Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ ፬—የሚስስ ኢ ጂ ኋይት ሕይወትና ሥራ ፡፡

    ኤሌን ጂ ሐርሞንና መንታ የሆነች እህቷ በዩናይትድ ስቴትስ ሰሜናዊ ምሥራቅ ክፍል በጎርሐም ሜይን ኅዳር ፳፯ ቀን ፲፰፻፳፯ ዓ.ም እ.ኤ.አ ተወለዱ፡፡ ዕድሜዋ ዘጠኝ ዓመት ሲሆን ግድ የለሽዋ የክፍል ባልንጀራዋ ደንጊያ ስለ ወረወረችባት ኤሌን ከአደጋ ላይ ወደቀች፡፡ በጣም የተጐዳው ፊቷ ሕይወቷን ሙሉ ከጉዳት ላይ ጣላት ትምህርቷንም ለመቀጠል እንዳትችል አድርጎ በድክመት ሁናቴ ላይ ጣላት፡፡CCh 12.1

    እድሜዋ አሥራ አንድ ዓመት ሲሆን ልብዋን ለእግዚአብሔር ሰጠች፤ ከዚያም በኋላ ጥቂት ጊዜ ቆይታ እባሕር ውስጥ በመጥለቅ ተጠመቀች ፤ የሜቶዲስት ቤተ ክርስቲያን አባል ሆና ተቀበሏት፡፡ ከሌሎችም የቤተሰብዋ አባሎች ጋር በፖርትላንድ ሜይን ወዳለው የአድቬንቲስት ስብሰባ ሔዳ የክርስቶስ ዳግመኛ ምጽዓት ቅርብ እንደሆነ በዊሊያም ሚለርና በጓደኞቹ የተነገረውንም ሐሳብ በሙሉ ተቀበለች፤ ለመድኃኒታችንም መመለስ በእምነት ለመጠባበቅ ጀመረች፡፡CCh 12.2

    አንድ ጊዜ እጧት በታህሣስ ወር ፲፷፻፵፬ ዓ.ም እ.ኤ.አ ከአራት ሌሎች ሴቶች ጋር ስትጸልይ ሳለች፤ የእግዚአብሔር ኃይል በርሷ ላይ አረፈ፡፡ በመጀመሪያ የምድራዊ ነገሮች ከአእምሮዋ ጠፉ ከዚያ በኋላ በምሳሌያዊ ገለጻ (ራእይ) የአድቬንት ሕዝብ ወደ እግዚአብሔር ከተማ የሚጓዙትን ጉዞዎችና ታማኞች የሆኑት የሚያገኙትን ዋጋ አየች፡፡ ይህች ያስራ ሰባት ዓመት ልጃገረድ ይህነንና ያየችውን ተከታዮቹን ራእዮች በፓርትላንድ ላሉት ጓድ ምዕመናን በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ ነገረቻቸው፡፡ ከዚያ በኋላ ምቹ ጊዜ እንዳገኘች ራእዩን በሜይንና በአቅራቢያ ባሉት እስቴትስ ላሉት የአድቬንቲስት ሰዎች እንደገና ነገረቻቸው፡፡CCh 12.3

    በነሐሴ ፲፷፻፵፮ ዓ.ም እ.ኤ.አ ኤለን ጂ ሐርሞን ካንድ የአድቬንቲስት ሰባኪ (ሚኒስተር) ከጀምስ ኋይት ጋር በጋብቻ ተባበረች፡፡ በተከታዮቹ ሰላሳ አምስት ዓመታት ከባልዋ ጋር በትጋት የወንጌልን ሥራ በመስራት ነሐሴ ፮ ቀን ፲፷፻፹፩ ዓ.ም እ.ኤ.አ በሞት እስኪለያት የሚስስ ኋይት ሕይወት ከርሱ ጋር በጥብቅ የተቆራኘ ሆነ፡፡ እየሰበኩና እየጻፉ በመትከል፤ በመገንባት፤ እያደራጁና እያስተዳደሩ በዩናይትድ እስቴትስ ውስጥ ብዙ ተጓዙ፡፡CCh 12.4

    ኤልደርና ሚስስ ኋይት፤ ጓደኞቹም የመሠረቱት መሠረት እንደምን የሰፋና የጸና እንደሆነና እንደምንስ በብልሃትና ደህና አድርገው እንደገነቡ ጊዜና ፈተና አስረድቷል፡፡ የማተሚያ ቤትን ሥራ በ፲፰፻፵፱ እና በ፲፰፻፶ ዓ.ም እ.ኤ.አ በመመረቅና ካምሳ ዓመት ወዲህ ሲካሔድበት የቆየውን ለቤተ ክርስቲያን ገንዘብ የማፍራት ሲስተም (ደንብ) ከማውጣት ጭምር የቤተ ክርስቲያንን ድርጅት ለማሳደግ ሰንበትን በሚጠብቁ አድቬንቲስቶች መኻኸል መሩ፡፡ ይህም የሰባተኛዋ ቀን አድቬንቲስቶች ጀኔራል ኮንፈረንስ ድርጅትን በ፲፰፻፷፫ ዓ.ም እ.ኤ.አ በማቋቋም ከፍ ወዳለው ደረጃ ደረሰ፡፡ መኻከለኛው ፷ው ዓመታት የሕክምና ሥራችን የተጀመረበትን የሚያመለክት ነው፤ ታላቁም የቤተ ክርስቲያኑ የትምህርት (የኤዱኬሺን) ሥራችን ቀደም ብሎ የተጀመረው ሰብዓኛው ዓመቱ ነው፡፡ በያመቱ የሚካሔደውም የሠፈር የጸሎት ስብሰባ ፕላን የታቀደው እ.ኤ.አ በ፲፰፻፷፰ ዓ.ም ነው፤ በ፲፰፻፸፬ም ዓ.ም ሰባተኛዋ ቀን አድቬንቲስቶች የመጀመሪያ ወንጌላዊያቸውን ላኩ፡፡CCh 12.5

    እነዚህ ሁሉ እድገቶች የተመሩት እግዚአብሔር በሚስስ ኢ ጂ ኋይት አማካይነት ለሕዝቡ በሰጠው ብዙ የቃልና የጽሁፍ ምክሮች ነው፡፡CCh 13.1

    አብዛኞቹ የቀድሞቹ ጽሑፎች የግል ደብዳቤዎች ሆነው በተጻፈው ፎርም (መልክ) ነው፤ ወይም ያሁኑ እውነት ተብለው በተጻፉት አርቲክልስ የመጀመሪያው ደንበኛው እትማችን ወጣ፡፡ ሚስስ ኋይት ፷፬ ገጾች ያሉትን የመጀመሪያ መጽሐፍዋን ኤ ስኬች ኦፍ ዘ ክርስቲያን ኤክስፒሪያንስ አንድ ቪውስ ኦፍ ኤሌን ጂ ኋይት (የክርስቲያናዊ ሁኔታ ዓላማና የዔሌን ጂ ኋይት አስተያየቶች (ሐሳቦች)) ተብሎ የተሰየመውን በ፲፰፻፶፩ ዓ.ም እ.ኤ.አ እስክታወጣ ድረስ አልነበረም፡፡CCh 13.2

    እ.ኤ.አ ከ፲፰፻፶፭ ዓ.ም ጀምሮ፤ ብዙዎች ትናንሽ ጽሑፎች ታተሙ እያንዳንዳቸውም የቤተ ክርስቲያን ምስክር የተባለውን አርዕስት የያዙ ናቸው፡፡ እነዚህም የምክርና የግሣጼ መልእክቶች ሆነው ጠቀሙ፤ ይኸውም እግዚአብሔር ከጊዜ ወደ ጊዜ ሕዝቡን ለመባረክ ለመገሠጽና ለመምራት ይልካቸው ዘንድ መረጠ፡፡ ለዚሁ ምክር እየቀጠሉ የጠየቁትን ጥያቄ ለማደላደል በ፲፰፻፹፭ ዓ.ም እ.ኤ.አ በአራት የተጠረዙ መጻሕፍት እንደገና ታትመው ወጡ፤ ከ፲፰፻፹፱--፲፱፻፱ ዓ.ም እ.ኤ.አ ከወጡት ሌሎች ቮሊዩምስ ጭምር ለቤተ ክርስቲያን ዘጠኝ የተሟሉ የምሥክሮች ቮሊዩምስ ሆነው ወጡ፡፡CCh 13.3

    ለሚስተርና ሚስስ ኋይት አራት ልጆች ተወለዱላቸው ታላቁ ልጅ ሔንሪ አሥራ ስድስት ዓመት እስኪሆነው ኖረ፤ ታናሹ ልጅ ሔርበርት በሦስት ወር እድሜው ሞተ፡፡ ሁለቱ መኻል ያሉ ልጆች ኤድስንና ዊልያም የአካለ መጠን እድሜ አግኝተው ኖሩ፤ እያንዳንዳቸውም የሰባተኛዋ ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያንን ሥራ በትጋት ሲሠሩ ቆይተዋል፡፡CCh 13.4

    ጀኔራል ኮንፈረንስ የጠየቃትን ልመና ተቀብላ ሚስስ ኋይት በበጋ ጊዜ በ ፲፰፻፹፭ ዓ.ም እ.ኤ.አ ወደ አውሮፓ ሔደች፡፡ እዚያ በክፍለ አገሩ ላዲሱ የተጀመረው ሥራ እያበረታታች ሁለት ዓመታት ቆየች፡፡ እቤትዋን በስዊትዘርላንድ በባሰል አድርጋ፤ በደቡባዊ፣ መኻከለኛውና ሰሜናዊ አውሮፓ ውስጥ ተጓዘች፤ የቤተ ክርስቲያንን ጠቅላላ ስብሰባዎች እየገባች ምዕመናንም በሚሰበሰቡበት ትገናኛቸው ነበር፡፡CCh 13.5

    ከአራት ዓመታት በኋላ ፤ ወደ ዩናይትድስቴትስ ተመልሳ ሚስስ ኋይት በ፰፫ ዓመት እድሜዋ የጀኔራለ ኮንፈረንስ ጥሪ ተቀብላ ወደ አውስትራልያ ተጓዘች፡፡ እዚያም ዘጠኝ ዓመት ቆይታ ሥራዋን በመጀመርና በማደርጀት ረዳች፤ በተለይም በትምህርትና (በኤዱኬሽናልና) በሕክምና መሥመሮች ነው፡፡ ሚስስ ኋይት እቤትዋን በምዕራባዊ የዩናይትድስቴስትስ ክፍል በሰይንት ሔሌና ካሊፎርኒያ ታደርግ ዘንድ እ.ኤ.አ በ፲፱፻ ዓ.ም ተመለሰች፤ እዚያም በ፲፱፻፲፭ ዓ.ም እስክትሞት ኖረች፡፡CCh 13.6

    ሚስስ ኋይት በአሜሪካ ስልሣ ዓመት በባሕር ማዶም አሥር ዓመት ባገለገለችበት ረዥም የአገለግሎት ዘመናት ፪ሺህ ራእዮች ያህል ተሰጥተዋታል (ታይተዋታል)፤ ይኸውም ሳትሰለች ባደረገችው ጥረት ሰዎችን ቤተ ክርስቲያናትንም ሕዝባዊ ስብሰባዎችንና የጀኔራል ኮንፈረንስን ስብሰባዎች እየመከረች፤ የዚህን ታላቅ እንቅስቃሴ እድገት በሰፊው አደረጀች፡፡ እግዚአብሔር የሰጣትን መልእክቶች ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ የማቅረብ ተግባርዋን ከቶ አላስቀረችም፡፡CCh 14.1

    ጽሑፎችዋ ካንድ መቶ ሺህ ገጾች በላይ የሆኑ ናቸው፡፡ የጻፈቻቸው መልእክቶች ለሰዎች ይደርስ የነበረው በግላዊ ጽሑፎች አማካይነት ነው፤ ሳምንት በሳምንት በቤተ ክርስቲያናችን በሚወጡት ጋዜጣዎችና በጻፈቻቸው ብዙዎች መጻሕፍት ውስጥ የተጻፉ አርቲክልስ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ የተወሱት አርዕስቶች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ስለ የዕለት ክርስቲያናዊ ሁኔታ፤ ስለ ጤና፤ ስለ ትምህርት፤ ስለ ወንጌላዊ ሥራ ስለ ሌሎችም ጠቃሚዎች አርዕስቶች የሚናገሩ ናቸው፡፡ ብዙዎች አርባ ስድስቱ መጽሐፎችዋ በዋና ዋናዎቹ የዓለም ቋንቋዎች ታትመዋል፤ በብዙ ሚልዮንም የሚቆጠሩ ግልባጮች (ኮፒ) ተሸጠዋል፡፡CCh 14.2

    በ፹፩ ዓመቷ ሚስስ ኋይት እ.ኤ.አ በ፲፱፻፱ ዓ.ም የተደረገውን የጀኔራል ኮንፈረንስ ስብሰባ ለመግባት ለመጨረሻ ጊዜ በክፍለ አገሯ ተጓዘች፤ በሕይወቷ የቀሩትን ፮ ዓመታት የጽሕፈት ሥራዋን በማከናወን አሳለፈች፡፡ በሕይወቷ መጨረሻ አቅራቢያ ላይ ሚስስ ኋይት እነዚህን ቃላት ጻፈች «በሕይወቴ ብቆይም ባልቆይም ጽሑፎቼ ዘወትር ይናገራሉ፤ ጊዜው እስካለ ድረስ ሥራቸውም ወደፊት ይቀጥላል” ፡፡CCh 14.3

    በታላቅ ድፍረትና በአዳኝዋ ምሉ እምነት አድርጋ በቤቷ እ.ኤ.አ ሐምሌ ፲፮ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓ.ም ሞተች፤ በበትል ክሪክ ሚችጋን ባለው በኦክሂል መቃብር በባልዋና በልጆችዋ አጠገብ አረፈች፡፡CCh 14.4

    በጓድ ሠራተኞችዋ፤ በቤተ ክርስቲያንና በቤተሰብዋ አባሎች ዘንድ ሚስስ ኋይት የተቀደሰች (መንፈሳዊ) እናት ትጉ፤ ለጋሥ፤ የማትሰለች ሃይማኖታዊ ሠራተኛ ሆና የታወቀችና የተከበረች ናት፡፡ እርሷ በኦፍሲያል የቤተ ክርስቲያን ቢሮ ሥራ ከቶ አልያዘችም፡፡ በቤተ ክርስቲያንና በራሷ ዘንድ ለሕዝቡ ከእግዚአብሔር መልእክት ያላት፤ «መልእክተኛ” ሆና የታወቀች ናት፡፡ ሌሎች ወደርሷ እንዲመለከቱ ከቶ አልጠየቀችም፤ ራሷንም በገንዘብ ለመደገፍ ወይም ለመወደድ ሥጦታዋንም አልተጠቀመችም፡፡ ሕይወቷንና የነበራትን ሁሉ ለእግዚአብሔር ጉዳይ ቀድሳ የሰጠች ናት፡፡CCh 14.5

    ስትሞት ፤ የታወቀው የሳምንት ጋዜጣ ጸሐፊ እ.ኤ.አ ነሐሴ ፳፫ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓ.ም በወጣው ዘ እንድፔንደንት በተባለው ጋዜጣ እነዚህን ቃላት በመናገር ስለ ፍሬያማው ሕይወቷ ሐተታዎቹን ዘጋ፤ «እርሷ ራእዮች ማየትዋን በምታምነው እምነት በፍጹም የታመነች ናት፡፡ ለሕይወቷ የተገቡ ናቸው፡፡ እርሷ መንፈሳዊ እብሪት አላሳየችም፤ ከንቱ ጥቅም የፈለገች አይደለችም፡፡ ተገቢ የሆነው የነቢይነትዋን ሕይወት ኖረች፤ ሥራም ሠራች»፡፡CCh 14.6

    ከመሞትዋ በፊት ጥቂት ዓመታት ቀደም ብሎ ሚስስ ኋይት ከቤተ ክርስቲያን መሪዎች ሰዎች የትራስቲስ ቦርድ አቋቋመች፤ ጽሑፎችዋንም እንዲጠነቀ ቁላቸውና ዘወትርም ታትመው እንዲወጡ ኃላፊዎች ይሆኑ ዘንድ ለነዚህ አደራ ሰጠቻቸው፡፡ በዋሽንግቶን ዲ.ሲ ዩ.ኤስ.ኤ ካለው የሰባተኛዋ ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን ዋናው የዓለም መሥሪያ ቤት ከሆነው ከጀኔራል ኮንፈረንስ ጽ/ቤቶች ጋር ይህ ቦርድ ዘወትር የሚወጡትን የኢ ጂ ኋይት መጻሕፍት በእንግሊዝኛ ታትመው እንዲወጡ እያጠናቀቀ፤ በምሉ ወይም በከፊልም ቢሆን በሌሎች ቋንቋዎችም ታትመው እንዲወጡ ያደፋፍራል፡፡ በየጊዜው የሚወጡትን የአርቲክልስ ጽሑፎችና ረቂቆችን በማጣመር አያሌዎችን ጽሑፎች ደግሞ አውጥቶአል፤ ይኸውም ከሚስስ ኋይት ምክር ተስማምቶ ነው፡፡ ይህም ቮሊዩም የወጣው በዚሁ ቦርድ ፈቃድ ነው፡፡CCh 14.7