Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ወላጆች አልባ ለሆኑት መጠንቀቅ፡፡

    ከኛ ለመጠቀም ፍላጎታቸው ከሚጠይቅብን ሁሉ መኻከል ባልቴትና አባት አልባ የሆኑት ታላቅ ርህራኄ ልናደርግላቸው እጅግ በጣም የሚፈልጉብን ናቸው፡፡ እነሱ የጌታ የሆኑ ልዩ ጥንቃቄ የምናደርግላቸው ዓላማዎች ናቸው፡፡ እነሱ ለእግዚአብሔር መተማመኛ (በአደራነት) ሆነው ለክርስቲያን ውሰት የተሰጡ ናቸው፡፡ ‹‹የነጻች በእግዚአብሔር ዘንድም ያላደፈች አምልኮ ይህች ናት ሰው አባትና እናት የሌላቸውን ባልቴቶችንም በመከራቸው ይጐበኛቸው ዘንድ ራሱንም ከዓለም እርኩሰት ይጠብቅ ዘንድ›› ፤ ያዕቆብ ፩፡፲፯፡፡CCh 128.2

    ብዙዎች በኃይማኖት የሞቱ አባቶች በዘላለማዊ ያምላክ ተስፋ አርፈው ተወዳጆቻቸውን ጌታ እንደሚጠነቀቅላቸው በምሉ በማመን ተለይተዋቸዋል፡፡ እንግዲህ ለነዚህ ወላጅ አልባ ለሆኑት ጌታ እንደምን ያስናዳቸዋልያ ከሰማይ መና በላክ ተዓምር አይሠራም፤ ምግብም እንዲያመጡላቸው ቁራዎችንም አይልክላቸውም ነገር ግን ከነፍስ ራስን መውደድ እያስወገደ፤ የቸርነትንም ምንጮች እያመነጨ በሰዎች ልቦች ውስጥ ተዓምር ያደርጋል፡፡ የተቸገሩትንና ወላጅ አልባ የሆኑትን ለመተዛዘኛ ምሕረታቸው አደራ በመስጠት ተከታዮች ነን የሚሉትን ፍቅራቸውን ይፈትናል፡፡CCh 128.3

    እንግዲህ የእግዚአብሔር ፍቅር ያላቸው እነዚህን ልጆች ለመውሰድ ልባቸውንና ቤቶቻቸውን ይከፈቱላቸው፡፡ በትላልቅ ድርጅቶች ላሉት መጠንቀቅ የተሻለ ፕላን አይደለም፡፡ ሊደግፉዋቸው የሚችሉ ዘመዶች ባይኖሩዋቸው የቤተክርስቲያን አባሎች እነዚህን ትናንሾች ወደ ቤተሰቦቻቸው ወስደው ማሳደግ ወይም በሌሎች ቤተሰቦች ዘንድ ለነሱ ምቹ ቤቶች መፈለግ ነው፡፡CCh 128.4

    እነዚህ ልጆች ክርስቶስ በተለይ የሚያስብላቸው ናቸው እነሱንም ችላ ማለት እርሱን የመበደል ያህል ነው፡፡ በየሱስ ስም የተደረገላቸውን የቸርነት አድራጎት ሁሉ ለራሱ እንደ ተደረገው አድርጎ እርሱ ይቀበለዋል፡፡፲፩116T28I.CCh 128.5