Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ሥነ - ትምህርት

 - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  ምዕራፍ 22—በአመጋገብ ራስን መቆጣጠርናሥ ርዓተ ምግብ

  እያንዳንዱ ተማሪ በቀላል የአኗኗር ዘዴና በመጠቀ አስተሳሰብ መካከል ያለውን ግንኙነት ማስተዋል አለበት፡፡ ሕይወታችን በአእምሮአችን ወይም በአካላችን ቁጥጥር ሥር መዋል እንዳለበት የምንወስነው እያንዳንዳችን ራሳችን ነን፡፡ ወጣቱ በየግሉ የራሱን ሕይወት የሚቀርጽለትን ምርጫ ራሱ መወሰን አለበት፡፡ ከምን ዓይነት ኃይሎችና ሁኔታዎች ጋር እንደሚታገልና ባህሪይንና የመጨረሻ ግብርን ለመወሰን ከሚጐትቱ ስበቶች አንዳችም ዓይነት ጉሸማ እንዳይኖርበት ማስተዋል አለበት፡፡ EDA 224.1

  ራስን በምግብ ለመቆጣጠር አለመቻል በደህና ሁኔታ መጠበቅ ለሚያስፈልገው ነገር ሁሉ አደጋ ነው፡፡ የዚህ አስከፊ ጥፋት በፍጥነት እየጨመረ መሄድ ዘሩን የሚያፈቅር ሰው ሁሉ ሊዋጋው ይገባል፡፡ በትምህርት ቤት ውስጥ በአመጋገብ ራስን የመቆጣጠር ትምህርት ርዕሶች የመሰጠቱ ተግባር ትክክለኛውን መስመር የመያዝ ጥሩ ጅምር ነው፡፡ በዚህ መስመር የሚሰጠው ትምህርት በየትምህርት ቤቱና የአልኮልን የትምባሆንና ሌሎች ተመሳሳይ መርዛማ ነገሮች ሰውነትን በመሰባበር፤ አእምሮን በጭጋግ በመሸፈንና ነፍስንም ስሜታዊ በማድረግ በኩል የሚኖረውን ጐጂ ውጤት ማስተዋል አለባቸው፡፡ እነኝህን ነገሮች የሚጠቀም ማንኛውም ሰው ሁሉ በአካላዊ በሕሊናውና በሞራሉ ልዩ ችሎታዎች ሙሉ ብርታት ሊኖረው እንደማይችል ግልጽ መሆን አለበት፡፡ EDA 224.2

  ራስን በምግብና በመጠጥ ወደ አለመቆጣጠር ሥር ውስጥ ጠልቀን ለመድረስ ከአልኮልና ከትንባሆ አጠቃቀም አልፈን መሄድ ይኖርብናል፡፡ ቦዘኔነት ዓላማ የለሽ መሆን ወይም በጥፋት ማህበር ውስጥ መግባት ለተጠቀሱት አደጋዎች ከመጋለጥ በፊት የሚኖሩ ምክንያቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ራሳቸውን በሚገባ በሚቆጣጠሩ ቤተሰቦችም እንዲህ አይነት ችግር ዘወትር ሊያጋጥም ይችላል፡፡ ማናቸውም የምግብ መፈጨትን የሚያውክ አለአግባብ አእምሮን የሚያስፈነድቅ፣ ወይም በማናቸውም መንገድ ሥርዓቱን አሚያዳክም፣ የሕሊናና የአካልን ሚዛን የሚረብሽ ነገር ሁሉ አእምሮ በአካል ላይ ሊኖረው የሚችለውን ቁጥጥር ያዳክማል፡፡ ስለሆነም የራስን መሻት ወደ አለመቆጣጠር ያዘንብላል፡፡ ብዙ ተስፋ የተጣለባቸው ወጣቶች ውድቀት ታሪካቸው ሲጠና ተፈጥሮአዊ ያልሆነ የምግብ ፍላጐት በተዛባ የምግብ ሥርዓት ምክንያት እንደመጣባቸው ታውቋል፡፡EDA 225.1

  ሻይ፣ ቡና፣ መልክና ሽታ ሰጭ ቅመማቅመሞች፣ ኬክና ልዩ ልዩ ጣፋጭ ፖስተሪ እነኝህ ሁሉ የምግብ አለመፈጨትን ችግር የሚያስከትሉ መነሻዎች ናቸው፡፡ የሥጋ ምግብም ደግሞ ጐጂ ነው፡፡ በተፈጥሮ አነቃቂነቱ ምክንያት የሚያስከትለው ውጤቱን ከጥቅሙ ጋር ማነፃፀር ለክርክር ብቁ መነሻ ነው፡፡ በአጠቃላይ በእንስሳት ላይ የሚኖረው ልዩ ልዩ በበሽታ የመበከል ዓለምአቀፋዊ ሁኔታ አንፃር ሲታይ ተቀባይነት ማጣቱን በእጥፍ ከፍ ያደርገዋል፡፡ ነርቮችን የሚቆጠቁጥ ፍላጐትን የሚያስቆጣ ወደ መሆን ያዘነብላል፡፡ ስለዚህም የኃይል ሚዛንን ዝቅ ያደርጋል፡፡EDA 225.2

  አነቃቂ የሆነ ምግብ በብዛት መውሰድ ልማድ የሆነባቸው ሰዎች ከጊዜ በኋላ ሆዳቸው ቀለል ባለ የምግብ ዓይነት አልሞላ እያለ ይቸገራሉ፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜም የበለጠ ትኩስ ኃይል ያለው እና በከፍተኛ ደረጃ ይበልጥ አነቃቂ የሆነውን ይፈልጋል፡፡ ነርቦች ሥርዓት የለሽ እየሆኑና ሥርዓቱም እየተዳከመ ሲሄድ ተፈጥሮአዊ ያልሆነውን ፍላጐት ለመቋቋም ልባችን ኃይል ያንሰዋል፡፡ እጅግ ስስ የሆነው የጨጓራችን ሽፋን የመጨረሻ ከፍተኛ የማነቃቃት ኃይል ያለው ምግብ ረፍት ወይም እርካታ ሊያስገኝ የማይችልበት ደረጃ ላይ እስከሚደርስ ድረስ ይቆጣና ይቀላል ወይም ይቆስላል፡፡ ካለ ጠንካራ አልካል በስተቀር ሌላ ምንም ሊያረካው የማይችል ጥማት ይፈጥራል፡፡EDA 225.3

  ክፉ ነገሮችን መከላከል የሚገባን ከመጀመሪያ መነሻቸው ነው፡፡ ወጣቶችን በምናስተምርበት ጊዜ ከትክክለኛው መንገድ ትንሽም እንኳ ዘንበል ማለት የሚያስከትለውን ጉዳት ግልጽ ሊደረግላቸው ይገባል፡፡ ተማሪው የቀላል አመጋገብና ጤናማ የሆኑ የምግብ ዓይነቶች ተፈጥሮአዊ ያልሆኑ አነቃቂ ነገሮችን በመከላከል ረገድ የሚኖራቸውን ጠቀሜታ ሊማር ይገባዋል፡፡ ወጣቱ ባሪያ በሚያደርጋቸው ሳይሆን የራሳቸውን ጌታ በሚያደርጋቸው ሐሳብ እንዲቀረፁ ይደረግ፡፡ በውስጣቸው ባለው ግዛት ላይ እግዚአብሔር ገዢ አድርጓቸዋል፡፡ ስለዚህ በሰማይ አምላክ የተሾሙበትን የንጉሥነት ተግባር መፈፀም አለባቸው፡፡ እንዲህ ዓይነት ትምህርት በፍፁም ታማኝነት በሚሰጥበት ጊዜ ውጤቱ ከወጣቶቹ ከራሳቸው አልፎ ሲስፋፋ ይታያል፡፡ የእነርሱ ስበት በሽህ የሚቆጠሩ ወንዶችና ሴቶችን ከጥፋት አፋፍ ያድናል፡፡EDA 226.1

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents