Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ዛሬ በድፍረት ኑር፡፡

    በልብ ውስጥ የተቀበልኸው እውነት ለደህነነት ጠቢብ ሊያደርግህ ይችላል፡፡ እሱን በማመንና በመታዘዝ ለዛሬ ተግባሮችና ፈተናዎች በቂ የሚሆን ጸጋ ታገኛለህ፡፡ ለነጌ የሚሆን ጸጋ አያስፈልገህም፡፡ ለዛሬ ብቻ የሚሆን እንዳለህ ሊሰማህ ይገባል፡፡ ለዛሬ አሸንፍ፤ ለዛሬ ራስን ካድ ለዛሬ ትጋ ጸልይም፤ ለዛሬ በአምላክ ድልን አግኝ፡፡ ሁኔታችንና አካባቢያችን ፤ የሚሆኑት ዕለታዊ ለውጦች ሁሉን ነገሮች የሚያመለክትና የሚያስረዳው (የሚፈትነው) የተጻፈው ያምላክ ቃል እነዚህ ተግባራችንና ዕለት ዕለት ምን ማድረግ እንደሚገባን ያስተምሩን ዘንድ በቂ ናቸው፡፡ ምንም ጥቅም ከማታገኝበት የሐሳብ ጐዳና ውስጥ አእምሮህ እንዲዳክር በመፍቀድ ፈንታ ዕለት ዕለት ቅዱሣት መጻሕፍትን መመርመርና አሁን በዕለታዊ ሕይወትህ ላንተ አስቸጋሪዎች የሆኑትን ፤ ግን በአንዱ ሊደረጉ የተገቡትን ተግባሮች ማድረግ አለብህ፡፡ ፭53T333;CCh 139.3

    ብዙዎች በአካባቢያቸው በሚሆነው በሚያስፈራ ዓመፃ ላይ በየሥፍራው ባለው ክህደትና ድካምነት ላይ አይኖቻቸውን አተኩረው ይመለከታሉ፤ ልባቸው በሀዘንና በጥርጣሬ እስኪሞላ ድረስ ስለነዚሁ ነገሮች ይነጋገራሉ፡፡ የሰማያዊ አብን ኃይልና አቻ የሌለውን ፍቅሩን ችላ የሚሉ (የማያዩ) ሲመስል ፤ የሚያይለውን የአታላዩን ሥራ በሐሳብ ፊት የላቁ አድርገው ያቀርቡና ተስፋ በሚያስቆርጥ የሁኔታቸው አስተያየት ላይ ይዋዥቃሉ፡፡ ይህ ሁሉ ሰይጣን እንደሚፈልገው ነው፡፡ በአምላክ ፍቅርና በኃይሉ ላይ እንዲህ አድርገን በትንሹ ስንኖርበት ፤ የጸድቅ ጠላት እንዲህ ያለ ትልቅ ኃይል መጐናጸፉን ማሰብ ስህተት ነው፡፡ ስለ ክርስቶስ ኃያልነት መነጋገር ይገባናል፡፡ ከሰይጣን ጭብጥ ራሳችንን ለማዳን በፍጹም አቅመቢሶች ነን፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የማምለጫ መንገድ አድርጎልናል፡፡ የልዑሉ አምላክ ልጅ ጦርነቱን ለኛ ይዋጋልን ዘንድ ኃይል አለው፤ «በወደደንም” «ከአሸናፊዎች በላይ” እንሆናለን፡፡CCh 139.4

    በድክመታችንና በማፈግፈጋችን ላይ ዘወትር እየዋዠቅንና ስለ ሰይጣንም ኃይል እያቃሰትን (እየተከዝንበት) መንፈሳዊ ኃይል የለንም፡፡ ይህ ታላቅ እውነት ማለት የቀረበልንን ታላቅ መሥዋዕት ችሎታ (ብቁነት) በቃሉ ውስጥ ከተወሱት ሁኔታዎች ጋር በመስማማት ወደርሲ የሚመጡትን ሁሉ እግዚአብሔር ያድናቸው ዘንድ እንደሚችልና በእርግጥም እንደማያድናቸው በልባችን ውስጥ ሕያው ፐሪንሲፐል ሁኖ ሉመሠረት አለበት፡፡ ሥራችንን ፈቃዳችንን በአምላክ ፈቃድ ጐን ማድረግ ነው፡፡ በዚያን ጊዜ በስርየቱ ደም የመለኮታዊ ባሕርይ ተካፋዮች እንሆናለን፤ በክርስቶስም አማካይነት የምላክ ልጆች ነን እግዚአብሔርም ልጁን እንደወደደ እንደሚወደን ማረጋገጫ አለን፡፡ ከየሱስ ጋር አንድ ነን ክርስቶስ ማመራንበት መንገድ እንሔዳለን፤ ሰይጣንም በመነገዳችን ላይ የሚጥለውን ጨለማዋቹን ጽላዎች ለማስወገድ ኃይል አለው፤ በለማና ተስፋ በመቁረጥ (በመስፈራራት) ፈንታም የክብሩ የጸሐይ ብርሃን በልባችን ውስጥ ይበራል፡፡CCh 139.5

    ወንድሞቼን እህቶቼ የምንለወጠው በመመልከት ነው፡፡ በአምላክና በመድኅኒታችን ፍቅር በመኖር፤ የመለኮታዊንም ባሕርይ ፍጹምነት በማሰብና የክርስቶስ ጽድቅ የኛ መሆኑን በኃይማኖት በመለመን፤ በርሱ ምሳሌነት መለወጥ ይኖርብናል፡፡ እንግዲህ ዓመፃዎችን እርኩሰትንና ተስፋ መቁረጥን፤ የሰይጣንንም ኃይል መረጃዎች የሆኑትን በአእምሮዎችን አዳራሾች ውስጥ እይሰቀልን ነፍሳችን ተስፋ በመቁረጥ (በማስፈራራት) እስኪሞላ ድረስ ስለዚሁ እየተነጋገርንበትና እየለቀስንበት ደስ የማያሰኙትን ምስሎች ሁሉ ባንድነት አናጠራቅማቸው፡፡ ተስፋ የቆረጠው (የተስፈራራው) ነፍስ የጨለማ አካል ነው፤ የምላክን ብርሃን መቀበልን ራሱን የማያሳጣ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም እንደይቀበሉ ይዘጋባቸዋል፡፡ ሰይጣን ሰብዓዊ ፍጥረቶችን ሃይማኖተቢስና የተስፈራሩ እያደረጋቸው፤ የድል ነሰነቱን እስሎች ውጤት ለማየት ይወዳል፡፡CCh 140.1