገው መሥራት እደሚገባቸው እየተሰማቸው ይለፉ፡፡ ለመጎብኘት ወይም ለማውራት ሌሎች ሊያልፉ እንዳይችሉ እያገዱዋቸው በመተላለፊያዎች ውስጥ መቆም ተገቢ አይደለም፡፡ የቤተ ክርስቲያን አካባቢ በተቀደሰው ከበሬታ መጠበቅ አለበት፡፡ የጥንት ወዳጆችን ሚገናኙበትና የሚጎበኙበት ተራም ሐሳቦችንና ዓለማዊ የሆኑትን የንግድ ሥራዎች የሚነጋገሩበት ሥፍራ መሆን የለበትም፡፡ እንዲህ ሉትን ነገሮች ከቤተ ክርስቲያን ውጭ መተው ነው፡፡ እግዚአብሔርና መላእክት በአንዳንድ ሥፍራዎች እግሮቻቸውን እየጎተቱ በማይጠነቀቁት እየተንጫጩ በሚስቁት አልተከበሩም፡፡CCh 115.1