Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
ሥነ - ትምህርት - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  ምግብና የሕሊና ዕድገት

  ምግብ ከአአምሮአዊ ዕድገት ጋር ያለው ግንኙነት እስከ ዛሬ ከተሰጠው የበለጠ ትኩረት ሊያገኝ ይገባዋል፡፡ የሕሊና መቃወስና መደንዘዝ ዘወትር ካመጋገብ ስህተት የሚመጣ ውጤት ነው፡፡EDA 226.2

  በምግብ ዓይነቶች አመራረጥ ላይ የምግብ ፍላጐት የሚገኝበትን ደረጃ ማየት የተሻለ ምልክት እንደሆነ በተደጋጋሚ ተነግሯል፡፡ ሁልጊዜ የጤና ሕጐችን በሚገባ ስንታዘዝ ይህ ነገር እውነት መሆኑን እንረዳለን፡፡ ነገር ግን በመጥፎ ልማዶች ምክንያት ከትውልድ ትውልድ በማከታተል የምግብ ፍላጐት በተሳሳተ አጠቃቀም ጐጂ ወደሆነ እርካታ እየተለወጠ መጥቷል፡፡ ስለዚህ እንደ አንድ ዋና መሪ ምልክት ሊሆን አይችልም፡፡EDA 227.1

  አጠቃላይ በሆነ የንጽህና ትምህርት ውስጥ ተማሪዎች የብዙ የልዩ ልዩ ዓይነት ምግቦችን ጠቀሜታ መማር አለባቸው፡፡ የተከማቸና አነቃቂ የሆነ ምግብ አልሚ ንጥረ ነገሮች የጐደለው ምግብ በሚያስከትለው ጉዳት ግልጽ ሊደረግላቸው ይገባለ፡፡ ሻይ ቡና የፊኖ ዱቆት ዳቦ፣ እንዳይበላሽ ተብሎ በጨው ውሃ የተነከረ ወይም ታሽቶ የተቀመጠ ምግብ አሻራ ጥሬ ቅጠላ ቅጠሎች ከረሜላዎች ጣዕምና ቃና (ሽታ) የሚሰጡ ቅመማ ቅመሞችና ልዩ ልዩ ጣፋጭ ኬኮች የተስተካከሉ ምጥን ምግቦች አይደሉም፡፡ አንዳንድ ተማሪዎች እንዲህ ዓይነት ምግቦችን በመጠቀም ተሰባብረው ወድቀዋል፡፡ አንዳንድ ደካማ ሕፃናት ኃይለኛ የአእምሮ ወይም የአካል ሥራ መሥራት አይችሉም፡፡ ምክንያቱም የተመጣጠነ ምግብ ካለማግኘት የተነሳ ነው፡፡ ጥራጥሬዎች ፍራፍሬዎች ቆሎ እና የጓሮ አትክልት በተገቢ ሁኔታ ከተወሰዱና በአግባቡ ከተዘጋጁ ትክክለኛውን ገንቢ ንጥረ ቅመሞች ስለሚይዙ ለአካልና ለአእምሮ ብርታት መዳበር እጅግ ጠቃሚ ናቸው፡፡EDA 227.2

  የምግቡን ባሕሪይ ብቻ ሣይሆን በተመጋቢው ላይ ሊፈጥር የሚችለው ሱስ መመዛዘን አለበት፡፡ በጉልበት ሥራ ላይ በተሠማሩ ሰዎች ዘንድ ዘወትር ያለ አንዳች ችግር ነፃ በሆነ መንገድ የሚወሰዱ የምግብ ዓይነቶች የአእምሮ ሥራ ብቻ በሚሰሩ ሰዎች ዘንድ መወሰድ የለበትም፡፡ በርካታ የምግብ ዓይነቶች ተቀላቅለው በአንድ ላይ በሚወስዱበት ጊዜም ተገቢው ቅንጅታቸው በትክክለኛ መጠናቸው ስለመጠበቁ አትኩሮች ሊሰጠው ይገባል፡፡ በአእምሮ ሠራተኞችና በሌሎችም ብዙ ጊዜ ሥራቸውን ቁጭ ብለው (በመቀመጥ) በሚያከናውኑ ሰዎች ዘንድ ከእነዚህ ዓይነቶች ምግቦች ጥቂት ብቻ መወሰድ አለበት፡፡EDA 227.3

  ጥሩ ምግብም እንኳን ቢሆን ባንድ ጊዜ ከመጠን በላይ መብላት ተገቢ አይደለም፡፡ ተፈጥሮ የተለያዩ ብልቶችን ለመገንባት ከሚያስፈልገው በላይ መጠቀም አይችልም፡፡ በብዛት ሲተርፍ ደግሞ ሥርዓቱን ያስተጓጉላል፡፡ የቆሻሻ ክምችት መስመር ይዘጋል፡፡ አንዳንድ ተማሪዎች ጉዳቱን ያመጣባቸው ከመጠን በላይ መብላታቸው ሆኖ ሳለ በብዙ ጥናት ተሰባብረው እንደ ወደቁ ይነግራል፡፡ ለጤና ሕጐች ተገቢው ትኩረት በሚሰጥበት ጊዜ በአእምሮ ላይ ሊመጣ የሚችለው ሕመም በጣም ትንሽ ነው፡፡ ነገር ግን ብዙ ጊዜ የአእምሮ ችግር የሚባለው የሆድ ክፉኛ መሙላት ነው፡፡ በዚህ ሰዓት ሰውነት ይደቅቃል አእምሮም ይደክማል፡፡EDA 228.1

  አብዛኛውን ጊዜ በቀን ሦስት ጊዜ ከሚሆን ይልቅ በቀን ሁለት ጊዜ ብቻ ምግብ መውሰድ ይመረጣል፡፡ ራት ቀደም ብሎ ከተወሰደ ከበፊተኛው ምግብ ጋር ለመፍጨት ያስቸግራል፡፡ ዘግይቶ ከተወሰደ ደግሞ ከመኝታ በፊት ደቅቆ አያልቅም፡፡ ስለዚህ ሆዳችን ተገቢውን ረፍት አያገኝም፡፡ እንቅልፍ ይረበሻል፡፡ አእምሮና ነርቮች ይደክማሉ፡፡ በቁርስ ሰዓት ሊኖር የሚገባው ፍላጐት ይቀንሳል፡፡ አጠቃላይ ሥርዓቱ ያልታደሰና ለቀኑ ሥራ ያልተዘጋጀ ይሆናል፡፡EDA 228.2

  የምግብ እና የመኝታን ሰዓትን የመጠበቅ ጥቅም በቸልታ ሊታለፍ የሚገባው አይደለም፡፡ ሰውነት የሚነባው በእረፍት ሰዓት ላይ በመሆኑ፡፡ በተለይም በወጣትነት ጊዜ እንቅልፍ የሚበቃውን ያክልና መደበኛ ጊዜውን የጠበቀ መሆኑ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡EDA 228.3

  በተቻለ መጠን እየተጣደፍን በችኮላ መብላትን ማስወገድ አለብን፡፡ የምግብ ሰዓት ባነሰ መጠን የምንወስደው የምግብ መጠንም እንደዚያው በጣም ትንሽ መሆን አለበት፡፡ በአፋችን ውስጥ ተገቢውን የማድቀቅ ተግባር ሳይፈፀም ከመዋጥ ይልቅ ምግቡን አለመብላት ይሻላል፡፡EDA 229.1

  የምግብ ሰዓት ለማኅበራዊ ግንኙነታችን የመዝናኛ ወቅት ሊሆንልን ይገባል፡፡ ማንኛውም ሸክምና ጭንቀት ብስጭት የሚያመጣ ነገር ሁሉ መወገድ አለበት፡፡ በጐውን ሁሉ ለሚሰጥ አምላክ አምነትን ደግነትንና ምሥጋናን ለርሱ ማቅረብ ልማዳችሁ ይሁን ጭውውታችሁ ሁሉ ለዛ ያለው የሚያስደስትና ልብን የሚያነቃቃ ያለመታከትም የደስታ ሐሳብ እንዲጐርፍ የሚያደርግ ይሁንላችሁ፡፡EDA 229.2

  በሁሉም ነገሮች ላይ ቁጥብ ሆኖ ራሱን በመቆጣጠር ሰዓታቸውን ጠብቆ በሚገባ መከታተል አስገራሚ ኃይል አለው፡፡ የሕይወትን መንገድ ለስላሳ ለሚያደርግ ጥሩ ጣፋጭና ንጹህ ጠባይ ከሁኔታዎችና ተፈጥሮአዊ ችሎታ የበለጠ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡ በዚሁ ጊዜ ራስን የመቆጣጠር ኃይል እየተለመደ ሲሄድ ለእያንዳንዱ ሰው በሕይወቱ በሚጠብቀው ትግል ውስጥ በጥብቅ ተግባራትና ተጨባጭ ሁኔታዎች ላይ እጅግ ጠቃሚ መሣሪያ ይሆንለታል፡፡EDA 229.3

  ጥበብ «መንገዷ የደስታ መንገድ ነው ጐዳናዋም ሁሉ ሰላም ነው፡፡» ምሣ፣ 3፡17 በአገራችን ያለ ወጣት ሁሉ ዘውድ ከጫኑ ነገሥታት በላይ የበለጠ የከፍተኛ ዓላማ ባለቤት ለመሆን ካለው ዕድል ጋር በጠቢቡ ሰው በተነገሩት ቃላት ላይ አተኩሮ ይመልከት፡፡ አንች አገር ሆይ …. ለብርታት እንጅ ለስካር ያይደለ በጊዜ የሚበሉ መኳንንት ያሉሽ አንች አገር ሆይ የተመሰገንሽ ነው፡፡ መክ 10፡1EDA 229.4

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents