Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    29—ለአገልግሎት መጠራት

    ጊዜው ጧት፤ቦታው በገሊላ ባሕር አከባቢ ነበር። የሱስና ደቀመዛሙርቱ በባሕሩ ላይ ሲንገላቱ ካደሩ በኃላ የጧት ጮራ በባሕሩና በየብሱ ላይ ሲያበራ የሰላም ምልክት አዩ፡፡ ግን ከባሕሩ ዳር ሲደርሱ ከባሕር ሞገድ የባሰ አሰቃቂ ነገር ተመለከቱ።CLAmh 164.1

    ከአንድ መካነ መቃብር አጠገብ ሁለት እብዶች ከተደበቁበት መድረፍ ብለው ቦጫጭቀው የሚጥሏቸው ይመስሉ ነበር ። እነዚያ ሰዎች ከእስር ቤት ማምለጣቸውን ለማሳውቅ የሰንሰለት ሰባራ ይጎትቱ ነበረ። አካሎቹ ቁስሎና ተላልጦ ደም ከማዝነቡም በላይ አይናቸው ፈጦ፤ጸጉራቸው ተንጨፍሮ ሰለ ነበረ ሰው አይመስሉም ነበር። አራዊት ይመስሉ ነበር። ደቀ መዛሙርቱና መሰሎቻቸው እግሬ አውጭኝ አሉ። ግን የሱስ ከእነርሱ ጋር አለመሸሹን ስላወቁ ዘውር ብለው ተመለከቱ። እርሱስ ከተውበት ቦታ አልተነቃነቀም ። የባሕርን ሞገድ ጸጥ ያሰኘ፤ ከአሁን በፊት ሠይጣንን ድል የነሣ፤አሁንም ከአጋነንንቱ ፊት አልሸሸም። ሰዎቹ ጥርሶቻቸውን እያፋጩ፤ለሀጫቸውን እያዝረከረኩ ሲቀርቡት ሲያይ የሱስ የባሕሩን ሞገድ ጸጥ ያሰኘባቸውን እጆቹን ሲያነሣ ቀጥ ብለው ቆሙ፡፡ ርኩሳኑ መናፍስት ከሰዎቹ እንዲወጡ በሥልጣን አዘዛቸው፡፡CLAmh 164.2

    ከሚያስቃዩአቸው አጋንንት የሚገላግል አዳኝ እንደደረሰላቸው ምስኪኖቹ ዕብዶች ተገነዘቡ፡፡ ምህረት ሊጠይቁ ከጌታ እግር ላይ ወደቁ፤ ግን ሊናገሩ ሲሞከሩ ሰይጣን በእነርሱ አማካይነት “እነሆ የሱስ ሆይ የእግዚአብሔር ልጅ ከአንተ ጋር ምን አለን ጊዜው ሳይደርስ ልታሰቃየን ወደዚህ መጣህን?” እያለ ይጮህ ነበር (ማቴዎስ 8፡29)CLAmh 164.3

    አጋንንቱ ከሰዎቹ እንዲወጡ ስለተገደዱ የአጋንንት ማደሪያ ሆነው የነበሩበት ሰዎች ግሩም ለውጥ አሳዩ፡፡ አእምሮአቸው ብሩህ ሆነ፡፡ የዓይኖቻቸው አገላለጥ ማስተዋል መቻላቸውን ያሰይ ነበር፡፡ ወደ ሰይጣንነት ተለውጠው የነበሩት ገጾቻቸው ባለለዛ ሆኑ፡፡ በደም የተበከሉት እጆቻቸው አረፉ፡፡ መድኃኒታቸውን ለመከተል እንደሚፈለጉም ምኞታቸውን ገለጡ፡፡ በየሱስ አጠገብ ከሆኑ የሰውነት መብታቸውን የገፈፉአቸውና እድሜ ልካቸውን ያሰቃዩአቸው አጋንንት እንደማይነኩአቸው ዋስትና እንዳላቸው አስተዋሉ፡፡CLAmh 164.4

    የሱስ ወደ ጀልባው ለመሳፍር ሲያመራ ቀርበው ተንበረከኩና የእርሱ ተከታዮች ሆነው ቃሉን የመስማት እድል እንዲያገኙ አቤት አሉ፡፡ የሱስ ግን ወደቤታቸው ተመልሰው ጌታ ያደረገላቸውን ታላቅ ነገር ለሌሎች እንዲነግሩ አዘዛቸው፡፡CLAmh 165.1

    እንዲፈጽሙት የታዘዙት ተግባር ወደ አረማውያን ቤተሰቦቻቸው ሄደው ከየሱስ ዘንድ የተቀበሉትን በረከት መናገር ነበር፡፡ ከጌታ መለየት ከባድ ሆኖ ተሰማቸው፡፡ አረማውያን ከሆኑት ያገራቸው ሰዎች ጋር ሲገናኙ ችግር ይገጥማቸዋል፡፡ ከማኀበራዊ ኑሮ ለብዙ ጊዜ ገለልተኛ ሆነው ስለኖሩ የታዘዙትን ሥራ ማከናወን የማይችሉ መስሎ ተሰማቸው፡፡ ግን ወዲያው ትእዛዙ ሲሰጣቸው ፈቃደኝነታቸውን ገለጡ፡፡ ታሪኩን ያዳረሱት በሞላው አገር እንጂ ለቤተሰቦቻቸውና ለጎረቤቶቻቸው ብቻ አልነበርም፡፡ በየሄዱበት የክርስቶስን የማዳን ኃይልና እንዴት ከታሠሩበት የአጋንንት እሥር ቤት ነጻ እንዳወጣቸው ይናገሩ ነበር፡፡ የጌርጌሶን ሰዎች ክርስቶስን ባይቀበሉትም ቅሉ በመረጡት የጨለማ ዓለም ውስጥ ተውጠው እንዲቀሩ አልተዋቸውም፡፡CLAmh 165.2

    ከእነርሱ እንዲርቅ የነገሩት ቃሉን ባይስሙ ነው። ሊቀበሉት ስላልወደዱት ሰለ የሱስ ምንም የሚያውቁት አልነበረም ።ስለዚህ በሚያዳምጡአቸው ሰዎች አማካኘነት መልእክቱን ላከላቸው።CLAmh 165.3