Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
ሥነ - ትምህርት - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  ምዕራፍ 19—ታሪክና ትንቢት

  «ከጥንት ጀምሮ ይኸንን ማን ገለጠ? እኔ ጌታ
  አይደለሁምን? ሌላም አምላክ የለም፡፡»
  EDA 192.1

  ሰዎች ካላቸው መጽሐፍት ሁሉ እጅግ ጥንታዊና ከሁሉም በበለጠ ታሪክን አጠቃልሎ የያዘ መጽሐፍ ቢኖር መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው፡፡ ከዘለዓለማዊው የእውነት ፏፏቴ ትኩስ የሚመጣ ሲሆን በዘመናት ሁሉ በንጽህና ይቀመጥ ዘንድ የመለኮት እጅ ጠብቆታል፡፡ ገና ጥንት በጣም ሩቅ በነበረው፤ የሰው ልጅ የሚደርስበት መስሎት በመመራመር በከንቱ በሚለፉበት እጅግ ጥንታዊ በሆነው ዘመን ሁሉ ላይ ያበራል፡፡ የምድርን መሠረት ባስቀመጠና ሰማያትን በዘረጋው የእግዚአብሔር የቃሉ ኃይል ብቻ መተማመን አለብን፡፡ የሕዝቦችን አመጣጥ እውነተኛ ታሪክ ምንጭ የምናገኘው እዚህ ብቻ ነው፡፡ የዘራችን ታሪከ በሰው የትንቢት መንፈስ ተንቆ ወይም በቅድመ ውሳኔ አፃፃፍ ሳይዛባ የሚገኘው በዙህ መጽሐፍ ውስጥ ብቻ ነው፡፡EDA 192.2

  በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ በየዓመቱ የተፈፀሙ አዳዲስ የሥራ ክንውኖች የሕዝቦች እድገት የሰፋፊ ንጉሣዊ ግዛቶች አነሳስና ውድቀት በሰው ልጅ ልዩ ችሎታና ጀግንነተ የሚከናወኑ ይመስላሉ፡፡ የተፈፀሙት ድርጊቶች ሁሉ ሁኔታና መልካቸው በአመዛኙ በሰው ኃይል ብልሃትና ፍላጐት መሠረት የሚወሰኑ ይመስላሉ፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሐር ቃል ውስጥ መረጃው ወደ ጐን ይገለጥና ከበስተኋላ ወደ ላይና ዙሪያውንም በግጥማያውም በመልስ ግጥሚየውም በሰው ልጅ ፍላጐቶችና ኃይሎች እንዲሁም በምኞቶቹም ሁሉ ዘለዓለማዊ መሐሪው አምላክ ባዘጋጃቸው አካላት አማካይነት በፀጥታ ሳይሰማና በትዕግሥት የእግዚብሔርን የራሱን ፍላጐትና ዓላማዎች ሲያካሂድ ይታያል፡፡EDA 192.3

  መጽሐፍ ቅዱስ የታሪክን እውነተኛ ፍልስፍና ይገልጣል፡፡ በነኛ ተወዳዳሪ በሌላቸው ውበትና የዋህነት በተሞሉ ቃላት የሐዋሪያው ጳውሎስ ብልህ አነጋገር ለአቴና ሰዎች ሲገልጽ የሰው ዘርን የፈጠረበትና ሕዝቦችንም በምድረ ላይ እየተራቡ የበተነበትን ዓላማ አስምጧል፡፡ «የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጠረ ለሚኖሩበት ስፍራ ዳርቻ መደበላቸው፡፡» የሐዋ ሥራ 17፡26-27 እግዚአብሔርን የሚፈልግ ሰው ቢኖር «ወደ ቃል ኪዳኑም እስራት አስገባችኋለሁ» ሕዝ 20፡37 ሰውን ሲፈጥር ምድር በሙሉ በፍጡራን እንድትሞላና የእርሱም ሕያው መሆን ለራሳቸውና እርስ በራሳቸውም በረከት እንዲሆን ለፈጣሪአቸውም ክብር ይሆን ዘንድ ዓላማው ነበር፡፡ ፍላጐታቸው ወይም ፈቃዳቸው የሆነ ሁሉ ራሳቸውን በዚህ ዓላማ ለይተው እንዲያስቀምጡና የግል መታወቂያቸው እንዲሆን ማድረግ አለባቸው፡፡ ሰለ እነሱም እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል፡፡ «ምስጋናዬን እንዲናገሩ ለእኔ የመረጥሁት ሕዝብ የመረጥሁትን ሕዝቤን አጠጣ ዘንድ በምድረበዳ ውሃን በበረሀም ወንዞችን ሰጥቻለሁ፡፡ የምድር አራዊት የከብሩኛል፡፡» ኢሳ 43፡21EDA 193.1

  እግዚአብሔር በሕጉ ውስጥ እውነተኛውን የሕዝቦችና የግል ብልጽግና መሠረት የሆኑ መርሆችን አስምሮባቸዋል፡፡ «ጥበባችሁና ማስተዋላችሁ ይህ ነውና» አለ ሙሴ የእግዚአብሔርን ሕግ ለእስራኤላዊያኑ ሲገልጽ «ይህ ነገር ሕይወታችሁ ነው እንጂ ለእናንተ ከንቱ ዓይደለምና፡፡» ዘዳ 4፡6፡ 32፡47 ስለዚህም ለእስራኤላዊያን የተረጋገጡላቸው በረከቶች ከሰፊው ሰማይ በታች ለሌላው ሁሉ ለእያንዳንዱ ሕዝብና ለእያንዳንዱ ግለሰብ በተሰጠው ሁኔታ ዓይነትና መጠን ለሁሉም እንደዚያው ነው፡፡EDA 193.2

  በዚህ ምድር ላይ በእያንዳንዱ ገዥ እጅ የተሠራበት ስልጣን ሁሉ ከሰማይ ተከፍሎ የተሰጠ ነው፡፡ የእያንዳንዱ ሰው ውጤት የሚመሠረተው በተሰጠው ስልጣንና በስልጣን አጠቃቀሙ ላይ ነው፡፡ በእያንዳንዱ ሰው የመለኮታዊ ጠባቂ ኃይል ቃል «አንተ ግን አላወቅኸኝም፡፡» ይላል ኢሳ 45፡5 ጥንት ለናቡከደነጾር የተነገሩ ቃላት ለእያንዳንዱ ሰው ትምህርት ናቸው፡፡ «የደህንነትህ ዘመን ይረዝም እንደ ሆነ ምክሬ ደስ ያሰኝህ ኃጢአትህንም በጽድቅ፣ በደልህንም በድሆች በመመጽወት አስቀር፡፡» ዳን 4፡27EDA 194.1

  እነኝህ ነገሮች ለማስተዋል «ጽድቅ ሕዝብን ከፍ ከፍ ታደርጋለች፡፡» እንዲሁ «ዙፋን በጽድቅ ይፀናልና» «በቸርነትም ይበረታል፡፡» ምሳ 14፡34 ምዕ 16፡12 ምዕ 20፡28 እነኝህን መሠረተ ሐሳቦች ለማስተዋል፡ በርሱ ኃይል ውስጥ ሲገለጡ ሥራቸውን ለመገንዘብ «ነገስታትን ያፈልሳል ነገሥታትን ያስነሳል፡፡» ዳን 2፡21 ይህ ኃይል ያለው በእርሱ ነው የታሪክን ፍልስፍና ማስተዋል የሚቻለው፡፡EDA 194.2

  ይህ በግልጽ ተብራርቶ የተቀመጠው በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ብቻ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ የሕዝቦችና የግለሰብ ብርታት በአጋጣሚ ዕድሎች ወይም ባላቸው ሀብት ንብረት መሣሪያና ምቾት የመነጨ እንዳልሆነ ወይም በጉራ እንደሚናገሩት ታላቅነታቸው ከራሳቸው ኃይል የሚመነጭ እንዳልሆነ ያሳያል፡ ፡ የእግዚአብሔርን ሐሳብ አሟልተው ለማሳካት በፈፀሙት መጠን የሚሠፈር ነው፡፡EDA 194.3

  ለዚህ እውነታ ጥሩ መግለጫ የሚሆንን በጥንታዊ ባቢሎን የሚገኝ ታሪክ ነው፡፡ ለንጉሡ ለናቡከደነጾር እውነተኛው የሕዝብ መንግሥት በአንድ ግዙፍ እጅግ ትልቅ የሆነ ዛፍ ተመስሎ ቁመቱ «እስከ ሰማይ ድረስ መልኩም እስከ ምድር ሁሉ ዳርቻ ድረስ ታየ፡፡ ቅጠሉም የተዋበ ነበረ ፍሬውም ብዙ ነበር፡፡» በጥላውም ሥር ብዙ የሜዳ አራዊት ይኖሩበት ነበር፡፡ በየቅርንጫፎቹም የሰማይ ወፎች ይኖሩበት ነበር፡፡ (ዳን 4፡11፡12) ይህ ምስል የሚያሳየው የእግዚአብሔርን ሐሳብ የሚፈጽሙ መንግሥታት ባህሪይን ነው፡፡ ሕዝባቸውን የሚጠብቁ የሚንከባከቡና የሚገነቡ መንግሥታትን ባሕሪይ ነው፡፡EDA 194.4

  እግዚአብሔር ባቢሎንን ይኸንን ዓላማ አሟልታ ትፈጽም ዘንድ እጅግ ከፍ አደረጋት፡፡ ሕዝቧም በብልጽግና ተሞልቷል፡፡ ከዚያ በፊት ከነበሩት የትኛውም ለስተካከሏት ባልቻሉበት ሁኔታ እጅግ ከፍተኛ ደርጃ እስከምትደርስ ድረስ በሐብትና በጉልበት ገነነች፡፡ በትክክል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በመንፈስ ምልክት የተባለላትን ሆነች፡፡ «የወርቅ ራስ» ዳን 2፡38EDA 195.1

  ነገር ግን ንጉሡ ያን ያክል ከፍ ከፍ እንዲል ያደረገውን ኃይል መገንዘብ አልቻለም፡፡ ናቡከደናጾር በልቡ ከነበረው ትዕቢት የተነሳ እንዲህ አለ፡፡ «ይህች እኔ በጉልበቴ ብርታት ለግርማየ ክብር የመንግሥት መኖሪያ እንድትሆን ያሠራኋት ታላቂቱ ባቢሎን አይደለችምን? » ዳን 4፡30EDA 195.2

  የሕዝብ ጠባቂ በመሆን ፈንታ ባቢሎን ጨካኝ ጨቋኝ ሆነች፡፡ የመንፈስ ቃላት በእስራኤል የነበሩ መሪዎች የጭካኔና ስግብግብ የአጋባሽነት ገጽታቸውን ስዕል የባቢሎንን እና ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ የነበሩ የሌሎች መንግሥታትን ውድቀት ምስጢር ገልጧል፡፡ «ጮማውን ትበላላችሁ ጠጉሩንም ትለብሳላችሁ የወፈሩትን ታርዳላችሁ በጐቹን ግን አታሰማሩም፡፡ የደከመውን አላፀናችሁትም የታመመውንም አላከማችሁትም የተሰበረውንም አልጠገናችሁትም የባዘነውንም አልመለሳችሁትም የጠፋውን አልፈለጋችሁትም በኃይልና በጭቆናም ገዛችኋቸው፡፡» ሕዝ 34፡3-4፡፡EDA 195.3

  ለባቢሎን ገዥ የመለኮታዊ ጠባቂው ቃል እንዲ ሲል መጣለት፡፡ እነሆ ንጉሥ ሆይ አለ «መንግሥት ከአንተ ዘንድ አለፈች፡፡ ተብሎ ለአንተ ተነግሯል፡፡» ዳን 4፡31፡፡EDA 196.1

  «አንች ድንግል የባቢሎን ልጅ ሆይ ውረጂ በትቢያም
  ላይ ተቀመጪ... ያለ ዙፋን በመሬት ላይ ተቀመጪ...
  የከለዳዊያን ሴት ልጅ ሆይ.. ከዚህ በኋላ
  የመንግሥታት እመቤት አትባይምና ዝም ብለሽ
  ተቀመጪ ወደ ጨለማም ውስጥ ግቢ፡፡» ኢሳ 47፡1-5
  ... «አንቺ በብዙ ውሃ አጠገብ የተቀመጥሽ በመዝገብ
  የበለፀግሽ ሆይ... ፍፃሜሽ ደርሷል፡፡» «እግዚአብሔርም
  ሰዶምንና ገሞራን ባፈረሰ ጊዜ እንደ ነበረው
  የመንግሥታት ክብር የከለዳዊያንም ትዕቢት ጌጥ
  ባቢሎን እንዲሁ ትሆናለች፡፡» «የጃርት መኖሪያ
  የውኃም መቋሚያ አደርጋታለህ፡፡ በጥፋትም
  መጥረጊያ እጠርጋታለሁ ይላል እግዚአብሔር
  የሠራዊት ጌታ፡፡» ኢሳ 13፡19፡14፡23
  EDA 196.2

  እያንዳንዱ ሕዝብ ወይም ወደ መደረክ የመጣ ብሔረ በምድር ላይ የራሱን ቦታ እንዲይዝና «ቅዱስ የሆነውን ጠባቂ» ዓላማዎች አሟልቶ ይፈጽም እነደሆነ ይታይ ዘንድ ለራሱ ዕድል ተፈቅዶለታል፡፡ ትንቢት በዓለም ላይ የነበሩ ትልልቅ ግዛት የነበራቸው ኃያላን መንግሥታት ውድቀት የባቢሎንን የሜዶንና የፋርስን፣ የግሪክ የሮም አነሳስና ውድቀት ተከታትሎ ተመልክቷል፡፡ በእነዚህም እንደ ሆነ ሁሉ ከነዚህ ባነሱ ደካማ መንግሥታትም ጭምር እንደዚሁ ታሪክ አንድ ነገር ደጋግሞ አሳይቷል፡፡ እያንዳንዳቸው የየራሳቸው የሙከራ ጊዜ ነበራቸው፡፡ ሁሉም በየተራቸው ወደቁ፡፡ ክብራቸውም ተገፈፈ፡፡ ኃይላቸው ተለያቸው፡፡ በቦታቸውም ሌላው ተተካ፡፡EDA 196.3

  ሕዝቦት የእግዚአብሔርን መርሆች ሲቃወሙ ይህ ተቃውሞአቸውም በራሳቸው ላይ ጥፋታቸውን ሲያፋጥን በዚያው ጊዜ ውስጥ የሚገለጠው የመለኮት የበላይ ገዥነት ዓላማዎች በእንቅስቃሴዎቻቸው ውስጥ ሁሉ ይሠራ እንደ ነበረ ነው፡፡EDA 197.1

  ይህ ትምህርት በሚያስገርም ምስል ተመስሎ ለነብዩ ሕዝቅኤል በከለዳዊያን ምድር በስደት በነበረ ጊዜ ተሰጥቶታል፡፡ ራእዩ የመጣለት ሕዝኤል በሐዘንና በጭንቀት ትዝታዎች ተውጦ በነበረበት ሰዓት ነው፡፡ ከአባቶቹ አገር ተነጥሎ ወጥቶ ነበረ፡፡ የየሩሳሌም ሕዝብ በኃጢአት ጠፍቷል፡፡ ነቢዩ ራሱ ወደዚያች የሥልጣን ጉጉትና ጭካኔ ወደ ነገሰባት አገር ሲመጣ እንደ እንግዳ ሆኖ ነበር፡፡ እያንዳንዱ እሱ የሚጨብጠው እጅ ሁሉ በአምባገነንነትና በስህተት የተሞላ ነበር፡፡ ነፍሱም አዘነች፡፡ ቀንና ሌሊትም አለቀሰ፡፡ ለእሱ የተሰጡት ምልክቶች ግን ከምድራዊ ገዥዎች በላይ አንድ ኃይል መኖሩን ይገልጣሉ፡፡EDA 197.2

  በከባር ወንዝ ዳርቻ ላይ ሕዝቅኤል ከወደ ሰሜን የመጣ የአውሎ ነፋስ ድምጽ ሰማ፡፡ «... አውሎ ነፋስና ታላቅ ደመና የሚበርቅም እሳት መጣ በዙሪያውም ፀዳል በመካከልም በእሳቱ ውስጥ እንደሚብለጨለጭ የወርቅ ምስያ ነበር፡፡» አንዱ ሌላውን አቋርጦ የሚሄድ የሚመሥል ጥቂት ሠረገላዎች ነበሩ፡፡ እነሱም በአራት ሕያዋን የሚንቀሳቀሱ ነበሩ፡፡ ከዚህም ሁሉ በላይ «በራሳቸውም ላይ ካለው ጠፈር በላይ የሰንፔር ድንጋይ የሚመስል የዙፋን አምሳያ ላይ ነበረ በዙፋኑም አምሳያ ላይ እንደ ሰው መልክ አምሳያ ነበረ፡፡» «በክሩቤልም ከክንፎቻቸው በታች የሰው እጅን መሳይ ታየ፡፡» ሕዝ 1፡4-26 ምዕ 10፡8 የሠረገላዎቹ አሠራር የተወሳሰበ ነው፡፡ በድንገት ሲያዩአቸው እንደ ነገሩ የተውተበተበ ምስቅልቅል ነገር ይመስላሉ፡፡ ሲጓዙ ግን በተስተካከለ ፍፁማዊ ቅንጅት ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ከኪሩቤልም ክንፎች ሥር ባሉ እጆች የሚመሩና የሚኖሩ የሰማይ ሕያዋን ሠረገላዎቹን ያንቀሳቅሱ ነበር፡፡ ከእነሱ በላይ በሰፒየር ዙፋን ላይ ዘለዓለማዊ የሆነው እርሱ ነበር፡፡ ከዙፋኑ በላይ ዙሪያውን ቀስተ ዳመና ነበረ፡፡ ይህም የመለኮት የምህረት ምልክት ነው፡፡EDA 197.3

  የሰረገላው ውስብስብ እንቅስቃሴ ከኪሩቢየም ክንፎች ሥር እንደሚመራ ሁሉ የሰው ልጆች ውስበስብ ሥራም እንደዚሁ በመለኮት ቁጥጥር ሥር ናቸው፡፡ ከሕዝቦች ብጥብጥና ቀውስ ከኪቢየም በላይ የሚቀመጠው እርሱ የዚህን ምድር ጉዳይ ይምራል፡፡EDA 198.1

  አንዱ በሌላው እየተተካ የተመደበላቸውን ጊዜና ቦታ ይይዙ የነበሩ ሳያስቡት ትርጉሙንም ለራሳቸው ሳያውቁት እውነት ይመሰክሩ የነበሩ መንግሥታት ታሪክ ዛሬ ለእኛ ይናገረናል፡፡ በዛሬው ዓለም ውስጥ ለእያንዳንዱ ሕዝብና ለእያንዳንዱ ግለሰብ እግዚአብሔር በታላቁ ዕቅድ ውስጥ ቦታ አስቀምጦለታል፡፡ ዛሬ ግለሰቦችና ሕዝቦች እጁ አንዳችም ዓይነት ስህተት በማይሠራው አምላክ ሚዛን እየተመዘኑ ነው፡፡ ሁሉም በራሳቸው መርጫ የመጨረሻ ግባቸውን እየወሰኑ ነው፡፡ እግዚአብሔርም ያሰበው ነገር ይፈፀም ዘንድ አጠቃላይ ሁሉን ነገር እየተቆጣጠረ ነው፡፡EDA 198.2

  ታላቁ «እኔ ነኝ» የሚለው አምላክ በቃሉ ውስጥ መልክት ያደረገበት ትሪክ የትንቢትን ሰንሰለት ጫፍ ለጫፋ አንድ ላይ በማያያዝ ከቅድመ ዓለም ጥንት ወደ ፊትም እስከ ዘለዓለም ድረስ ዛሬ ያለንበትን የዘመናትን ሂደት ቅደም ተከተልና ወደ ፊትም ምን እንደሚጠበቅ ይነግረናል፡፡ እንደሚፈፀም በትንቢት የተነገረለት ጉዳይ ሁሉ እስከ አሁን ዘመናችን ድረስ የሆነውና እየሆነ ያለው ሁሉ በታሪክ ገጾች ላይ ተመልክቷል፡፡ ወደ ፊትም የሚመጣውም እንደዚሁ ሥርዓቱን ጠብቆ ይፈፀል፡፡EDA 198.3

  የመጨረሻው የዓለም መንግሥታትና ምድራዊዩ ግዛት ሁሉ የሚያከትምበት ሁኔታ በእውነት ቃል ውስጥ በግልጽ ተነግሯል፡፡ ለእስራኤል የመጨረሻ ንጉሥ እግዚአብሔር በቃሉ በትንቢት ሲናገረው እንዲህ የሚል መልዕክት ሰጥቷል፡EDA 199.1

  «መጠምጠሚያውን አውልቅ ዘውዱንም አርቅ የተዋረደውን ከፍ አድርግ ከፍ ያለውንም አዋርድ ባድማ ባድማ ባድማ አደርጋትለሁ፡፡ ፍርድ ያለው እስኪመጣ ድረስ ለእርሱ እሰጣታለሁ፡፡» ሕዝ 21፡26-27EDA 199.2

  ከእስራኤል ላይ የተወሰደው ዘውድ በተከታታይ ለባቢሎን ሜዶንና ፋርስ ለግሪክ ለሮም መንግሥታት ተሰጠ፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል «ይህች ደግሞ አትሆንም ፍርድ ያለው እስኪመጣ ድረስ ለእሱ እሰጠዋለሁ፡፡»EDA 199.3

  ያ ጊዜ በእርሱ እጅ ውስጥ ያለ ነው፡፡ ዛሬም የጊዜው ምልክቶች አንድ ታላቅ ጉዳይ የሚፈፀምበት ደጃፍ ላይ መድረሳችን ይገልፃሉ፡፡ በዚህ ዓለም ላይ ያለው ማንኛውም ነገር ሁሉ እኛን በመቀስቀስ ላይ ነው፡፡ልከ የርሱ መምጣት እንደ ተቀረበ በዚያ ትንሽ ቀደም ብሎ የመድህንን መምጣት የሚያመለክት ትንቢት እፊታችን ላይ በዐይናችን ሥር ሲፈፀሙ እናያለን፡፡ «ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ ይህ ሊሆን ግድ ነውና... ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሳል፣ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፡፡ ማቴ 24፡6፡7EDA 199.4

  ያሁኑ ጊዜ ሕያው የሆነውን ሰው ሁሉ በሐሳብ የሚያጥለቀልቅ ነው፡፡ ገዥዎችና የመንግሥት ባለ ሥልጣኖች በየደረጃው የኃላፊነት ቦታ የያዙ የሚያስቡ በማንኛውም መደብ ውስጥ ያሉ ሴቶችና ወንዶች በዙሪያችን በየዕለቱ የሚከናወኑ ነገሮች ላይ አትኩረው ይገኛሉ፡፡ በየሕዝቦቹ መካከል ያለው ግንኙነትና የተራዘሙ ያለዕረፍት የሚካሄዱ ነገሮችን በንቃት ይከታተላሉ፡፡ በዓለም ላይ የሚፈፀሙ የየዕለቱን ጉዳዮች ዕድገት በአንክሮ ያጤናሉ፡፡ አንድ የሚገነዘቡት ነገርም አለ፡፡ ይኸውም ወሳኝ የሆነ አንድ ታላቅ ጉዳይ ሊፈፀም እንደ ተቃረበ ይረዳሉ፡፡ ዓለም እጅግ በሚደንቅ ቀውጢ ጫፍ ላይ መሆኗን፡፡EDA 199.5

  አሁን ዓለምን የሚያደባልቀውን የጦርነት ነፋስ መላዕክት ይዘውታል፡ የሚመጣው መዓት ማስጠንቀቂያ ለዓለም ሳይነገር በፊት ዓለምን እንዳይመታት ተይዟል፡፡ ነገር ግን ማዕከሉ በዓለም ላይ ሊፈነዳ ተጠቅልሎ ተቃርቦአል፡፡ እግዚአብሔር መለአክቱ ነፋሱን እንዲለቁት ባዘዘ ጊዜ በምንም ዓይነት ብዕር ሊገልጽ የማይችል ሁኔታ ይከሰታል፡፡EDA 200.1

  የእነዚህን ነገሮች ትክክለኛ ገጽታ የሚያሳየን መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው፡፡ በእሱም ውስጥ በዚች ዓለማችን ታሪክ ተላቅና የመጨረሻ ትዕይንት ጥላቻውን አስቀድመው የዘረጉ ትርኢቶች መቃረባቸውን የሚገልፀው ድምጽም ዓለምን የሚያንቀጠቅጥና የሰዎችንም ልቦና በፍርሃት የሚጥሉ ነገሮች ተገልፀዋል፡፡EDA 200.2

  «እነሆ እግዚአብሔር ምድርን ባዶ ያደርጋታል፡፡ ባድማም ያደርጋታል፡፡ ይገለብጣትማል፡፡ በርሷም የተቀመጡትን ይበትናል፡፡ ... ሕጉን ተላልፈዋልና ሥርዓቱንም ለውጠዋልና፡፡ የዘለዓለሙንም ቃል ኪዳን አፍርሰዋልና ስለዚህም መርገም ምድርን ትበላለች በእርሷም የተቀመጡ ይቀጣሉ፡፡ የከበሮው ሐሴት ቀርቶአል የደስተኞች ድምጽም ዝም ብሏል፡፡ የመሰንቆው ደስታ ቀርቶአል፡፡» ኢሳ 24፡1-8 EDA 200.3

  «የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና ለቀኑ ወዮ! እርሱም ሁሉን ከሚችል አምላክ ዘንድ እንደ ጥፋት ይመጣል፡፡ ….. ዘሩ በምድር ውስጥ በሰበሰ እህሉ ደርቋልና ጐተራዎቹ ባዶ ናቸው፡፡ እንስሶቹ እጅግ ጮኹ የላምም መንጐች መሰማሪያ የላቸውምና ተጠራሩ የበግም መንጐች ጠፍተዋል፡፡» …. «በለሱም ጠውልጐአል፣ ሮማኑና ተምሩ እንኩቶውም የምድርም ዛፎች ሁሉ ደርቀዋል ደስታም ከሰው ልጆች ዘንድ ርቆአል፡፡» እዮኤል 1፡15-18‚12፡፡EDA 201.1

  «…… ልቤ በጣም ታምሞአል በውስጤም ልቤ ታውኮብኛል፡፡ ነፍሴ ሆይ የመለከትን ድምጽና የሰልፍን ውካታ ሰምተሻልና ዝም እል ዘንድ አልችልም፡፡ መከራ በመከራ ላይ ተጠርቷል ምድርም ሁሉ ተበዝብዛለችና፡፡»EDA 201.2

  «ምድሪቱንም አየሁ እነሆም ባዶ ነበረች አንዳችም አልነበረባትም፤ ሰማያትንም አየሁ፣ ብርሃንም አልነበራቸውም፡፡ ተራሮችን አየሁ እነሆም ተንቀጠቀጡ ኮረብቶችም ሁሉ ተናወጡ፡፡ አየሁ፣ እነሆም ሰው አልነበረም የሰማይ ወፎች ሁሉ ሸሽተው ነበር፡፡ አየሁ፣ እነሆም ፍሬአማ እርሻ ምድረ በዳ ሆነች ከተሞችም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፊት ከጽኑ ቁጣው የተነሳ ፈርሰው ነበር፡፡ ኤር 4፡19‚20‚23-26፡፡EDA 201.3

  ወዮ! «ያ ቀን ታላቅ ነውና እርሱንም የሚመስል የለምና፣ ያ የያዕቆብ መከራ ዘመን ነው፣ ነገር ግን ከእርሱ ይድናል፡፡» ኤር 30፡7፡፡ ሕዝቤ ሆይ ና ወደ ቤትህም ግባ ደጅህን በኋላህ ዝጋ ቁጣ እስኪያልፍ ድረስ፡፡» ኢሳ 26፡20EDA 201.4

  «አቤቱ አንተ ተስፋዬ ነህና ልዑልን መጠጊያህ አደረግህ
  ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም መቅሰፍትም ወደ
  ቤትህ አይገባም፡፡» መዝ 91፡9‚10
  EDA 201.5

  «የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ተናገረ፡፡ ከፀሐይ
  መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ምድርን
  ጠራት፡፡ ከክብሩ ውበት ከጽዮን፡፡ …… እግዚአብሔር
  ግልጥ ሆኖ ይመጣል፣ አምላካችን ይመጣል ዝምም
  አይልም፡፡»
  EDA 202.1

  «በላይ ያለውን ሰማይን ምድርንም በሕዝቡ ለመፍረድ
  ይጠራል፡፡ …. ሰማያት ጽድቁን ይናገራሉ እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና፡፡» መዝ 50፡1-3፣ 50፡4-፡፡
  EDA 202.2

  «የጽዮን ልጅ ሆይ፣ ….. እግዚአብሔር ከጠላቶችሽ ይቤዥሻል፡፡ አሁንም ርኩስ ትሁን ዓይናችንም በጽዮን ላይ ይይ የሚሉ ብዙ አህዛብ በአንች ላይ ተሰብስበዋል፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔርን አሳብ አያውቁም ምክሩንም አያስተውሉም፡፡» «እኔ ጤናህን እመልስልሃለሁ ቁስልህንም እፈውሳለሁ ይላል እግዚአብሔር፡፡» «እነሆ የያዕቆብን ድንኳን ምርኮ እመልሳለሁ ለማደሪያውም እራራለሁ፡፡ ሚክ 4፡10-12 ኤር 30፡17‚18EDA 202.3

  «በዚያም ቀን እነሆ አምላካችን ይህ ነው ተስፋ
  አድርገነዋል ያድነንማል እግዚአብሔር ይህ ነው፡፡ ጠብ
  ቀነዋል በማዳኑ ደስ ይለናል ሐሴትም እናደርጋለን
  ይባላል፡፡»
  EDA 202.4

  «ሞትን ለዘላለም ይውጣል፡፡ …. የሕዝቡንም ስድብ ከምድር ሁሉ ላይ ያስወግዳል እግዚአብሔር ተናግሮአልና፡፡» ኢሳ 25፡8‚9EDA 202.5

  «ጽዮንን ተመልከት ዐይኖችህ የሰላም ማደሪያ ….. እየሩሳሌምን ያያሉ ካስማውም የማይነቀል አውታሩም ሁሉ የማይጠበስ የማይወገድ ድንኳን» «እግዚአብሔር ፈራጃችን ነው እግዚአብሔር ሕግን ሰጪያችን ነው፡፡» እግዚአብሔር ንጉሣችን ነው፡፡» ኢሳ 33፡20-22፡፡EDA 202.6

  «ለድሆች በጽድቅ ይፈርዳል ለምድርም የዋሆች በቅንነት ይበይናል፡፡» ኢሳ 11፡4፡፡EDA 203.1

  ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔር አሳብ ሙሉ ለሙሉ ይፈፀማል፡፡ የመንግሥቱ ዋና መሠረታዊ ሐሳቦችም ከፀሐይ በታች ባሉ ሁሉ ይከበራሉ፡፡EDA 203.2

  «ከዚያ በኋላ በምድር ውስጥ ግፍ በዳርቻሽም ውስጥ ጉስቁልናና ቅጥቃጤ አይሰማም ቅጥርሽን መዳን በሮችሽንም ምስጋና ብለሽ ትጠሪያለሽ፡፡» «በጽድቅ ትታነጺአለሽ ከግፍ ራቂ አትፈሪምም ድንጋጤም ወደ አንች አትቀርብም፡፡» ኢሳ 60፡18 54፡14፡፡EDA 203.3

  እነዚህ ታላላቅ ትዕይንቶች የተገለጡላቸው ነቢያት የነገሮቹን አስፈላጊነት ለማስተዋል ተመኝተው ነበር፡፡ እነሱም «ስለእናንተም ስለሚሰጠው ፀጋ ትንቢት የተናገሩት ነቢያት ስለዚህ መዳን ተግተው እየፈለጉ መረመሩት በእነርሱም የነበረ የክርስቶስ መንፈስ ስለ ክርስቶስ መከራ …. በምነ ወይም እንዴት ባለ ዘመን እንዳመለከተ ይመረምሩ ነበር፡፡ ….. እናንተን እንጅ ራሳቸውን እንዳላገለገሉ ተገለጠላቸው ይኸንም ነገር መላዕክቱ ሊመለከቱ ይመኛሉ፡፡» 1ኛ ጴጥ 1፡10-12፡፡EDA 203.4

  ለእኛ ከፍፃሜው መዳረሻ ላይ ላለነው እንዴት ዓይነት ቅጽበት ነው፡፡ ምን ዓይነት ሕያው የሆኑ ስሜትን የሚስቡ የሚመጡ ነገሮችን የሚያሳይ ሥዕላዊ መግለጫ ነው፡፡ የመጀመሪያ ወላጆቻችን እግራቸውን ከኤደን ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የእግዚአብሔር ልጆች በትኩረት የተከታተሉት፤ የጠበቁት፤ የናፈቁትና የፀለዩበት ጉዳይ ነው፡፡EDA 203.5

  በዚህ ሰዓት ፤ ከታላቁ ቀውስ መምጣት ቀደም ብሎ ከዓለም የመጀመሪያው ጥፋት በፊት እንደሆነው ሁሉ ሰዎች በሁኔታው ይገፋፉና በደስታ ይዋጣሉ፡፡ በሚታየውና አላፊ በሆነው ነገር ተከብበው፤ የማይታየውንና ዘለዓለማዊውን ማየት አልቻሉም፡፡ ተጠቅመውባቸው ወዲያውኑ ለሚጠፉ ነገሮች የማይጠፋውን ዘለዓለማዊ ሀብት በከንቱ መስዋዕትነት አሳልፈው ይከፍላሉ፡፡ አእምሮአቸው መነሳሳት አለበት ፤ ስለ ሕይወት ያላቸው አመለካከትም መስፋት ያስፈልገዋል፡፡ ከዓለማዊው የሕልም ድካም ነቅተው መበርታት ያስፈልጋቸዋል፡፡EDA 203.6

  በቅዱስ መጽሐፍ በግልጽ እንደ ተቀመጠው፣ ሕዝቦች አነሳስና ውድቀት፣ በውጪ የሚታይ ዓለማዊው ግርማ ሞገስና ክብር ብቻውን ምን ያክል ዋጋ የለሽ እንደ ሆነ መማር ያስፈልጋቸዋል፡፡ ባቢሎን ፣ ያ ሁሉ እጹብ ድንቅ የሚያበራ ውበቷና የነበራት ኃይል ፤ እንደዚያ ዓይነት ከዚያ ወዲህ በዓለማችን ታይቶ የማይታወቅ፤ ኃይሏና እጅግ ድንቅ ውበቷ በዚያ ዘመን ለነበሩ ሰዎች የማያልፍና ዘለዐለማዊ ይመስላቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ያች ባቢሎን እንዴት ሆና ነው የጠፋችው፤ ፍጹም አለፈች፡፡ እንደ «ሣር አበባ» ረገፈች ጠፋች፡፡ እግዚአብሔር መሠረት ያላደረገ ነገር ሁሉ ይጠፋል፡፡ በእርሱ ዓላማ የተያዘና የርሱን ባሕሪ የሚገልጽ ሰው ብቻ ነው ብዙ መቆየት የሚችለው፡፡ ዓላማችን የሚያውቀው ፀንቶ የሚኖር የእርሱ መርህ ብቻ ነው፡፡EDA 204.1

  እነኝህን ታላላቅ እውነቶች ነው አረጋዊያንና ወጣቶች መማር የሚያስፈልጋቸው፡፡ የእግዚአብሔርን ሐሳብና አሠራር በሕዝቦች ታሪክና ስለሚመጡ ነገሮች በተሰጠው መግለጫ፤ የሚታዩትንና የማይታዩትን ነገሮች እውነተኛ ፋይዳቸውን በመገመት፣ የሕይወት ዕውነተኛው ዓላማ ምን እንደ ሆነ እንማር ዘንድ፤ የጊዜውን ነገሮች በዘለዓለማዊው ነገር ብርሃንነት እናያቸው ዘንድ፣ በእውነተኛውና በተቀደሰው ሁኔታቸው እንጠቀምባቸው ዘንድ ማጥናት ያስፈልገናል፡፡ ስለዚህም የእርሱን መንግሥት መርሆዎች እዚህ በመማርና የእሷም አገልጋዮችና ዜጐች በመሆን ለእርሱ መምጣት ዝግጁ ሆነን ከእርሱ ጋር ወደ እሷ እንድንገባ ማጥናት ያስፈልገናል፡፡EDA 204.2

  ያ ቀን እጃችን ውስጥ ነው፡፡ ስለዚህም ትምህርቱን ለመከታተል፣ መከናወን ላለበት ሥራ ፣ ለሚታየው የባሕሪ ለውጥ የቀረው ጊዜ አጭርና ቅጽበታዊ ነው፡፡EDA 205.1

  «እነሆ የእስራኤል ቤት ፣ ይህች የሚያያት ራዕይ ለብዙ ዘመን ናት፣ እርሱም ለሩቅ ወራት ትንቢት ይናገራል ይላሉ፡፡ ስለዚህ በላቸው፣ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል የምናገረው ቃል ይፈፀማል እንጅ ከቃሌ ሁሉ ደግሞ የሚዘገይ የለም፣ ይላል እግዚአብሔር፡፡» ሕዝ 12፡27‚28EDA 205.2

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents