Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
ሥነ - ትምህርት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ታማኝነት የተሞላባቸው የሥራ ግንኙነቶች

    «የንፁሐንን መንገድ እግዚአብሔር ያውቃል፡፡ ርስታቸውም ለዘላለም ነው፡፡ በክፉ ዘመን አያፍሩም በራብ ዘመንም ይጠግባሉ፡፡» መዝ 37፡18-19EDA 154.2

    «በቅንነት በሚሄድ ጽድቅንም የሚያደርግ በልቡም እውነትን የሚናገር በአንደበቱ የማይሸነግል በባልጀራው ላይ ክፋትን የማያደርግ ዘመዶቹንም የማይሰድብ፡፡ ኃጢአተኛ በፊቱ የተናቀ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን የሚያከብር፡፡ ለባልንጀራው የሚምል የማይከዳም፡፡» «በጽድቅ የሚሄድ ቅን ነገርንም የሚናገር በሽንገላ የሚገኝ ትርፍን የሚንቅ መማለጃን ከመጨበጥ እጁን የሚያራግፍ ደግ ማፍሰስን ከመስማት ጆሮቹን የሚያደነቁር ክፋትንም ከማየት ዐይኖቹን የሚጨፍን ነው፡፡.. እንጀራም ይሰጠዋል ውኃውም የታመነች ትሆናለች፡፡... ዓይኖችህ ንጉሡን በውበቱ ያዩታል፡፡ እነርሱም በሩቅ ያለች ምድርን ያዩአታል፡፡ » መዝ15፡2-4 ኢሳ 33፡15-15EDA 155.1

    እግዚአብሔር በቃሉ ውስጥ ስለአንድ የበለፀገ ሰው ይገልፃል፡፡ አንድ ሰው በትክክለኛው አነጋገር የተሳካለት ባለፀጋ ሰው ሰማይና ምድር ስለ አከበረው ሰው፡፡ በኑሮው ስለገጠመው ነገር ኢዮብ እንዲህ ይላል፡፡EDA 155.2

    «በሙሉ ሰውነቴ እንደነበርሁ ጊዜ
    እግዚአብሔር ድንኳኔን በጋረደ ጊዜ
    ሁሉን የሚችል አምላክ ከእኔ ጋር ገና ሳለ
    ልጆቼም በዙሪያዬ ሳሉ መንገዴ በቅቤ
    ይታጠብ በነበረ ጊዜ ድንጋዩ የዘይት ፈሳሽ
    ያፈስስልኝ በነበረ ጊዜ ወደከተማይቱ
    በር በወጣሁ ጊዜ በአደባባዩም ወንበሬን
    ...ባኖርሁ ጊዜ ጐበዛዝት እኔን አይተው
    ተሸሸጉ፡፡ ሽማግሌዎችም ተነስተው ቆሙ፡፡
    አለቆቹ ከመናገር ዝም አሉ እጃቸውንም
    በአፋቸው ላይ ጫኑ፡፡ የታላላቆቹ ድምጽ አረመመ
    ምስላቸውም በትናጋቸው ተጣጋ፡፡»

    «የሰማችኝ ጆሮ አሞገሰችኝ፤ ያየችኝም ዐይን
    መሰከረችልኝ የሚጮኸውን ችግረኛ ድሀ
    EDA 155.3

    አደጉንና ረጅ የሌለውን አድኜ ነበርሁና፡፡»

    «ለጥፋት የቀረበው በረከት በላዬ መጣ
    የባልቴቲቱንም ልብ እልል አሰኘሁ፡፡
    ጽድቅን ለበስሁ እርሷም ለበሰችኝ፣
    ፍርዴም እንደ መጐናፀፊያና አንደ ኩፋር
    ነበረ፡፡ ለስውር ዓይን ለአንካሳ እግር ነበርኩ
    ለድሀው አባት ነበርሁ የማላውቀውን ሰው
    ሙግት መረመርሁ፡፡»

    «መፃተኛው ግን በሜዳ አያድርም ነበር
    ደጄንም ለመንገደኛ እከፍት ነበር፡፡»

    «ሰዎች እኔን ሰምተው በትዕግሥት ተጠባበቁ፤
    ...የፊቴንም ብርሃን አላወረዱም፡፡ መንገዳቸውን
    መረጥሁ እንደ አለቃ ሆኜ ተቀመጥሁ ንጉሥ
    በሠራዊቱ መካከል እንደሚኖር፣ኅዘነተኞችን
    እንደሚያጽናና ኖርሁ፡፡» ኢዮብ 29፡4-16፣31፡32 29፡21-25
    EDA 156.1

    «የእግዚአብሔር በረከት ባለጠጋ ታደርጋለች ሀዘንንም ከርሷ ጋር አይጨምርም፡፡» ምሳ 10፡22EDA 156.2

    «ብልጽግናና ክብር በእኔ ዘንድ ነው ብዙ ሀብትና ጽድቅም፡፡» ምሳ 8፡28EDA 156.3

    መጽሐፍ ቅዱስ ከእግዚአብሔርና ከሌሎች ሰዎች ጋር በሚኖረን ግንኙነት ከትክክለኛው መርህ ውጪ ስንሄድ ውጤቱን ያሳየናል፡፡ የሱን ስጦታ ተቀብለው እርሱ እንዲያደርጉ የሚፈልግባቸውን ነገር ቸል ለሚል ሰው እግዚአብሔር እንደዚህ ይላል፡፡EDA 156.4

    «ልባችሁን በመንገዳችሁ ላይ አድርጉ ብዙ ዘራችሁ ጥቂትም አገባችሁ፡፡ በላችሁ ነገር ግን አልጠገባችሁም፡፡ ጠጣችሁ ነገር ግን አልረካችሁም፣ ለበሳችሁ ነገር ግን አልሞቃችሁም ደመወዙን የተቀበለ ሰው በቀደደ ከረጢት ያደርገው ዘንድ ደመወዙን ተቀበለ፡፡... እናንተ ብዙ ነገርን ተስፋ አደረጋችሁ፤ እነሆም ጥቂት ሆነ ወደ ቤትም ባገባችሁት ጊዜ እፍ አለሁበት፡፡» «ሃያ መስፈሪያ ወዳለበት ምርት በመጣ ጊዜ የተገኘው አሥር መስፈሪያ ብቻ ነው፡፡ አምሳ ማድጋም ይቀዳ ዘንድ ወደ መጥመቂያው በመጣ ጊዜ የተገኘው ሃያ ብቻ ነው፡፡» «ለምንድን ነው ይላል እግዚአብሔር የሠራዊት ጌታ እናንተ ግን እኔን ሰርቃችኋል» «ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን?» ብላችኋል እናንተ ግን እኔን ሰርቃችሏል፡፡ እናንተም የሰረቅንህ በምንድን ነው? ብላችኋል፡፡ በአሥራትና በበኩራት ነው፡፡ «ስለዚህም ሰማያት በላያችሁ ጠልን ከልክለዋል መድሪቱመ ፍሬዋን ከልክላለች፡፡» ሐጌ 1፡5-9 ሚል 3፡8 ሐጌ 1፡10EDA 156.5

    «ድሀውን ደብድባችኋልና ...ከተጠረበ ድንጋይ ቤቶችን ሠርታችኋልና ነገር ግን አትቀመጡባቸውም፡፡ ያማሩ የወይን ቦታዎች ተክላችኋል ነገር ግን ከወይን ጠጃቸው አትጠጡም፡፡» «በምትሠራው ሥራ ሁሉ እግዚአብሔር መርገምን ሽሽትን ተግሳጽን የሰድድብሃል፡፡» «ወንዶችና ሴት ልጆችህ ለሌላ ሕዝብ ይሰጣሉ ዐይኖችህም ያያሉ ሁልጊዜም ስለነርሱ ሲባክኑ ያልቃሉ በእጅህም ኃይል ምንም አይገኝም፡፡» አሞጽ 5፡11 ዘዳ28፡20-32EDA 157.1

    «በቅን ሳይሆን ባለጠግነትን የሚሰበስብ ሰው ነው በእኩሌታ ዘመኑ የተወዋል፤ በፍፃሜውም ሰነፍ ይሆናል፡፡ ኤር 17፡11EDA 157.2

    ከእያንዳንዷ የንግድ እንቅስቃሴ የምትገኝ ሃሳብ በእያንዳንዷ ልውውጥ ያለች ዝርዝር በማይታዩ ኦዲተሮች ይጠበቃሉ፡፡ እነዚህ ሂሳብ መርማሪዎች ያለሐቅ ከሆነ ነገር ጋር የማይደራደረው ስህተትን ዝም ብሎ ከማያልፈው ስህተትን የማይታገሰው አምላክ የርሱ ናቸው፡፡EDA 157.3

    «ከፍ ካለው በላይ ከፍ ያለ ይመለከታልና በአገሩ ድሆች ሲገፉ ፍርድና ጽድቅም ሲነጠቅ ባየህ ጊዜ አታድንቅ፡፡» «ኃጢአትን የሚሰሩ ይሰወሩበት ዘንድ ጨለማ ወይም የሞት ጥላ የለም፡፡» መክ 5፡8 እዮ 34፡22EDA 158.1

    «አፋቸውን በሰማይ አኖሩ፡፡ እንዲህም አሉ እግዚአብሔር እንዴት ያውቃል? በልዑል ዘንድ በውኑ እውቀት አለ? ይላሉ፡፡» «ይኸንን አደረግህ ዝም አልሁህ እኔ እንዳንተ እሆን ዘንድ ጠረጠርህ እዘልፍሃለሁ በፊትህም አቆማለሁ፡፡» መዝ 73፡9-11 ምዕ 50፡21EDA 158.2

    «ተመልሼም ዓይኖቼን አነሳሁ፣ እነሆ አንድ በራሪ የመጽሐፍ ጥቅል አየሁ፡፡ ይህ በምድር ፊት ሁሉ ላይ የሚወጣው እርግማን ነው የሚሰርቅ ሁሉ በርሱ ላይ በዚህ በኩል እንደተፃፈው ሁሉ ይጠፋል፡፡ በሀሰት የሚምልም ሁሉ በርሱ ላይ በዚያ በኩል እንደተፃፈው ሁሉ ይጠፋል፡፡ እኔ አስወጣዋለሁ፣ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወደሚሰርቀውም ቤት በሐሰትም በስሜ ወደሚምለው ቤት ይገባል፡፡ በቤቱም ውስጥ ይኖራል እርሱንም እንጨቱንና ድንጋዩንም ይበላል፡፡» ዘካ 5፡1-4EDA 158.3

    በእያንዳንዱ ክፉ አድራጊ ላይ የእግዚአብሔር ሕግ ይፈርድበታል፡፡ ያንን ቃል ይንቅ ይሆናል ማስጠንቀቂያውንም ጥሶ መሄድ ይፈልግ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ይህ ሁሉ በከንቱ ነው፡፡ ምክንያቱም ይከተለዋልና11 ራሷ እንድትሰማ ታደርጋለች፡፡ ሰላሙን ታጠፋበታለች፡፡ ራሷን ከፍ ካላደረጓት እስከመቃብር ታሳድደዋለች፡፡ ራሷን ከፍ ካላደረጓት እስከመቃብር ታሳድደዋለች፡፡ በፍርድ ቀን ትመሰክርበታለች፡፡ ነፍስና ሥጋና በምትበላ በማትረካ እሳት ይቃጠላል፡፡EDA 158.4

    «ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ሰውስ ስለነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል ?» ማር 8፡36-37EDA 158.5

    ይህ ጥያቄ በእያንዳንዱ ወላጅ በእያንዳንዱ መምህር በእያንዳንዱ ተማሪ ወጣትም ሆነ ሽማግሌ በእያንዳንዱ ሰብዓዊ ፍጡር በሚገባ ሊታሰብበት የሚገባ ነው፡፡ ወሰን የሌለበትን የወደፊቱን ተመልከቶ ተገቢውን የማያደርግና ለዚህኛው አጭር እድሜ ሙጥኝ ብሎ የሚኖር ሰው ምንም ዓይነት ዕቅድ ወይም ንድፍ ቢያወጣ ሕይወቱ ሞቅ ያለ ወይም የተሟላ ሊሆን አይችልም፡፡ ወጣቶች የዘለዓለሙን ግባቸውን አንድ በአንድ አስልተው እንዲያልሙ ይማሩ፡፡ መሠረተ ሐሳቦችን እንዲመርጡና የዘለዓለም ንብረቶች የሆኑትን እንዲይዙ አስተምሯቸወ፡፡ «ሌላ የማይቀርብበት ብልም በማያጠፋበት ብልም በማያጠፋበት፡፡ በሰማያት የማያልቅ መዝገብ» ለራሳቸው መሠረት ይጥሉ ዘንድ «የአመፃ ገንዘብ ሲያልቅ በሰማይ ቤት፡፡» የሚቀበሉ ጓደኞች እንዲኖራቸው፡፡ ሉቃ 12፡33 ምዕ16፡9EDA 159.1

    ይኸንን የሚያደርጉ ሁሉ በዚህ ዓለም ላይ ላለው ሕይወት ብቻ ከፍተኛውን ዝግጅት የሚያደርጉ ናቸው፡፡ በምድር ላይ በሚኖረው ሕይወት የባሕሪይ መሻሻልና መከበር ያላሳየ ሰው በሰማይ መዝገብ ሊኖረው አይችልም፡፡EDA 159.2

    «እግዚብሔርን መምሰል ግን የአሁኑንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው ለነገር ሁሉ ይጠቅማል፡፡» 1ኛ ጢሞ 4፡8EDA 159.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents