Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ልጆች ከበሬታ የሚሰጡ መሆን አለባቸው፡፡

    ወላጆች የክርስቲያንነትን ዓላማ በልጆቻችሁ ሐሳብ ውስጥ ከፍ አድርጉ የሱስን ብምምዳቸው እንዲያዋሕዱ እርዱዋቸው ለአምላክ ቤት እጅግ ከፍ ያለ ከበሬታ እንዲኖራቸውና ወደ እግዚአብሔር ቤት ሲገቡ በእንደነዚህ ባሉት ሐሳቦች በለሰለሱና በገር ልቦች መሆን እንደሚገባቸው ያስተውሉ ዘንድ አስተምሩዋቸው፡፡ ‹‹አምላክ እዚህ ነው ይህ የርሱ ቤት ነው ንጹህ ሐሳብና እጅግ የተቀደሰ ዓላማ ሊኖረኝ ይገባኛል፡፡ ትዕቢት ቅናት ምቀኝነት ክፉ ሐሳብ ጥላቻ ወይም ማታለል በልቤ ውስጥ ሊኖር አይገባም በቅዱስ አምላክ ፊት መምጣቴ ነውና፡፡ ይህ አምላክ ተገናኝቷቸው ሕዝቡን የሚባርክበት ስፍራ ነው ልዑልና ቅዱስ አምላክ ለዘለዓለም የሚኖር ይመለከተኛል ልቤንም መረምራል ሕይወቴንም እጅግ ምሥጢራዊ የሆኑትን ሐሳቦችና አድራጎቶች ያነባል››፡፡CCh 115.2

    ገራገርና ተጠራጣሪ የሆነው የወጣት ሐሳቦች ያምላክን አገልጋዮች የሥራቸውን ግምት የሚያገኙት ወላጆቻቸውን ስለ ጉዳዩ በሚያወሱት ጎዳና ነው፡፡ ብዙዎች የቤተሰቦች አለቆች የሆኑ ጥቂት ነገሮች እየተቀበሉ ሌሎችን በመንቀፍ የስብከት አገልግሎትን በቤት የመነቃቀፍ ጉዳይ ያደርጉታል፡፡ በእንዲህ ለሰዎች የቀረበው ያምላክ መልእክት ይነቀፍና ይጠራጠሩበታል የቅሌት ጉዳይም ያደርጉታል፡፡ እነዚህ የማይጠነቀቁት ከበሬታ የሌላቸው ምልክት ያለባቸው እንዲህ አድርገው ለወጣቶች ያሳተፉትን ሐሳብ የሰማይ መጻሕፍት ብቻ ይገልጹታል፡፡ ልጆች እኒህን ነገሮች ወላጆቻቸው ለማሰብ ከሚያቀለጥፉት ይልቅ በጣመ ፈጥነው የሚያዩና የሚያስተውሉ ናቸው፡፡ የሞራል (የግብረገብ) ሐሳባቸው ጊዜ ፈጽሞ የማለውጠውን የስህተት ዝንባሌ ይቀበላል፡፡ ወላጆች የልጆቻቸው ልብ በመንደንደኑና የግብረገብ ስሜታቸው ለአምላክ ፍላጎቶች መልስ ለመስጠት በማነቃቃት ረገድ ችግር በመሆኑ ወላጆች ያለቅሱበታል፡፡45T493-197; CCh 115.3

    ከበሬታን ደግሞ ለአምላክ መስጠት ተገቢ ነው፡፡ ይህን ስም በቀላል ወይም ያለ ሐሳብ መናገር ተገቢ ኤደለም፡፡ በጸሎት ጊዜ እንኳ ስሙን አህንም አሁንም ወይም ሳያስፈልግ ደጋግሞ አለማንሳት ተገቢ ነው፡፡ ‹‹ስሙ የተቀደሰ የተፈራ ነው››፡፡ (መዝሙር (((፡():: መላእክት ስሙን ሲናገሩ ፊታቸውን ይጋርዳሉ፡፡ እንግዲህ እና የወደቅንና ኃጢአተኞች የሆነ በከንፈሮቻችን በምን ከበሬታ ልናነሳው ይገባን ይሆን!CCh 116.1

    ያምላክን ቃል ማክበር አለብን፡፡ ለታተመው ቮሊዩሙ ከበሬታ ማሳየት አለብን እንደ ተራ ነገር አድርገን መጠቀም ወይም ያለ ጥንቃቄ ከቶ መያዝ የለብንም፡፡ ቅዱሱን ጽሑፍ ለቀልድ መጥቀስ ወይንም የብልጠት አነጋገር ለማመልከት ከቶ ቃሉነ ማውሳት ተገቢ አይደለም፡፡ ‹‹የእግዚአብሔር ቃል ፈጽማ የተፈተነች ናት››፡፡ በምድር መቅለጫ እንደ ተፈተነ ብር ሰባት ጊዜ እንደ ጸራ››፡፡ (ምሳሌ ( ( መዝሙር (( ()፡፡CCh 116.2

    ከሁሉም በላይ እውነተኛ ከበሬታ በመታዘዝ መሆኑን ልጆች ይማሩ፡፡ እግዚአብሔር የመያስፈልገውን ነገር ምንም አላዘዘም እርሱ ለተናገረለት እንደ መታዘዝ ያለ በጣም የሚያስደስተው ከበሬታ የሚገለጽበት ሌላ መንገድ የለም፡፡CCh 116.3

    ለአምላክ እንደራሴዎች ማለት ለሰባኮች፣ ለመምሕራንና በርሱ ፈንታ ለመናገርና ለመሥራት ለተጠሩት ወላጆች ከበሬታ መስጠት ተገቢ ነው፡፡ ለነሱ ከበሬታ በመስጠት እርሱ ይከበራል፡፡5Ed236, 243, 244; CCh 116.4

    እግዚአብሔር በተለይ አብሮን በመገኘት የተመለከተውን ሥፍራ እንደምን ልንመለከተው እንደሚገባን የሚያሳዩንን የቅዱስ ጽሑፍ ቃላት ማሰብ ለሽማግሎችና ለወጣቶች ደህና ነው፡፡ ‹‹ከግርኸ ጫማኸን አውታ አንተ የምትቆምባት ሥፍራ የተቀደሰች ምድር ናትና›› ሲል በሚቃጠል ቁጥቋጦ ውስጥ ሙሴን አዘዘ ‹‹አንተ የምትቆምባት ሥፍራ የተቀደሰች ምድር ናትና››፡፡ (ዘፀዓት (፡():: ያዕቆብ የመላእከትን ራእይ ካየ በኋላ ‹‹በእውነት እግዚአብሔር ከዚኽ ነው እኔ አላውቅም ነበርሁ፡፡ … ይህ ምንድር ነው የእግዚአብሔር ቤት እነጂ ይህም የሰማይ ደጅ ነው›› ሲል ተናገር፡፡ (ዘፍጥረት ((፡((፡(()፡፡ 6GW 176, 179;CCh 116.5

    በትእዛዝም ሆነ በምሳሌ ሃይማኖትህን እንደምታከብር ስለ የተቀደሱት ነገሮች በአክብሮት መናገርህን ማሳየት አለብህ፡፡ ቅዱስ ጽሑፉን ስትጠቅስ አንዳችም የማቅለልና የቀልድ ነገር ከከንፈርህ እንዲያመልጥህ ከቶውን አትፍቀድ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን በእጅህ ይዘህ ሳለህ በቅዱስ ሥፍራ መሆንህን አስ ታውስ፡፡ መላእክት በአካባቢህ ናቸው ዓይኖችህንም ለመግለጥ ቢቻልህ ኖረ ትመለከታቸው ነበር፡፡ በምትወዳቸው ነፍስ ሁሉ ላይ ያን የሚከብህን ንጹህ የሆነ የተቀደሰ አየር የምታሳትፍበትን ሐሳብ የምትተውለት መሆንህን ሚያመለክት ዓመል ይኑርህ፡፡ አንድ ከንቱ ቃል አንዱም ቀልድ ሳቅ በስህተት አቅጣጫ ነፍስን ሊመዝን ይችላል፡፡ ከአምላክ ጋር ዘወትር ግንኙነት አለማድረግ ፍሬዎቹ የሚያስፈሩ ናቸው፡፡ 7FE !94, 195;CCh 116.6