Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
ሥነ - ትምህርት - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  የክርስቶስ የመለወጥ ኃይል

  ከአሥራ ሁለቱ ደቀመዛሙርት መካከል አራቱ በአንድ ልዩ ዘርፍ ወሳኝ የሆነ ተግባር ማከናወን ነበረባቸው፡፡ ለዚህም ዝግጅት እንዲረዳ ክርስቶስ መጪውን ነገር ሁሉ አስተማራቸው፡፡ ያዕቆብ በቅርቡ ለመጣበት በሰይፍ የመመታት ሞትን ለመቀበል በቀርጠኝነት የዘጋጀ ነበር፡፡ ከሁሉም ረዘም ያለ እድሜ የቆየው ዮሐንስ ጌታውን በጽሁፍ እንዲያገለግል፤ ጴጥሮስ ለብዙ ዘመናት መከላከያ አጥር ሆኖ የቆየውን መሠናክል በመበጣጠስና ሃይማኖት የለሹን ዓለም በማስተማር ግንባር ቀደም ፊር ቀደጅ ሆነ፡፡ ይሁዳ ከወንድሞቹ ሁሉ የበለጠ ችሎታ ያለው ሆኖ እያለ ነገር ግን በልቡ ውስጥ ሊያስከትሉ የሚችሉትን ውጤት በሚገባ ሳያጤን የፈፀመው ድብቅ ዓላማ ነበረው፡፡ የክርስቶስ ታላላቅ ግቦችና የርሱን ያላሰለሰ ጥንቃቄ የተሞላበትን ትምህርት ተቀባዮቹ እነዚህ ነበሩ፡፡EDA 94.1

  ጴጥሮስ ያዕቆብና ዮሐንስ ከአለቃቸው ጋር ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በሆነ ምክንያት ከርሱ ከጌታቸው ጋር መገናኘት ያዘወትሩ ነበር፡፡ ይህ ፍላጐታቸው ደግሞ ተሳክቶላቸዋል ተሟልቶላቸዋልም፡፡ ከአሥራ ሁለቱ ሁሉ እነሱ የበለጠ ቀረቤታ ነበራቸው፡፡ ዮሐንስ ደግሞ ከሁሉም የበለጠ ትስስር ስለነበረው ይረካ ነበር፡፡ እርሱም እንደዚሁ ተሳክቶለታል፡፡ በዮርዳኖስ ዳር በተደረገው የመጀመሪያ ስብሰባ ላይ እድርያስ የሱስን ሰምቶ ወንድሙን ለመጥራት ቸኮለ፡፡ ዮሐንስ ፀጥ ብሎ ተቀመጠ፡፡ ልቦናውን ወደእነዚህ አስደናቂ ንግግሮች በትኩረት አሰባሰበ፡፡ አዳኙን ተከተለ፡፡ ሁልጊዜ በጉጉትና በትጋት የሚከታተል አዳማጭ ነበር፡፡ ይሆን እንጅ ዮሐንስ ያለስህተት አልነበረም፡፡ የተረገጋ አልነበረም፡፡ አንድ ነገር የሚያልም ኃይለኛ ነበረ እንጂ፡፡ እርሱና ወንድሙ «የመብረቅ ልጆች» ይባሉ ነበር፡፡ ማርቆ 3፡27 ዮሐንስ ኩሩ፤ አንድ ዓላማ ያለው፤ ኃይለኛ ተዋጊ ወይም ለጥል የሚቸኩል ነበር፡፡ ነገር ግን ከነዚህ ሁሉ መለኮታዊው መምህር ትጉህ ፍፁም ንፁህ፤ አፍቃሪ ልብ የላቸውን መረጠ፡፡ የሱስ የእሱን (የዮሐንስን) ራስወዳድነት ገሰፀ፡፡ ምኞቱንም ተስፋ አስቆረጠው፡፡ እምነቱንም ፈተነው፡፡ ለዮሐንስም ከልቡ የተመኘለትን ገለፀለት ያም የቅድስና ውበትና ለውጥ ሊያስከትል የሚችለውን የርሱን ፍቅር «ከዓለም ለሰጠኸኝ ሰዎች» አለ ለአባቱ «ስምህን ገለጽሁላቸው» ዮሐ 17፡6EDA 94.2

  የዮሐንስ ባህሪ ፍቅርን አዛኝነትንና ወዳጅትነትን የሚመኝ ዓይነት ነበር፡፡ ወደየሱስ በጣም ገፍቶ ይጠጋ ነበር፡፡ አጠገቡ ይቀመጣል፡፡ አንገቱን ወደደረቱ ያዘነብላል፡፡ አበባ ፀሐይና ጤዛ እንደምታገኝ እርሱም የመለኮትን ብርሃንና ሕይወት ተመገበ፡፡ መድኃኔዓለምን በማክበርና በማፍቀር ያዘ የክርስቶስ ተምሳሌነትና ወዳጅነት ጽኑ ፍላጐቱ እስከሚሆን ድረስ በባህሪው ውስጥ የመምህሩ ባህሪ እስከሚንፀባረቅ ድረስ እጅግ ወደርሱ ቀረበ፡፡EDA 95.1

  «ከፈሪሳዊያንም ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፡፡ እርሱም በሌሊት ወደየሱስ መጥቶ መመህር ሆይ እግዚአብሔር ከርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እንዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደመጣህ እናውቃለን አለው፡፡ እየሱስም መልሶ እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው፡፡» ዮሐ 3፡1-3EDA 95.2

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents