Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    መግቢያ

    ይህ “ወደ ክርስቶስ የሚመራ መንገድ» (Steps To Christ) የተባለው መጽሐፍ አማርኛን ጨምሮ ከ140 ቋንቋዎች በላይ የተተረጎመ መጽሐፍ ሲሆን ይህንን መጽሐፍ የጻፉት ወ/ሮ ኤለን ጂ. ኋይት ልዩ የሆነ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ የነበራቸው እ.ኤ.አ ከ 1827-1915 ዓ.ም. የኖሩ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነበሩ፡፡ክየመ 5.1

    ወ/ሮ ኤለን ጂ. ኋይት በሕይወት ዘመናቸው ከ 5,000 በላይ የሚሆኑ አጫጭር ጽሑፎችንና 26 መጽሐፎችን ጽፈዋል፡፡ በዓለማችን የጽሑፍ ታሪክ ከተዘረዘሩት ሴት ደራሲዎች ውስጥ መጽሐፎቻቸው በብዙ ቋንቋዎች በመተርጎማቸው የመጀመሪያውን ቦታ የያዙ ሴት ደራሲ ሲሆኑ፣በጽሑፋቸውና በአገልግሎታቸው በዓለም አቀፍ ደረጃ በብዙ ሚሊዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች መንፈሳዊ ሕይወት አዎንታዊ ለውጥን በማምጣት ታላቅ አስተዋጽኦ የነበራቸው ናቸው፡፡ክየመ 5.2

    የወ/ሮ ኤለን ጂ. ኋይት ጽሑፎች በተለያዩ ርዕሶች ዙሪያ ላይ ያተኮሩ ሲሆን ከእነርሱም አንዳንዶቹ፡- ሃይማኖት፣ ትምህርት፣ ጤና፣ ማህበራዊ ኑሮ፣ወንጌልን ማስፋፋት፣ ትንቢት፣ የህትመት ሥራ አስፈላጊነት፣ የትክክለኛ አመጋገብ ምክሮች እንዲሁም የስራ አመራር ናቸው፡፡ክየመ 5.3

    ይህ በእጅዎ የያዙት መጽሐፍ ከ 100 በላይ ለሚሆኑ ዓመታት የሰዎችን ሕይወት በመለወጥ ታላቅ ሚና ተጫውቷል፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ከሚገኙት ምክሮችና መመሪያዎች ብዙ አንባቢያን መጽናናትንና ተስፋን አግኝተዋል፡፡ እንዲሁም በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ የክርስቶስ ተከታዮች የእምነት ጉዟቸውን በደስታና በድፍረት እንዲጓዙ ይህ መጽሐፍ ረድቷቸዋል፡፡ክየመ 5.4

    ዛሬም እርስዎ፣ ለነፍስ ጥማት ብቸኛ አርኪ ወደ ሆነው ወደ ክርስቶስ የሚያመላክተውን ይህንን መጽሐፍ በማንበብ በረከትን እንዲያገኙ ተጋብዘዋል፡፡ክየመ 5.5

    ያዕቆብ ኃጢአቱ ከእግዚአብሔር እንደለየው ካስተዋለ በኋላ ፍርሃት ውጦት ሳለ እንቅልፉ መጥቶበት በተጋደመ ጊዜ “ሕልምን አለመ፣ እነሆም መሰላል በምድር ላይ ተተክሎ፣ ራሱም ወደ ሰማይ ደርሶ ነበር» ዘፍ. 28፡12፡፡ ያዕቆብ በምድርና በሰማይ መካከል የሚያገናኘውን መሰላል ተመለከተ፡፡ በመሰላሉ ጫፍ ላይ ከቆመውም የመጽናናትና የተስፋ ቃል ተላከለት፡፡ ይህ ሰማያዊ ራዕይ ይህንን መጽሐፍ በሚያነቡ ሁሉ ሕይወት ውስጥ እንዲደገም ምኞታችን ነው፡፡ክየመ 5.6

    አሳታሚዎች

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents