Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በእግዚአብሔር መተማን

    የእንጀራው ተአምር በእግዚአብሔር እንድናምን ይረዳናል፡፡CLAmh 139.6

    ክርስቶስ አምስት ሺህ ሕዝብ ሲመግብ ምግብ አልነበረውም፡፡ የሚሸኝበት አልነበረውም፡፡ ከልጆችና ከሴቶች ሌላ አምስት ሺህ ሰዎች በምድረ በዳ ነበሩ፡፡ ሕዝቡንም እንዲከተሉት አልጋበዛቸውም ነበር፡፡ ከእርሱ ጋር መዋል ስለፈለጉ ሳይጋበዙ ወይም ሳይታዘዙ ተከተሉት፡፡ ግን ቀኑን ሙሉ ሳይበሉ ሲዳምጡት ስለዋሉ መራባቸውንና መድከማቸውን አወቀ፡፡ ከቤታቸው ርቀው ይገኙ ነበር፤ ከዚያም በላይ መሸ፡፡ ብዙዎቹ ምግብ የሚገዙበት ገንዘብ አልነበራቸውም፡፡CLAmh 140.1

    ስለ እነርሱ 40 ቀናት የጾመላቸው ጌታ ጾመኛ ሆነው ወደየቤታቸው እንዲሄዱ አልፈለገም፡፡ የእግዚአብሔር ጸጋ ክርስቶስን ከነበረበት ደረጃ አደረሰው፡፡ የሕዝቡን ፍላጎት ለማርካት ምክንያት እንዲገኝ በአብ አመነ፡፡ የጭንቅ ጊዜ ሲገጥመን በእግዚአብሔር ማመን አለብን፡፡ እንድ ድንገተኛ አጋጣሚ ሲያጋጥመን የማያቋርጥ ምንጭ ያለው አምላክ እንዲረዳን መጠየቅ አለብን፡፡CLAmh 140.2

    በዚያ ተዓምር ጊዜ ክርስቶስ ከአብ ተቀበለ፤ ለደቀመዛሙርቱ አስረከባቸው፤ እነርሱ ደግሞ ለሕዝቡ አሳለፉ፡፡ ሕዝቡም እርስ በርሳቸው ተቀባበሉ፡፡ የክርስቶስ ተከታዮች የሆኑ ሁሉ የሕይወትን እንጀራ ከእርሱ ተቀብለው ለሌሎች ማካፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ደቀመዛሙርቱ ክርስቶስን ከሕዝቡ ጋር የሚያገናኙ አስተዋዋቂዎች ናቸው፡፡CLAmh 140.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents