Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በኅብረት ኃይል አለ፡፡

    ለኅብረት አጥብቃችሁ ተጣጣሩ፡፡ ስለርሱም ጸልዩ ስለርሱም ሥሩ፡፡ መንፈሳዊ ጤነን የሐሳብ ከፍተኛነትን፣ የጠባይ ጨዋነትን፣ ሰማያዊ ሐሳብን ያመጣል፣ ራስንም መውደድንና ክፉ ሐሳቦችን እንድታሸንፉና በወዳጃችሁና ራሱንም ለናንተ በሰጠው አማካይነት ከአሸናፊዎች በላይ ትሆኑ ዘንድ ያስችላችኋል፡፡ ራስን ወዲያ ስቀሉት፣ ከራሳችሁ የበለጠ ሌሎችን አክብሩ፡፡ በእንገዲህ ከክርስቶስ ጋር አንድነት ይኖራችኋል፡፡ በሰማያዊ ዓለማት (ዩኒቨርስ) በቤተ ክርስቲያኒቱና በዓለም ፊት ያምላክ ወንዶችም ሴቶችም ልጆች እንደሆናችሁ የማይሳሳት ማስረጃ ይኖራችኋል፡፡ በምታሳዩትም ምሳሌ አምላክ ይመሰገናል፡፡CCh 133.1

    ዓለም ያምላክን ሕዝብ ልብ በክርስቲያናዊ ፍቅር ባንድነት የሚያስተሳስር ተዓምር በፊቱ እንዲደረግ ለማየት ይፈልጋል፡፡ በሰማያዊ ሥፍራዎች በክርስቶስ ባንድነት ሲቀመቱ ለማየት ይፈልጋል፡፡ ያምላክ እውነት ለሚወዱትና ለሚያገለግሉት ሊያደርግ የሚችለውን ማስረጃ (ምስክርነት) በሕይወታችሁ አትሰጡምን( እግዚአብሔር ምን ለመሆን እንደምትችሉ ያውቃል፡፡ ያምላክ ባሕርይ ተካፋዮች ከሆናችሁ መለኮታዊ ጸጋ ምን ሊያደርግላችሁ እንደሚችል ያውቃል፡፡59T188;CCh 133.2

    ‹‹እለምናችኋለሁ ግን ወንድሞቼ ሆይ በጌታችን በየሱስ ክርስቶስ ስም የምትናገርዋት ነገር አንዲት ትሆን ዘንድ ለሁላችሁ፡፡ በላንትም መኻከል መለያየት አይሁን፡፡ የጸናችሁም ትሆኑ ዘንድ ባንድ ልብ ባንድም ምክር››፡፡CCh 133.3

    ኅብረት ኃይል ነው መለያየት ድክመት ነው፡፡ ያሁኑን እውነት የሚያምኑ ሲተባበሩ የሚናገር አርአያነት (ኃይል) ያሳያሉ፡፡ ሰይጣን ይህንን ደህና አድርጎ ያስተውላል መማረርንና ፀብን በአምላክ ሕዝብ መኻከል በመንዛት ያምላክን እውነት ፍሬቢስ በማድረግ ካሁን ይበልጥ ቁርጠኛ ሆኖ አያውቅም፡፡65T236CCh 133.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents