Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

ሥነ - ትምህርት

 - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  ምዕራፍ 8—ከእግዚአብሔር የተላከው መምህር

  «እዩትና አስተውሉ»EDA 77.1

  «ስሙም ድንቅ፤ መካር፤ ኃያል አመላክ፤ የዘለዓለም አባት፤ የሰላም አለቃ፡፡» ኢሳ9፡6EDA 77.2

  ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከው መመህር ሰማይ ሊያበረክት የሚችለው ታላቅ መምህር ለሰው ልጅ የተሰጠው እጅግ ምርጥ መምህር እርሱ ነው፡፡ በላይ በሰማያት ከፍታ ላይ ባለው ምክር ቤት ውስጥ የቆመው በዘለዓለማዊው ቤተመቅደስ ቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ የተቀመጠው ለሰብዓዊ ፍጡሮች የእግዚአብሔርን እውቀት በአካል እንዲገልጥ የተጠራው እርሱ ነበር፡፡EDA 77.3

  ከዚያ በፊት ወደዚች ወደ ወደቀች አለም መጥተው የማያውቁ እያንዳንዷ የመለኮት ብርሃን ጨረሮች በክርስቶስ አማካይነት ተገኝተዋል፡፡ በዘመናት ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ለሰው ልጅ ሲያስተምሩ በነበሩ ሰዎች ውስጥ ይናገር የነበረው እርሱ ነው፡፡ በዓለም ታላላቅና ድንቅ ሰዎች አንደበት ስለእርሱ የተነገሩ ክቢርና ድንቅ ቁም ነገሮች ሁሉ የእርሱ ነፀብራቅ ነበሩ፡፡ የዮሴፍ ንጽህናና ደግነት የሙሴ እምነትና ታላቅ ታጋሽነት የኤልሳዕ ጽናት የተከበረና የተረጋጋ የዳንኤል ጥብቅነት ነቁ ቀልጣፋ የነበረውና ራሱን መስዋዕት ያደረገው ጳውሎስ በእነዚህ ሰዎች ሁሉ አማካይነት የተገለጠ የሕሊናና መንፈሳዊ ኃይል በሌሎችም በምድር ላይ በነበሩ ሰዎች ሁሉ ከሚያበራው ከእርሱ የክብር ብርሃን የተገኙ ፍንጣቂዎች ብቻ ናቸው፡፡ ፍጹምና ድንቅ የሆነው ሐሳብ ከእርሱ የሚገኝ ነው፡፡EDA 77.4

  ይኸንን ከፍተኛ ድንቅ ኃሳብ እንደብቸኛ የእውነት አፈፃፀም መለኪያ አድርጐ ለመግለጥ እያንዳንዱ ሰብዓዊ ፍጡር ወደፊት ወደምንነት ሊለወጥ እንደሚችል ለማሳየት በሰብዓዊነት ውስጥ መለኮታዊነት ሲያድር እርሱን የተቀበለ ሁሉ ምን ሊመስል እንደሚችል ለማስረዳት ለዚህ ነው ክርስቶስ ወደዚች ዓለም የመጣው፡፡ ሰዎች እንዴት ሆነው ቢሰለጥኑ የእግዚአብሔር ልጅ ሊሆኑ እንደሚችሉ ለማሳየት፣ በምድር በመሠረታዊ ሀሳቦች መሠረት የሰማይን ውስጥ ኑሮ በምድር እንዲለማመዱ ለማሳየት ነው እርሱ የመጣው፡፡EDA 78.1

  የእግዚአብሔር እጅግ ታላቅ ስጦታ የሰውን ልጅ እጅግ ከፍተኛ ፍላጐት ያረካ ዘንድ ተሰጠ፡፡ በዓለም የወደቀው ጭለማ እጅግ ድቅድቅ በሆነበት ሰዓት መብራቱ መጣ፡፡ በሀሰተኛ ትምህርት የሰዎች አእምሮ ከእግዚአብሔር መንገድ ተለይቶ ከጠፋ ብዙ ጊዜ ሆኖት ነበር፡፡ በነበረው የትምህርት ሥርዓት መለኮት በሚገለጥበት ቦታ የሰው ልጅ ፍልስፍና ተተክቶ ነበር፡፡ ለእውነት መለኪያ ይሆን ዘንድ ከሰማይ በተሰጠው መስፈርት ፋንታ ሰዎች ራሳቸው ያወጡትን የማካፈል ሥርዓት ተቀበሉ፡፡ የሕይወት ብርሃን ከሆነው ሸሽተው ሥርዓት ተቀበሉ፡፡ የሕይወት ብርሃን ከሆነው ሸሽተው ራሳቸው ባነደዱት እሳት ፍንጣቂ ብልጭታ መራመድ ፈለጉ፡፡EDA 78.2

  ራሳቸውን ለሰብዓዊ ኃይል ዋና መተማመኛ ከሆነው ከእግዚአብሔር ሲለዩ ጉልበታቸው ሁሉ ደክሞ ነበር፡፡ ራሳቸው መመዘኛ ይሆናል ብለው ያስቀመጡትን መስፈርት እንኳ ሊደርሱበት ተሳናቸው፡፡ እውነተኛና ድንቅ ጥራትን የመፈለግ ስሜት በአካልና በሙያ ተሰጥቷቸው ነበር፡፡ ነገር ግን አስመሳይነት የእውነትን ቦታ ወሰደ፡፡EDA 78.3

  ሰዎች የእውነት ምንጭ የሆነውን ያዩ ዘንድ የሚያመለክቱ መምህራን ከጊዜ ወደጊዜ ይነሱ ነበር፡፡ እውነተኛ መሠረታዊ ሐሳቦች መግለጽ በሰብዓዊ ፍጡሮች ሕይወት ውስጥም ኃይላቸው ተመስክሮላቸዋል፡፡ ነገር ግን እነዚህ ለውጦች ዘላቂ ሥርፀት አላገኙም፡፡ ይህ የክፋት ጐርፍ አልፎ አልፎ ቢገታመ አወራረዱን ጨርሶ ለመገደብ ግን አልተቻለም፡፡ የተሃድሶ ለውጥ አራማጆች በጨለማ ውስጥ እንደሚገኝ ብርሃን ነበሩ እንጅ ከሥሩ ሊያስወግዱት አልቻሉም፡፡ ዓለምም ‹ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ወደደች፡፡› ዮሐ 3፡19EDA 79.1

  ክርስቶስ ወደ ምድር በመጣ ጊዜ ሰበዓዊነት በፍጥነት እያሽቆለቆለ መጨረሻ ነጥብ ላይ የደረሰ ይመስል ነበር፡፡ የሕብረተሰብ ዋና መሠረቶች ተንቀው ነበር፡፡ ሕይወት ራሷ የውሸትና ሰው ሠራሽ ትመስል ነበር፡፡ አይሁዶች የእግዚአብሔርን የቃሉን ኃይል ተራቁተው አእምሮ ለሚያደነዝዝና ነፍስን ለሚገድል ልማድና አስተሳሰብ ለወጡት፡፡ «በመንፈስና በእውነት» የሚደረገው የእግዚአብሔር አምልኮ ሰው ሰራሽ በሆኑ ራሳቸው በሚያደነቋቸው ማብቂያ የለሽ በዙር የሚከናወኑ የሰበሰባ ሥርዓቶች ተተኩ፡፡ በመላው ዓለም ላይ ሁሉም ዓይነት ሃይማኖቶች አእምሮንና ነፍስን ሊይዙ የሚችሉ አልሆኑም ፡፡ በተረትና ታማኝ ባመሆኑ ሐሳብ ደረቅ ሐሳቦችን በመውደድ ተጨባጭ ወደሆነ ቁሳቁሳዊ ሐብት ማጋበስ ዞሩ፡፡ ዘለዓለማዊኑትን ከአዕምሮአቸው አውጥተው የዞሬን ኑሮ ብቻ ያዙ፡፡EDA 79.2

  የመለኮታዊውን መንገድ ማስታወስ እንደተውት ሁሉ የሰብዓዊውንም እንደዚሁ ዘነጉት፡፡ እውነት ክብር፣ መረጋጋት ልበሙሉነትና ትህትና ከዓለም ተለይተው ሄዱ፡፡ ገደብየለሽ ስግብግበነትና የማጋበስ ምኞት ዓለም አቀፋዊ የታማኝነት ጉድለትን ወለደ፡፡ የተግባር ሐሳብ ግዳጅን የመወጣት ሐሳብ በድክመት ላይ የመጠንከር ሐሳብ የሰው ክብርና መብቶች ሐሳብ፤ እንደህልም ወይም ተረት ተቆጥረው ወደጐን ተገልለው ነበር፡፡ ተራው ሕዝብ እንደጋማ ከብት የቆጠሩ ነበር፡፡ ወይም የምኞት መወጣጫ ደረጃና መሣሪያ እንደሆነ አድርገው አሰቡ፡፡ ሐብት፣ ንበረት፣ ኃይል እና የሥነ-ምግባር ጉድለት እጅግ በጣመ ከፍተኛ ድንቅ ነገር እንደሆነ ተደርጐ ይታሰብ ነበር፡፡ በአካል መጐሳቆል አእምሮን በስካርና በሌላም ማድከምና መንፈሳዊ ሞት የዘመኑ ልዩ መታወቂያ ባህሪይ ሆነ፡፡EDA 79.3

  የሰዎች የክፋት ሐሳብና ዓላማ እግዚአብሔርን ከአዕምሮአቸው እንዲርቅ እንዳደገው ሁሉ እርሱን እየረሱ መሄዳቸውም የበለጠ ወደከፋት እንዲያዘነብሉ አደረጋቸው፡፡ ሀጢአትን ያፈቀረ ልብ ውጤቶቹ እርሱን ሸፈኑት፡፡ ይህ ሐሳብ ደግሞ የሀጢአትን ኃይል አጠናከረው፡፡ ራስን መካከል እንደ አንደኛው አድርገው አሰቡት፡፡ እንደ አንድ ፍጡር የግል ክብር የሚፈልግ ነገሮቹን ሁሉ ለእርሱ እንደሚያስደስተው ብቻ አድርጐ ያዘጋጀ ፍጡር ሰዎች እርሱ ራሱን በመውደድ መንፈስ ያዘጋጃቸውን ነገሮች በመደገፋቸው ወይም በቃወማቸው ወደላይ እንደያድጉ ወይም ወደታች እንዲጣሉ የሚያደርግ ፍጡር እንደሆነ አድርገው አሰቡት፡፡ የታችኛው መደበ አባላት ደግሞም ይኸንን የኃያላን ኃያል የሆነውን አምላክ እነሱን ከማጨቁኗቸው ገዥዎቻቸው በጥቂት ብቻ የሚለይ በኃይል ስለ ሚበልጣቸው ብቻ እንደሚያድን አድርገው ተመለከቱ፡፡ በዚያ ጊዜ የነበሩ ሃይማኖቶች ሁሉ ከእነኝህ ሀሳቦት አንፃር ተቀረፁ፡፡ ሥርዓቱ ሁሉ የቀረጥ ዓይነት ሥራ ሆነ፡፡ ይኸንን እምነት የሚከተሉ በስጦታና በደማቅ ስብሰባ የአምላክን ፈቃድና ፍላጐት ለራሳቸው ዓላማ እንዲስማማ አድርገው ለመግዛት አሰቡ፡፡ እንዲህ ዓይነት በልቦና ወይም በህሊና ላይ ኃይል የሌለው ሃይማኖት ሊሆን የሚችለው የስበሰባ ቅርጽ ብቻ ነው፡፡ በዚህም ሰዎች የሚያገኙበት ጠቀሚታ ያው ሊሰጣቸው የሚችለውንና የሚመኙትን ልቅነትን ብቻ ነው፡፡ ስለዚህም መልካሙን ነገር መውደድና ማድነቅ እየቀረ ገደብ የሌለው ክፋት እየጠነከረ መጣ፡፡ ሰዎች የእግዚአብሔርን ተምሳሌነታቸውን እያጡ በቁጥጥሩ ሥር ያዋላቸውን የባዕድ አምልካ ገዥ ኃይል ምስል ተቀበሉ፡፡ ጠቅላላዋ ዓለም የዋልጌት ቅሌት ጐሬ ሆነች፡፡EDA 80.1

  ለሰው ዘር የቀረው አንድ ተስፋ ብቻ ነበር፡፡ ይኸውም ይህ ሥርዓት ያጣ ያልተሰተካከለ ሕዝብና በወራዳ ተግባሮች የተበከሉ ፍጥረቶች ተወግደው በአዲስ እርሾ እንዲተካ የአዲስ ሕይወት ኃይልም ለሰው ልጅ ይመጣለት ዘንድ የእግዚአብሔር እውቀትም ለዓለም ይመለስላት ዘንድ ነበር የማያስፈልገው፡፡EDA 81.1

  ይኸንን እውቀት ለመመለስ ሲል ክርስሮስ መጣ፡፡ እግዚአብሔርን እናውቀዋለን የሚሉትና በተሳሳተ መንገድ እንዲወክሉት ያደረጋቸውን የውሸት ትመህርት ለማስወገድ መጣ፡፡ የሕጉን ባህሪ ለመግለጽና የቅዱስናን ድንቅነት በራሱ ባህሪ ውስጥ ለማሳየት መጣ፡፡EDA 81.2

  ክርስቶስ ካከማቸው ዘለዓለማዊ ፍቅር ጋር ወደዚህ ዓለም መጣ፡፡ ለእግዚአብሔር ሕግ እንቅፋት የሆኑትን የምልጃ ሥርዓት ጠራርጐ ሕጉ የፍቅር ሕግ እንደሆነና የመለኮታዊ ቸርነት መግለጫ እንደሆነ አሳየ፡፡ የሰው ልጅ ደስታ ለሕጉ መሠረታዊ ሀሳቦች በመታዘዝ ውስጥ ያለ መሆኑንና በዚህም ለሰው ልጅ ማህበረሰብ ዋና መሠረትና መዋቅሩ መሆኑን አሳየ11EDA 81.3

  እንግዲህ የማይረቡ ምክንያት የሌላቸው የጉልበት ህጐችን በማስቀመጥ ደግዴታ አንዲሟሉ የሚጠይቅ ሳይሆን የእግዚአብሔር ሕግ ለሰዎች እንደጋሻና መከታ መከላከያ እንዲሆናቸው የተሰጠ ነው፡፡ መሠረታዊ ሐሳቦቹን የሚቀበል ማንኛውም ሰው ከክፉ ይቆጠባል ይጠበቃልም ለእግዚአብሔር ታማኝ መሆን ለሰውም ታማኝ መሆንን ያካትታል፡ ስለዚህም ሕጉ የእያንዳንዱን ሰው መብቶችና ግላዊነት ያስከብራል፡፡ የበላዩን ጨቋኝ ከመሆን የበታችንም ከእንቢተኝነት ይገታዋል፡፡ በዚህ ዓለም ላይ እያለም ሆነ በሚመጣው ዓለም የሰውን ደህነነት ያረጋግጥለታል፡፡ ታዛዥ ለሆነው ሰው የዘለዓለም ሕይወት ዋስትና ነው፡፡EDA 81.4

  ክርስቶስ የሰው ልጅ ዘር እንደገና እንዲያለመልም ወይም እንዲያቆጠቁጥ ለማድረግ የሚያስችለውን የመለኮትን መሠረታዊ ሐሳቦችና የኃይላቸውንም ዋጋ በተግባር ለማሳየት መጣ፡፡ እነኝህ መሠረታዊ ሐሳቦች እንዴት ሊዳብሩና ሥራ ላይ ሊውሉ እንደሚችሉ ለማስተማር መጣ፡፡EDA 82.1

  በዚያ ዘመን በነበሩ ሰዎች ዘንድ የማንኛውም ነገር ዋጋ ይተመን የነበረው ከውጭ ከሚታየው መልኩ ነበር፡፡ የሃይማኖት ኃይል ቀርሶ አሸቆልቁሎ ስለነበር ያሸበረከ የስብሰባ ሥርዓት እየገነነ ሄደ ነበር፡፡ የዚያን ጊዜ የነበሩ መመህራን ትዕዛዝ በመስጠት ክብራቸው እንዲታይላቸው ሐብታቸው እንዲታወቅላቸውና እንዲከበሩ ይፈልጉ ነበር፡፡ ከዚህ ሁሉ ነገር አንፃር የየሱስ ሕይወት ፍፁም ልዩ ሆኖ ይታይ ነበር፡፡ የእርሱ ሕይወት ሰዎች በኑሮ ውስጥ እጅግ ከፍተኛ ግምት አላቸው የሚሏቸውን ነገሮች ሁሉ ዋጋቢስ መሆናቸው አስመሰከረ፡፡ ብልግና በተሞላበት አካባቢ ተወልዶ፣ ከአንድ ገበሬ ቤት ተጋርቶ የገበሬውን ምግብና ኑሮ ተካፍሎ የእጅ ጥበብ ባለሙያነትን፣ ማንነቱ በግልጽ ሊታወቅ በማይቻልበት ሁታ እየኖረ በዓለም ውስጥ ፈጽሞ ከማይታወቁ ሠራተኞች ጋር ራሱን በማጐዳኘት በእነዚህ ሁኔታዎችና አካባቢዎች መካከል የሱስ የመለኮትን የትምህርት እቅድ ተከተለ፡፡ በእርሱ ጊዜ የነበሩ ትምህርት ቤቶች ትንንሽ ነገሮችን እያጐሉ ማጋነንና ትልልቅ ነገሮችን ማቃለል ማጣጣል ሥራቸው ስለነበር አልፈለጋቸውም፡፡ የእርሱ ትምህርት የሚገኘው በቀጥታ በሰማይ ከተመረጠው ምንጭ ጠቃሚ ከሆነ ሥራ መጽሐፍትንና ተፈጥሮን ለማጥናት፣ እና የእግዚአብሔር መጽሐፍት ከሆኑት እጃቸውን ለሚዘረጉ ተመልካች ዐይንና አስተዋይ ልቦና ላላቸው ሁሉ የሚሰጥ ነው፡፡ «ሕፃኑም አደገ ጥበብም ሞልቶበት በመንፈስ ጠነከረ የእግዚአብሔርም ፀጋ በእርሱ ላይ ነበረ፡፡» ሉቃ 2፡40EDA 82.2

  እንደዚህ ሆኖ በመዘጋጀት በተልዕኮው ወደፊት ቀጠለ፡፡ ከእያንዳዱ ሰው ጋር በሚኖረው ግንኙነት በላያቸው ላይ በረከት ያወርድባቸዋል፡፡ ዓለምም ከዚህ በፊት ዐይታ የማታውቀውን የለውጥ ኃይል ያሳድርባቸው ነበር፡፡EDA 83.1

  ሰብዓዊነትን መለወጥ የሚፈልግ ሰው መጀመሪያ እሱ ራሱ ሰብዓዊነትን በሚገባ ማስተዋል አለበት፡፡ ሰዎችን መቅረብና ማነሳሳት የሚቻለው በመተባበር መነፈስ፣ በእምነት፣ እና በፍቅር ብቻ ነው፡፡ እዚህ ላይ ክርስቶስ ከዚያ በፊት በዓለም ላይ ከኖሩት በተለየና በላቀ መንገድ የሊቃውንት መምህር ሆኖ ራሱን ገለጠ፡፡ የሰውን ልጅ ነፍስ በትክክለኛው መንገድ ያስተዋለው እርሱ ብቻ ነው፡፡EDA 83.2

  «ሊቀካህናት የለንም» ታላቅ መምህር ማለት ነው ካህናት መምህራን ነበሩና፡፡ «ከሀጢአት በቀር በነገር ሁሉ እንደኛ የተፈተነ ነው እንጅ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀካህሃት የለንም፡፡» አበራ 4፡15EDA 83.3

  «እርሱ ራሱ ተፈጥሮ መከራን ስለተቀበለ የሚፈተኑትን ሊረዳቸው ይችላልና፡፡ » እብ 2፡18EDA 83.4

  በሰው ልጆች ላይ የወደቁትን መሪር ሐዘኖች እና ፈተናዎች ሁሉ የተቀበለውና የተፈተነው መምህር ክርሰቶስ ብቻ ነው፡፡ ማንም ከሰው የተወለደ ሌላ ሰው በእንዲህ ዓይነት ከባድ ጭንቅ ፈተና ተፈጥኖ አያውቅም፡፡ ማንም ሌላ ከሴት የተወለደ ሰው እንዲህ በሀኃአትና በስቃይ የተሞላ የዓለም ሀጢአት ተሸክሞ አያውቅም፡፡ ርህራሄው እጀግ ሰፊ ፍቅሩም እጅግ ጥብቅ የሆነ እንዲህ ዓይነት ሌላ ሰው ፈጽሞ አልነበረም፡፡ የሰውን ልጅ ሁሉ የኖረ በደል ለተሸከሙ ለተፈተኑና ለሚታገሉ ሁሉ የሚያዝን ብቻ ሳይሆን አበሯቸው የሚሆን ነው፡፡EDA 83.5

  ያስተማረውን ነገር የኖረበት ‹ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና› አላቸው ለደቀመዛሙርቱ ‹የአባቴን ትዕዛዝ እንደጠበቅሁ፡፡› ዮሐ 13፡15 ምዕ 15፡10 ስለሆነም በሕይወቱ የክርስቶስ ቃላት ትክክለኛ መገለጫና ድጋፍ ነበሩ፡፡ ከዚህም በላይ የሚለውን ሆኖ የተገኘ ነበር፡፡ የእርሱን ኑሮና ገጠመኙን ብቻ ሳይሆን የእርሱን ባህሪ የሚገልፁ ነበሩ፡፡ እውነት ማስተማር ብቻ አይደለም እርሱ ራሱ እውነት ነበር፡፡ የርሱ ትምህርት ኃይል የሚሆንበትም ምክንያት ይኸው ነበር፡፡EDA 84.1

  ክርስቶስ በእምነት የተሞላ ትክክለኛና ተገቢ ኃይለቃላትን የሚናገር ነበር፡፡ እንደእርሱ አድርጐ ክፉን የሚጠላ ሌላ ሰው እሱንም ያለፍርሃት የሚያወግዝ ሰው እንደእርሱ ማንም አልነበረም፡፡ አርሱ ባለበት ለማንኛውም ውነት ላልሆነ የማያስከብር ነገር ወዲያውኑ ይገስፃል፡፡ በእርሱ ንፁህ ብርሃን ሰዎች የራሳቸውን ነገር ወዲያውኑ ይገስፃል፡፡ በእርሱ ንፁህ ብርሃን ሰዎች የራሳቸውን ቆሻሻ ይመለከታሉ፡፡ የሕይወት ዓላማዎቻቸውም ደካማና ውሸት መሆናቸውን በእርሱ ተረዱ፡፡ እርሱም ወደራሱ ሳባቸው፡፡ እርሱ ሰውን የፈጠረ ስለሆነ፡፡ የሰብዓዊነትን እሴት (ዋጋ) ያውቃል፡፡ ሊባርካቸውና ሊያድናቸው ለሚፈልገው ሰዎች ክፋት ጠላታቸው መሆኑን አውቆ አወገዘ፡፡ በእያንደንዱ ሰው ውስጥ ምንም እንኳ የወደቀ ቢሆንም ወደ መለኮታዊነት ሊመለስ የሚችል የእግዚአብሔር ልጅ ኃይል አለበት፡፡EDA 84.2

  «ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጅ በዓለም እንደፈርድ እግዚአብሔረ ወደዓለም አልላከውምና፡፡» ዮሐ 3፡17፡፡ ሰዎችን ሲሰቃዩና ሲዋረዱ ተመልክቶ ክርስቶስ ተስፋ መቁረጥና ጥፋት ባለበት የተስፋ ቦታ አሰበላቸው፡፡ ፍላጐቱ ባለበት ቦታ ሁሉ ሊያወጣቸው የሚችልበት ዕድል እንዳለ ተመለከተ፡፡ የተፈተኑና የተሸነፉ ነፍሳት መንገድ መሳታቸውን ያውቁና ሊጠፋ የተቃረቡ መሆናቸውን የተገነዘቡትን ሲያገኝ ማውገዝ ሳይሆን ይባርካቸዋል፡፡EDA 85.1

  ለመላው የሰው ልጅ ቤተሰብ የሚሰጠው ሰላምታ «የተባረካችሁ ሆይ» በሚል የሚጀምር ነበር፡፡ የተራራውን ስብከት ለማዳመጥ የተሰበሰበውን ሕዝብ ሲመለከት በአንድ ቅጽበት ላይ በቅድስት ሰማይ ውስጥ አለመሆኑን የረሳ ይመስል ነበር፡፡ የተለመደውን የዓለም ብርሃንን ሰላምታም ሰላም አለ፡፡ ከከንፈሮቹም በረከት እንደወንዝ ፏፏቴ ይወርድ ነበር፡፡EDA 85.2

  ከምኞታዊና ራስን የማርካት ዓለማዊ ፍላጐቶች ለሚመለሱ ምንም ያክል ታላቅ ቢሆን ፍላጐታቸውን እንደሚሰጣቸውና የእርሱን ፍቅርና ብርሃን እንደሚቀበሉ ገልጾአል፡፡ በመንፈስ ለደከሙ፤ ለሚያዝኑ፣ ለሚሳደዱ እጁን በመዘርጋት «ወደኔ ኑ እኔም እረፍት እሰጣችኋለሁ፡፡» ይላቸዋል፡፡ ማቴ 11፡28EDA 85.3

  በእያንዳንዱ ሰብዓዊ ፍጡር ውስጥ ወሰን የሌላቸው ከህሎቶችን (ተሰጥኦዎችን) አስቀምጧል፡፡ ሰዎችን ሊሆኑ በሚገባቸው ደረጃ «የአምላካችን የእግዚአብሔር ብርሃን በላያቸው »ው አያቸው፡፡ መዝ 90፡17 በተስፋ ዐይን እየተመለከታቸው በውስጣቸው ተስፋ እንዲያድርባቸው አነቃቃቸው፡፡ በሙሉ ልብ፣ ስለሚገናኛቸው፣ እምነታቸውን አነሳሳ፡፡ የሰውን እውነተኛና ከፍተኛ ድንቅ ሀሳብ በእሱ ውስጥ በመግለጽ ፍላጐትና እምነት እታሰበላቸው ደረጃ ይደርሱ ዘንድ አነቃቃ፡፡ እርሱ በተገኘበት ቦታ የተናቁና የወደቁ ሁሉ እስከዚያ ጊዜ ድረስም ሰዎች እንደነበሩ ተገነዘቡ፡፡ እናም እርሱ ለሚፈልጋቸው ነገር ብቁ ለመሆን ተመኙ፡፡ ስብሰባዎቹ ልብ ውስጥ ቅዱስ የሆኑትን ነገሮች ሁሉ የማይቀበሉ የሞቱ ይመስሉ የነበሩት በአዲስ ብርታት ተነቃቁ፡፡ ተስፋ ለቆረጡት ብዙሃን የአዲስ ሕይወት ዕድል ከፈተላቸው፡፡EDA 85.4

  ክርስቶስ ሰዎችን በፍቅሩ በቤዛነቱ ከልቡ አቀፋቸው፡፡ በእነዚሁ ማስተሳሠሪያዎችም እርስ በራሳቸው እንደፋቀሩ አደረጋቸው፡፡ በእርሱ ዘንድ ፍቅርና ሕይወት ነበር፡፡ ሕይወትም ለአገልግሎት የተሰጠ ነበር፡፡ «በከንቱ ተከብላችሁ» አለ «በከንቱ ስጡ» ማቲ 10፡8EDA 86.1

  ክርስቶስ ራሱን ለሰው ልጆች መስዋዕት ያደረገው በመስቀሉ ላይ ብቻ አይደለም፡፡ «መልካም እየሠሩ በሄዱ ቁጥር» የሐዋ ሥ 10፡38 የእያንዳንዱ ቀን ሥራ ሁሉ የእርሱ ሕይወት ሥጦታ ነበር፡፡ እንዲህ ዓይነት ሕይወት ሊኖር የሚችለው በአንድ መንገድ ብቻ ነው፡፡ የሱስ በእግዚአብሔር ላይ በመተማመንና ከርሱ ጋር በመገናኘት ኖረ፡፡ ሰዎች በሚስጥር ቦታ በሆነው የሰማዩ ውስጠኛ ክፍል ሁሉን በሚችለው ጌታ ጥላ ሥር ያን ጊዜም ሆነ አሁን ተማፀኑ፡፡ ለተወሰነ ወቅት ተጣበቁ ውጤቱም በክቡር ሥራ ተገለጠ፡፡ ከዚያም በኋላ እምነታቸው ወደቀ፡፡ ግንኙነቱም ተቋረጠ፡፡ ሕይወታቸውም ተበላሸ፡፡ የየሱስ ሕይወት ግን የማያቋርጥ የእምነት ሕይወት ነበር፡፡ በማያቋርጥ ግንኙነት የተጠናከረ ለሰማይና ለምድር የነበረው አገልግሎትም ውድቀት ወይም መንገዳገድና ያልተለመደ አረማመድ የነበረበት አይደለም፡፡EDA 86.2

  እንደአንድ ሰው የእግዚአብሔር ዙፋን የርሱ ትህትናና ሰብዓዊነት ለመለኮታዊው ጋር በሚያገናኘው ሰማያዊ ኃይልEDA 86.3

  እስኪሞላ ድረስ በማገናኘት ከእግዚአብሔር ሕይወትን በመቀበል ለሰዎች ሕይወት ከፍሎ ሰጠ፡፡ «ማንም ሰው እንደዚህ ሰው የተናገረ የለም፡፡» ዮሐ 7፡41 እርሱ በአካላዊነትና እውቀት ነክ ወይም የንድፈ ሐሳብና መላምትን የሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ አተኩሮ ቢያስተምር ኖሮ ይህ ስለክርስቶስ የተነገረው እውነት በሆነ ነበር፡፡ ወደ ውስጥ ብዙ ዘልቆ ለማወቅ የብዙ ምዕተ ዓመታት ልፋትና ጥናት የጠየቁትን ሚስጥራት በከፈተ ነበር፡፡ እስከ ዘመን መጨረሻ ለሀሳብ ምግብና ለመፈለሰፍ አነቃቂ በሆኑ የመፍትሄ ሐሳቦች ሳይንሳዊ በሆኑ መስኮችም ባስከመጡ ነበር፡፡ ነገር ግን ይኸንን አላደረገም፡፡ የሚያጓጓ ወይም የራስ መውደድ ምኞትን የሚቀሰቅስ አንድም ቃል አልተናገረም፡፡ በረቀቀ የንድፈ ሐሳብ አቀራረብ ሳይሆን የሚያስተምረው ለባህሪይ መዳበር ጠቃሚ በሆነ መንገድ ሰው እግዚአብሔርን ለማወቅ ይበቃ ዘንድ ችሎታውን ሊያሰፋለት በሚችልና መልካም ነገር ለመሥራት የሚረዳ ኃይል በሚጨምርለት መንገድ ነበር፡፡ ከህይወት ባህሪ ጋር ስለተያያዙና ሰውን ከዘለዓለማዊው ጋር ስለሚያገናኙ ዕውነታዎች ነበር የሚናገረው፡፡EDA 87.1

  ሰዎች ስለእግዚአብሔር ስለ ሥራው ወይም ስለ ቃሉ የፃፉትን ንድፈ ሐሳብ እንደያጠኑ ሕዝቡን ወደ ሰዎች ንድፈ ሐሳብ ከመምራት ይልቅ በሥራዎቹ በቃሉና በስጦታዎቹ በገለጠው በርሱ እንዲፀኑ አስተማራቸው፡፡ አእምሮአቸው ወሰን ከሌለበት አእምሮ ጋር እንዲገናኝ አደረገ፡፡EDA 87.2

  ሰዎቹ «በርሱ ትምህርት እጅግ ተደነቁ፡፡» «የርሱ ቃል ኃይል ነበረውና፡፡» ሉቃ 4፡32 እንደዚህ ሐሳበን ማነቃቃት የሚችል እንደዚህ ዓይነት ሰው ከእርሱ በፊት ማንም አልነበረም፡፡EDA 87.3

  የክርስቶስ ትምህርቶች እንደአዛኝነቱ ሁሉ አለምን በሙሉ የሚያቅፉ ሆኑ፡፡ በርሱ ትምህርት ሳይሆን አይቀርም ብሎ በግምት መሥራት የለም፡፡ ምክንያቱም መሠረታዊ ሐሳቦቹ ትምህርት ያልሆኑት ማይነኩት የሕይወት አጋጣሚና የሰው ልጅ ኑሮ ዘርፍ አልነበረም፡፡ የካህናት አለቃ፣ የርሱ ቃላት አብረውት ለሚሠሩ ሁሉ እስከዓለም ፍፃሜ ድረስ መመሪያቸው ይሆናል፡፡EDA 88.1

  ለእርሱ የአሁኑና የወደፊቱ የቅርብና የሩቁ አንድ ናቸው፡፡ የሰውን ልጅ ፍላጐቶች ሁሉ ይመለከታል፡፡ የርሱ ሕሊናና ዐይኖች የእያንዳንዱን ሰብዓዊ ፍጡር ፋረትና ውጤት፤ ፈተናና ጦርነት ግራ መጋባትና የሚያደርጉትን ማጣት ከባድ አደጋንና መከራን ሁሉ ይምለከታሉ፡፡ ልቦች ሁሉ ቤቶች ሁሉ ደሰታና ፍስሀ የመንፈስ መነቃቃትም ሁሉ በርሱ ዘንድ የሚታወቁ ናቸው፡፡EDA 88.2

  ለሰው ልጅ ሲል ብቻ ሳይሆን በሰው ልጅ ላይ በሙሉ ተናገረ፡፡ ለትንሹ ልጅ ገና በጧት የደስታ ሕይወቱ ችኩልና ረፍት የለሽ ለሆነው የወጣት ልብ፣ ለጐልማሶች የኃላፊነትና የእንክብካቤ ሸክምን ይዞ ለአረጋዊያንም በድካማቸውና በጭንቀታቸው ሁሉ ለሁሉም የእርሱ መልዕክት ለሰው ልጆች በሙሉ በየአገሩና በየትኛውም የእድሜ ደረጃ ላሉ ሁሉ ተነግሯል፡፡EDA 88.3

  የጊዜው ማለትም አሁን ያሉትና የዘለዓለማዊ ነገሮች የሚታዩት ነገሮችና ከማይታየው ጋርም ያላቸው ግንኙነት፣ የሚያልፉት የዘወትር የሕይወት አደጋዎች በሚመጣው ሕይወት ወደፊት የሚኖሩ ድንቅ ዘላቂ ዕድሎች በርሱ ትምህርት ውስጥ ተካትተው ተጠቃለዋል፡፡EDA 88.4

  በዚህ የአሁኑ ሕይወት ውስጥ ያሉ ነገሮችን ሁሉ በትክክለኛው የመስተጋብር ቦታቸው አስቀምጧቸዋል፡፡ አነስተኞችን ከዘላለማዊ ፍላጐት ጋር አደረገ፡፡ ነገር ግን አስፈላጊነታቸውን ውድቅ አላደረገውም ሰማይና ምድር አንድ ላይ መሆናቸውንና የመለኮትን ዕውነት ማወቅ፡፡ ሰው የየቀኑን የሕይወት ተግባራት በተሻለ መልኩ እንዲየቀናውን ያዘጋጀዋል፡፡EDA 88.5

  በርሱ ዘንድ ያለ ዓላማ የተቀመጡ ነገሮች የሉም፡፡ የሕፃን ልጅ መቧረቅ የአዋቂ ሰው ልፋትና ድካም የሕይወት ደስታዎችና ጥንቃቄዎች እንዲሁም በሕይወት ውስጥ ያሉ ስቃዮች ሁሉም ወደ አንድ ግብ የሚወስዱ መንገዶች ናቸው፡፡ ይኸውም ሰብዓዊነትን ወደላይ ለማንሳት የእግዚአብሔር መግለጫ መሣሪያዎች መሆናቸው ነው፡፡EDA 89.1

  ከርሱ ከንፈሮች የእግዚአብሐር ቃል ከአዲስ ኃይልና በአዲስ ትርጉም ጋር ወደሰው ልጆች ቤትና ልቦና መጣ፡፡ የርሱ ትምህርቶች የተፈጥሮን ነገሮች በአዲስ ብርሃን እንዲታዩ አደረገ፡፡ በተፈጥሮ ገጽ ላይ ያ ሀጢአት ሸፍኖና አበላሽቶት የነበረው የቀድሞ ጸዳለ ብርሃን እንደገና ማብራት ጀመረ፡፡ በሁሉም የሕይወት እውነታዎችና ገጠመኞች ሁሉ የመለኮታዊ ትምህርትና ለመለኮት ጋር የመገናኘት ዕድልም ይገለጥባቸው ነበር፡፡ እግዚአብሔር እንደገና መሬት ላይ አረፈ፡፡ የሰው ልቦናም የርሱን እዚህ መሬት ላይ መሆን ተገነዘቡ፡፡ ዓለምም በርሱ ፈቅር ተከበበች፡፡ ሰማያዊው ነገር ሁሉ ወደሰው መጣ፡፡ በክርስቶስ አማካይነት የዘለዓለማዊነት ሳይንስ ተከፍቶላቸዋልና ልቦች እርሱን አመሰገኑ፡፡EDA 89.2

  «አማኑኤል... እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሆነ» ከእግዚአብሔር በተላከው መምህር ውስጥ ዕውነት የሆነው ትምህርታዊ ሥራዎች ሁሉ መሠረታቸውን ያገኛሉ፡፡ ከአሥራ ስምንት ምዕተ ዓመታት በፊት እንደነበረው ሥራ ሁሉ በዛሬው ሥራው የዓለም መድህን ቃላት እንዲህ ይነገራሉ፡፡EDA 89.3

  «መጀመሪያው መጨረሻም እኔ ነኝ፡ ... ሕይወትም
  «አልፋና ኦሜጋም፡ ... » ራዕ፡ ዮ 1፡17 ምዕ 21፡6
  EDA 90.1

  እንዲህ ዓይነት መምህር ባለበት፣ ከመለኮት ትምህርት ለማግኘት ካለው እድል ጋር ሲታይ እንዲህ ዓይነቱን መምህር ለቅቆ ሌላ ከመፈለግ በጥበብ ርቆ ጥበብን ከመፈለግ የበለጠ እውነትን እየካዱ እውነተኛ ለመምሰል ከመሞከር ከብርሃን እየራሱ ብርሃንን ከመፈለግ የበለጠ ያለ ሕይወት ሕልውናን ከመሻት ከሕያው የውሃ ፏፏቴዎች ፊትን መልሶ ውሃ ሲይዙ ከማይችሉ ሰባራ የውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳዎች ላይ ውሃ ከመፈለግ የበለጠ ሞኝነት አለን?EDA 90.2

  ተዘጋጁ አሁንም እየጋበዛችሁ ነውና «የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣ ከእኔም ይጠጣ በኔ የሚያምነ ሁሉ መጽሐፍ እንዳለ፡፡» ከእርሱ «የሕይወት ውሃ ምንጮች ይወጣሉ፡፡» «በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ የሕይወት ውሃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል፡፡» «እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ሁሉ ለዘላለም አይጠማም፡፡» ዮሐ 7፡37‚38 መዕ 4፡14EDA 90.3

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents