Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
ሥነ - ትምህርት - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  «አስገራሚውን የእርሱን ሥራ ተመልከቱ በእውቀት ፍፁም የሆነውን፡፡»

  ምዕራፍ 14—ሳይንስና መጽሐፍ ቅዱስ

  «እነዚህ ጌታ የሠራቸውን ነገሮች
  ሁሉ የማያውቅ ማን ነው?»
  EDA 140.1

  ሳይንስ፣ የተፈጥሮና የመገለጥ መጽሐፍ ፣ የዚያን የታላቅ አእምሮ ሕትመት ምልከት የያዘ መጽሐፍ የተዋሐደ ንግግር ከማድረግ በስተቀር ሌላ ምንም ማለት የማይችል መጽሐፍ ነው፡፡ በተለያዩ ዘዴዎችና በተለያዩ ቋንቋዎች ነገር ግን እነኛውኑ እውነቶች መልሰው የሚመሰክሩ ናቸው፡፡ ሣይንስ ዘወትር አዲስ ግኝቶች ላይ ትደርሳለች፡፡ ነገር ግን በትክክለኛው መንገድ ከተስተዋለ የመለኮትን መገለጥ እንጅ ሌላ የሚያጋጭ ሐሳብ አታመጣም፡፡ የተፈጥሮ መጽሐፍና የተፃፈው ቃል አንዱ በሌላው ላይ ያበራል፡፡ እርሱ ሥራዎቹን ከሚያከናውንባቸው ሕጐች አንዳንድ ነገር በማስተማር ከእግዚአብሔር ጋር ያስተዋውቁናል፡፡EDA 140.2

  ከተፈጥሮ ላይ ተሰብስበው የተወሰዱና በተሳሳተ መንገድ ግንዛቤ ከተጨበጠባቸው ዕውነታዎች ተነስቶ የተሳሳቱ ድምዳሜዎች ላይ መድረስ በሳይንስና በመገለጥ መካከል ሊፈጠር ወደሚችል የግምት ግጭቶች ያመራሉ፡፡ እንደገናም ተመልሰው ስምምነትና ቅንብር እንዲፈጥሩ ለማድረግ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃላት ወስደው የሚተረጐሙ መጽሐፍት ለማዘጋጀት ጥረት ተደርጓል፡፡ እነዚህ ጽሁፎችም የእግዚአብሔር ቃል ያለውን ኃይል ዝቅ የሚያደርጉና የሚያጠፉ ናቸው፡፡ የዘፍጥረትን የሙዚየምነት የቃል በቃል ትርጉም እንዲቃረን ተደርጐ የተዘጋጀ የሥነ-ምድር ትምህርት ተሰጥቷል፡፡ መሬትን ከምስቅልቅል ውስጥ አውጥቶ በአሁኑ መልኳ ለመፍጠር በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአመታት አዝጋሚ ለውጥ እንዳስፈለገ ተደርጐ ተነገረ፡፡ በዚህ በሣይንስ በተገመተው መገለጥ ውስጥ ለመጽሐፍ ቅዱስ ቦታ ለመስጠት ሲባልም የዘፍጥረት ቀኖች እጅግ ሰፊ፣ ያልተወሰነ ጊዜ በሺዎችና እንዲያውም ሚሊዮን ዓመታትን የሚሸፍኑ እንደሆነ ተደርጐ ታሰበ፡፡ EDA 140.3

  እንዲህ ዓይነት ድምዳሜ በአጠቃላይ ተቀባይነት የሌለው ነው፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባዎች እርስ በራሳቸውም ሆነ ተፈጥሮ ከምትሰጠው ትምህርት ጋር የሚስማማ ነው፡፡ በዘፍጥረት ሥራ ውስጥ የመጀመሪያው ቀን ራሱ ተዘግቧል፡፡ «ማታም ሆነ ጠዋት አንድ ቀን፡፡» ዘፍ 1፡5 እንደዚሁም እያንዳንዱ ለመጀመሪያ ስድስት የፍጥረት ሳምንት ቀናት ሁሉም የተባለው ይኸው ነው፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ወደዚህ ባሉት ቀናት እንደ ሆነው ሁሉ እነዚህ የመነሳሳት ጊዜዎች የራሳቸው ሙሉ ቀንና ሌሊት እንደነበራቸው ተገልጿል፡፡ ራሱን የፍጥረትን አሠራር በተመለከተ መለኮታዊው የምስክር ቃል እንዲህ ይላል፡፡ «እርሱ ተናግሯልና ሆኑም፣ እርሱ አዘዘ ፀኑም፡፡» መዝ 33፡9 እርሱ ባለ ጊዜ ቁጥር የሌላቸው ዓለማት ሕልው ሆኑ፡፡ ታዲያ መሬት ከሆነ ምስቅልቅል ወጥታ ለመፈጠር ይህን የሚሉትን ያክል ረዥም የለውጥ ዓመታት እንዴት ወሰደባት? የእርሱን ሥራዎች አጠናቀን መዝግበን ለመያዝ ስንል ቃሉን መጣስ ይገባናልን?EDA 141.1

  እርግጥ ነው በመሬት ውስጥ የሚገኙ ቅሪት አካሎች አሁን ከሚታወቁት በጣም የበለጡ ግዙፍ ሰዎች እንስሳትና አትክልቶች እንደነበሩ ይመሰክራሉ፡፡ እነኝህ ነገሮች የቅርስ መዛግብት መሰብሰብና መመዝገብ ከጀመሩ በፊት የነበሩ የአትክልትና እንስሳት ሕይወት መኖሩን ያረጋግጣሉ የሚባሉ ናቸው፡፡ ነገር ግን እነዚህን ነገሮች በተመለከተ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ጥሩ መግለጫ ይሰጣል፡፡ ከውሃ ጥፋት በፊት የአትክልቶችና እንስሳት ሕይወትና እድገት ከዚያ ወዲህ ከሚታወቀው እጅግ በበለጠ ልክ የሌለው ግዙፍ ነበረ፡፡ በውሃ ጥፋት ጊዜ የመሬት ገጽ ተሰባበረ፡፡ ትልቅ ምልክት ያለው ለውጥም ተፈጠረ፡፡ በመሬት አካል መልሶ መጠገን ምክንያት ቀደም ሲል ለነበሩ ነገሮች ሕይወት ብዙ ማስረጃዎች ተጠብቀው ተገኝተዋል፡፡ በውሃ ጥፋት ጊዜ እንዳለ መሬት ውስጥ ተቀብሮ የነበረው እጅግ ሰፊ ደን ወደከሰልነት ከተቀየረበት ጊዜ ጀምሮ ከትልልቅ የከሰል ማዕድን ሥፍራዎች ለዛሬው ምቾታችንና ድሎታችን የሚያገለግሉ የነዳጅና ዘይት አቅርቦቶች ሆነውልናል፡፡ እነኝህን ነገሮች ወደብርሃን አምጥተን ስንመለከታቸው በለሆሳስ (ፀጥ ባለ) ድምጽ የእግዚአብሔርን ቃል እውነትነት የሚመሰክሩ ናቸው፡፡EDA 141.2

  ስለመሬት አዝጋሚ ለውጥ እንደተባለው ሁሉ በተመሳሳይ ሁኔታ ከጀርሞች፣ ሞላስኮችና ኳድሩፔዶች ዝርያዎች ቡድን በአንድ የሆነ የእድገት ለውጥ መስመር ተከታትለው በአዝጋሚ ለውጥ የፍጥረታት የመጨረሻ የክብር ዘውድ የሆነውን ሰውን እንደፈጠሩ ተደርጐ ሐሳብ ቀርቧል፡፡EDA 142.1

  የሰው ልጅ ለምርምር የተሰጡትን እድሎች ስናመዛዝን የተግባር አድማሱ ምን ያክል ውሱን፣ የማየት ችሎታውም የተከለለ በድምዳሜ ሐሳቦቹ ላይም ምን የክል ተደጋጋሚና ትልልቅ ስህተቶች እንደሚሠራ በተለይም በውሸት የተቀመጡ ሐሳቦች ከመጽሐፍ ቅዱሰ ታሪክ የሚቀድሙ ድርጊቶችን በተመለከተ የሳይንስ ግምታዊ ሂሳቦች ስንት ጊዜ ተከልሰው የተቀመጡ ወይም ወደጐን የተጣሉ አሉ፡፡ የዓለም ዕድገት ወሰደ ተብሎ የተገመተው ዘመን ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚሊዮን ዓመታት የብልጫ ወይም የማነስ ልዩነት የሚያሳየው በምንድን ነው? በተለያዩ ሳይንቲስቶች የቀረቡ ንድፈ ሐሳቦችስ እንደምን ይጋጫሉ? ይህን ሁሉ ስናመዛዝን ዝርያችን ከጀርሞች ሞልስኮችና ጦጣዎች የመጣ መሆኑን ወደኋላ ተመልሰን በመከታተለ ለማወቅ ስንል በቀላል አቀማመጥ የተቀመጠውን ታላቅ የቅዱስ መጽሐፍትን ቃላት ወዲያ እንጣልን? «እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው» ዘፍ 1፡27 በነገሥታት አደባባዮች ከተከበረ መዝገብ በላይ የሚያኮራንን «የአዳም ልጅ የእግዚአብሔር ልጅ፡፡» ሉቃ 3፡38 ይኸንን የመሰለ የዘራችን መሠረት የሚገልፀውን ዘገባ ወዲያ እንጣልን?EDA 142.2

  በትክክል ከተስተዋለ የሳይንስ መግለጫዎችና የሕይወት ልምዶች እግዚአብሔር የፍጥረት ውስጥ ያለማቋረጥ ለሚሠራው ነገር ሁሉ ከመጽሐፍ ምስክርነት ጋር የሚስማሙና የተቀነባበሩ ናቸው፡፡EDA 143.1

  በነህምያ በተመዘገበው መዝሙር ውስጥ ሌዋውያን «አንተ ብቻ እግዚአብሔር ነህ ሰማይንና የሰማያትን ሰማይ ሠራዋታቸውንም ሁሉ ምድርንና በርሷ ላይ ያሉትን ሁሉ ባህሮችንና በእነርሱ ውስጥ ያለውን ሁሉ ፈጥረሃልና ሁሉን ሕያው አድርገኸዋል፡፡» እያሉ ይዘምሩ ነበር፡፡ ነህምያ 9፡6EDA 143.2

  ይኸንን ዓለም በተመለከተ የዘፍጥረት ሥራ ፍፁም የተሟላ እንደነበረ ይገለፃል፡፡ «ሥራው ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ተፈጽሟል፡፡» ዕብራ 4፡3 የእግዚአብሔር ኃይል ግን የርሱን ፍጡሮች ሁሉ ጠብቆ በመያዝ አሁንም እየሠራ ነው፡፡ የልብ ዓመታትና ትንፋሽም በትንፋሽ እየተተካካ የሚሄደው አንድ ጊዜ በራሱ ውስጥ በተፈጠረለት ኃይል እንቅስቃሴ መሠረት ብቻ የሚቀጥል አይደለም፡፡ እያንዳንዱ ትንፋሽና የደም አመታት በርሱ ጥንቃቄ የምንኖርና የምንቀሳቀስ ሕልውናችንም ጭምር በርሱ ላይ ያለ ለመሆኑ መረጃ ነው፡፡ ከትንሽ ነፍሳት እስከ ሰው ድረስ እያንዳንዱ ሕይወት ያለው ፍጡር ሁሉም ሕልውናው በየቀኑ በርሱ ስጦታ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡EDA 143.3

  «ምግባቸውን በየጊዜው ትሰጣቸው ዘንድ እነዚህ ሁሉ
  አንተን ተስፋ ያደርጋሉ፡፡ በሰጠሃቸውም ጊዜ
  ይሰበስባሉ፡፡ እጅህን ትከፍታለህ ከመልካም ነገርም
  EDA 143.4

  ይጠግባሉ፡፡ ፊትህን ስትሰውር ይደነግጣሉ፡፡EDA 144.1

  ፍሳቸውን ታወጣለህ ይሞታሉም፡፡ ወደአፈራቸውም ይመለሳሉ፡፡ መንፈስህን ትልካለህ ይፈጠራሉም፡፡ የምድርን ፊት ታድሳለህ፡፡» መዝ 104፡27-30EDA 144.2

  «ሰሜንን በባዶ ስፍራ ላይ ይዘረጋል ምድሪቱንም
  በታችዋ አንዳች አልባ ያንጠለጥላል፡፡ ውኆችን
  በደመናዎች ውስጥ ያስራል፡፡ ደመናይቱ ከታች
  አልተቀደደችም፡፡ ብርሃንና ጨለማ እስከሚለዩበት
  ድረስ በውኆች ፊት ላይ ድንበርን አደረገ፡፡»
  «የሰማይ አእማድ ይንቀጠቀጣሉ ከተግሳፁም የተነሳ
  ይንቀጠቀጣሉ፡፡ በኃይሉ ባህርን ፀጥ
  ያደርጋል፡፡ …… በመንፈሱ ሰማያት ውበትን አገኙ፡፡ እጅም
  በራሪይቱን እባብ ወጋች፡፡ እነሆ ይህ የመንገዱ ዳርቻ
  ብቻ: ነው፡፡ ይህም የሰማነው ነገር ምንኛ ጥቂት ፡፡
  የኃይሉንስ ነጐድጓድ ያስተውል ዘንድ ማን ይችላል፡፡ ኢዮብ 26፡7-10 ፣ 26፡11-14.
  «እግዚአብሔር በወጀብና በአውሎ ነፋስ ውስጥ መንገድ
  አለው፡፡ ደመናም የእግሩ ትቢያ ነው፡፡ ናሆም 1፡3
  EDA 144.3

  በተፈጥሮ ውስጥ የሚሠራውና ለሁሉም ነገሮች ሕይወት የሚሰጠው የእግዚአብሔር ኃይል አንዳንድ የሳይንስ ሰዎች እንደሚሉት በሁሉም ዘንድ ያለ የማሠራት ኃይል ያለው መርህ ብቻ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር መንፈስ ነው፡፡ ይሁንና ሕያው አካለም ነው፡፡ ሰው በእርሱ አምሳል ተፈጥሮአልና፡፡ እግዚአብሐር እንደ አንድ ሕያው አካል ራሱን በልጁ ገልጧል፡፡ የሱስ የአባቱን ክብር «የሚያንፀባርቅና የባህሪው ምሳሌ ሆኖ፡፡» (እብ 1፡3) በመሬት ላይ በሰው መልክ ኖረ፡፡ እንደ አንድ የግል መድህን ወደዚህ ዓለም መጣ እንደ ግል መድህን ወደላይ አረገ፡፡ እንደ አንድ የግል መድህን በሰማይ አደባባይ መካከል ገባ፡፡ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊትም ስለእኛ ያገለግላል «እንደ ሰው ልጅ ሆኖ፡፡» ዳን 7፡13 EDA 144.4

  ሐዋሪያው ጳውሎስ በመንፈስ ቀዱስ ተመርቶ ሲጽፍና ስለ ክርስቶስ ሲገለጽ «ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአልና፡፡ እርሱ ከሁሉ በፊት ነው፡፡ ሁሉም በእርሱ ተጋጥሞአልና፡፡» ቆላሳ 1፡16‚17 ዓለማት ሁሉ በሕዋው ውስጥ እንዲቆዩ ያስቻላቸው እጅ በቅደም ተከተላቸውም በሥነሥርዓት እንዲኖሩ አድርጐ የያዘ ያ እጅ በእግዚአብሔር ፍጥረተዓለም ዩኒቨርስ ሁሉ ያሉትን ነገሮች እንቅስቃሴአቸው ሳይደክም እንዲቀጥል ያስተካከለ ያ እጅ ነው ለእኛ ሲል በመስቀል ላይ የተቸነከረው፡፡EDA 145.1

  የእግዚአብሔር ታላቅነት በእኛ አቅም ሊስተዋል የሚችል አይደለም፡፡ «የጌታ ዙፋን በሰማይ ላይ ነው፡፡» መዝ 11፡4 ይሁንና በመንፈሱ በሁሉም ቦታ ይገኛል፡፡ የእጁ ሥራዎች ለሆኑት ነገሮች ሁሉ ጥልቅ ዕውቀትና የግል ፍቅር አለው፡፡EDA 145.2

  «እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር የሚሆን ማነው?
  በላይ የሚኖር በሰማይና በምድር የተዋረድትን
  የሚያይ፡፡»

  «ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ? ከፊትህስ ወዴት
  እሸሻለሁ? ወደ ሰማይ ብወጣ አንተ ከዚያ ነህ»
  መዝ 139፡8 ኢዮብ 26፡6

  «የንጋትን ክንፍ ብወስድ እስከባህር መጨረሻም ብበር
  በዚያ እጅህ ትመራኛለች፡፡ ቀኝህም ትይዘኛለች፡፡ መዘ 113፡5‚6 ምዕ 139፡10

  EDA 145.3

  «አንተ መቀመጤንና መነሳቴን አወቅህ፡፡ ሀሳቤን ሁሉ
  ከሩቅ አስተዋልህ፡፡ ፍለጋዬንና ረፍቴን አንተ
  መረጥህ መንገዶቼን ሁሉ
  ቀድመህ አወቅህ፡፡ አቤቱ አንተ
  እነሆ የቀደመውንና የኋላውንና የፊቱን አወቅህ
  አንተ ፈጠርኸኝ እጅህንም በላየ አደረግህ እውቀትህ ከእኔ
  ይልቅ ተደነቀች በረታች ወደርሷም ለመድረስ
  አልችልም፡፡ መዝ 139፡2-6
  EDA 145.4

  ሁሉን የሠራ ጌታ የማግኛ መንገዱንና ውጤቱን ፍላጐትና አቅረቦትን በአስገራሚ ሁኔታ ያስማማው እርሱ ነው፡፡ በዚህ ዓለም ላይ ያለ ንብረትን በተመለተ በውስጣችን ለተፈጠሩብን ፍላጐቶች ሁሉ ማርኪያውንም የሰጠን እርሱ ነው፡፡ የሰውን ነፍስ የፈጠረ የማወቅና የማፍቀር ችሎታ የሰጠ እርሱ ብቻ ነው፡፡ እርሱ ደግሞ የነፍስ ፍላጐት እንዳይረካ የሚያደርግ አይደለም፡፡ በዚህ ከኃጢአት ከሀዘንና ከስቃይ ጋር ትግል በሚደረግበት ዓለም ውስጥ ተጨባጭ ያልሆነ መርህ የግል ያልሆነ ውስጠ መሠረት ከሌላ ሰው በተወሰደ ሀሳብ የሰው ልጆች ፍላጐትና ምኞት ሊረካ አይችልም፡፡ በሕግና በኃይል ልቦናን በማይሰበስብ ነገር እርዳታ የሚጠይቁ የጩኸት ድምጾችን ሰምተው በማያውቁ የሃይማኖት ነገሮች ላይ ማመን በቂ አይደለም፡፡ ሁሉን ነገር አስተካክሎ መያዝ የሚችል ክንድ መኖሩን ማወቅ የሚያዝንልንና ወሰን የሌለው ጓደኛ መኖሩን ማወቅ ያስፈልገናል፡፡ ሞቅ ያለውን የእርሱን እጅ መጨበጥ ይኖርብናል፡፡ ገርነትና የዋህነት በተሞላችው ልብ ላይ ማመን አለብን፡፡ እግዚአብሔር ራሱን በቃሉ ውስጥ ገልጧልና፡፡EDA 146.1

  ወደ ተፈጥሮ ሚስጢሮች ውስጥ ጠለቅ ብሎ ገብቶ የሚያጠና ሰው የራሱን ድንቁርናና ደካማነት ሙሉ ለሙሉ ሊገነዘብ ይችላል፡፡ ሊደርስባቸው የማይችል ጥልቆችና ከፍታዎች ዘልቆ ሊገባባቸውና ሊደርስባቸው የማይችለ ሚስጢሮች እፊቱ የተዘረጉ ገና ያልተገባባቸው እጅ ሰፋፊ የእውነት መስኮች መኖራቸውን ይረዳል፡፡ ከኒውተን ጋር እንዲህ ለማለት ይዘጋጃል፡፡ «ገና ያልታሰሰው ታላቁ የእውነት ውቅያኖስ እፊቴ ተዘርግቶ ሳለ በባህር ዳርቻ ጠጠሮችና ዛጐል እየፈላለገ እንደሚለቅም ሕፃን መሆኔ እኔ ለራሴ ይሰማኝ ነበር፡፡»EDA 146.2

  የሳይንስ ተማሪዎች ወደ ጥልቀት በገቡ ቁጥር በተፈጥሮ ውስጥ ወሰን የሌለበትን አምላክ ሥራ ለመገንዘብ ይገደዳሉ፡፡ ነገር ግን ሰው ምክንያቶችን ሲያፈላልግ የሚረዳው ኃይል ካላገኘ በስተቀር የተፈጥሮ ትምህርት እርስ በራሱ የሚምታታና ተስፋ የሚያስቆርጥ ከመሆን በስተቀር ሌላ ምንም አይፈይድም፡፡ በመገለጥ ብርሃን አማካይነት ብቻ ነው በትክክል ሊነበብ የሚችለው፡፡» በእምነት እናስተውላለን፡፡» እብ 11፡3EDA 146.3

  «በመጀመሪያ እግዚአብሔር» (ዘፍ 1፡1) እዚህ ላይ እንኳ ለማወቅ ካለው ጉጉት አንፃር ለሚያነሳው ጥያቄ እርግቧ ወደመርከቡ በርራ እንደ ገባች እንዲሁም አእምሮም ረፍት ያገኛል፡፡ በላይም በታችም በማዶም ወሰን የሌለው ፍቅር ነገሮች «የበጐነት ፈቃድ ይፈጽም ዘንድ፡፡» 2ኛ ተሰለ 1፡11EDA 147.1

  «የማይታየው ባህሪይው ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት አምላክነቱ ታውቆ በእርሱ ይስተዋላል፡፡» ሮሜ 1፡20 ምስክርነታቸው ሊስተዋል የሚችለው በመለኮታዊ መምህር እርዳታ ብቻ ነው፡፡ «በእርሱ ውስጥ ካለው ከሰው መንፈስ በስተቀር ለሰው ያለውን የሚያውቅ ሰው ማን ነው? እንዲሁም ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር ለእግዚአብሔር ያለውን ማንም አያውቅም፡፡» 1ኛ ቆሮ 2፡11EDA 147.2

  «ነገር ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል» ዮሐ 16፡13 በዚያ መንፈስ እርዳታ ብቻ በመጀመሪያ «በውሆች ላይ ያረፈው» ከዚያ ቃል ውስጥ «ሁሉም ነገሮች የተሠሩ» ከዚያ «እውነተኛ ብርሃን ወደ እርሱ ለሚመጣ ሰው ሁሉ የሚያበራው ብርሃን» ብቻ ነው የሳይንስ ምስክርነት ትክክል ሊተረጉም የሚችለው ጥልቅ የሆኑት እውነቶች ሁሉ ተለይተው ሊታወቁ የሚችሉት በእነሱ አመራር ብቻ ነው፡፡EDA 147.3

  ዘለዓለማዊ ጠቢብ በሆነው አምላክ አመራር ስንመራ ብቻ ነው ሥራዎቹን ስናጠና የርሱን ሐሳቦች ተከትለን ለማሰብ የምንችለው፡፡EDA 147.4

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents