Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    4—የዘመናዊ ቤተሰብ ምሳሌ

    ወንጌል አስገራሚ የሆነ የሕይወት ችግር አቃላይ ነው፡፡ ትምህርቱን ብንከተል ብዙ ችግር ስለሚያቃልልልን ብዙ ስህተት ከመሥራት እንድናለን፡፡ ዘላለማዊውንና አላፊውን ነገር ለይተን እድናውቅና ዘላለማዊነት ያለውንም ነገር ለማግኘት እንድንጥር ያስተምረናል፡፡ ትዳር የማቋቋም ኃላፊነት ያለባቸው ሁሉ ይህ ዓይነት ትምህርት ያሻቸዋል፡፡ ከፍ ወዳለው ዓላማ ከማነጣጠር መመለስ የለባቸውም፡፡ የዚህ ዓለም ቤታችን የሰማዩ ቤት ምሳሌና ለሰማዩ ቤት መዘጋጃ መሆኑን ማስታወስ ይገባቸዋል፡፡ ሕይወት ወላጆችም ሆኑ ልጆች ለሰማዩ ኑሮ የሚሰለጥኑበት ትምህርት ቤት ነው፡፡ ቤት የሚሰራበት ቦታ በሚመረጥበት ጊዜ በዚህ ሐሳብ መመራት ያስፈልጋል፡፡ በብልጽግና ምኞት፣ በአለባበስ ዓይነትና (ፋሽን) በኅብረተሰብ ልምድ አለመገደድ ነው፡፡ ሊታሰቡ የሚገባቸው ግን ንጽህና፣ ጤንነትና ጠቃሚነት ናቸው፡፡CLAmh 17.4

    በመላው ዓለም በየከተማው አመጽ እየበዛ ሔዷል፡፡ በየቦታው ዝሙትና ገንዘብ ማባከን እየበዛ ሄዷል፡፡ ወንጀል በዝቷል፡፡ በየቀኑ ስርቆት፣ ነፍስ መግደል፣ የራስን ሕይወት ማጥፋትና ሌላም ወንጀል መደረጉን አንሰማለን፡፡CLAmh 18.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents