Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ክርሰቶስ ስጦታን ያበረክታል

    ደቀመዛሙርቱ የሱስ “ስጧቸው ይብሉ” ብሎ ሲያዝ በአእምሯቸው ትዝ ያላቸው አስቸጋሪው ነገር ሁሉ ነው፡፡ “ወደ መንደር ሄደን ምግብ እንግዛ እንዴ?” ብለው ጠየቁ፡፡ ክርስቶስ ግን “ስጧቸው ይብሉ” ብሎ አዘዛቸው፡፡ ያላቸውን ሲያመጡለት ብሉ አላላቸውም፡፡ ለሕዝቡ እንዲያሳልፉ አዘዛቸው፡፡ ደቀመዛሙርቱ እጃቸውን ወደ የሱስ በዘረጉ ቁጥር ይሞላላቸው ነበር፡፡ ያቺ ትንሽ ምግብ ለሁሉም በቃች፡፡ ሕዝቡ በልቶ ከጠገበ በኋላ የሱስና ደቀመዛሙርቱ ከሰማይ የተላከውን መልካም ምግብ በሉ፡፡CLAmh 140.4

    የድሆችን የማይማንንና የተጐሳቈሉትን ችግር ስንመለከት ልባችን በትካዜ ፍላፃ ይወጋል፡፡ ለእነዚህ ደካሞች ርዳታ የምንሰጥበት ምን ኃይልና ችሎታ አለን? ብለን ራሳችንን እንጠይቃለን፡፡ ሌላ የተሻለ ሀብትና ብርታት ያለው ግለሰብ ወይም ድርጅት አይሠራውም እንዴ? ክርስቶስ “የሚበሉትን ስጧቸው” ይላል፡፡ ያላችሁን ሀብት ብርታትና ችሎታ ሥሩበት፡፡ የገብስ እንጀራችሁን ለየሱስ ስጡ፡፡CLAmh 140.5

    ንብረታችሁ በሺህ ለሚቆጠሩ ሰዎች ባይበቃም ለአንድ ሰው ይበቃል፡፡ ለክርስቶስ ስታስረክቡት ግን ለብዙ ይበቃል፡፡ እንደ ደቀመዛሙርቱ ያላችሁን ስጡ፡፡ ክርስቶስ ስጦታችሁን ያበዛዋል፡፡ በእርሱ ለሚያምኑና ቅንነት ለሚያሳዩት ዋጋቸውን ይከፍላቸዋል፡፡CLAmh 141.1

    “በጥቂት የሚዘራ በጥቂት ደግሞ ያጭዳል፤ በበረከት የሚዘራ በበረከት ያጭዳል፡፡ … በተነ ለምስኪኖችም ሰጠ ጽድቁ ለዘለዓለም ይኖራል ተብሎ እንደተጻፈ እግዚአብሔር ሁልጊዜ ብቃትን ሁሉ በነገር ሁሉ አግኝታችሁ ለበጎ ሥራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል፡፡ ለዘሪም ዘርን እንጀራን ለመብላት በብዙ የሚሰጥ እርሱ የምትዘሩትን ዘር ይሰጣችኋል፡፡ ያበረክትላችሁማል፡፡ የጽድቃችሁንም ፍሬ ያሳድጋል፡፡ በሁሉ ነገር ባለጠጎች ትሆናላችሁ፡፡ (2ኛ ቆሮንቶስ 9፡6-11)CLAmh 141.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents