Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    እውነተኛ ባለ መብራት

    በያዕቆብ ጉድጓድ አጠገብ ከየሱስ ጋር የተነጋገረችው ሴት መሲህ መሆኑን እንደተረዳች ሌሎችን ሰዎች ወደ የሱስ ይዛ መጣች፡፡ ከደቀመዛሙርቱ ይልቅ ቁም ነገረኛ ወንጌላዊት መሆኗን አሳየች፡፡ ደቀመዛሙርቱ ሰማርያ ለወንጌል ስራ የሚመች ቦታ መሆኑን አላወቁም ነበረ፡፡ እነርሱ የሚያስቡት ለወደፊቱ ታላቅ ስራ ለመስራት ነበረ፡፡ ያን ጊዜ በዚያው ቦታ የደረሰ ሰብል መኖሩን አልተገነዘቡም ነበር፡፡CLAmh 166.5

    ግን ይንቋት የነበረች ሴት የከተማውን ኗሪ በሙሉ ወደ የሱስ ይዛ መጣች፡፡ የተቀበለችውን ብርሃን ለአገሯ ሰዎች አዳረሰች፡፡CLAmh 166.6

    ይቺ ሴት የተቀበልነውን እምነት ከስራ ላይ እንድናውል ታስተምራለች፡፡ ዕውነተኛ ክርሰቲያን ሁሉ ለእግዚአብሔር መንገስት የወንጌል መልዕክተኛ ነው፡፡ እግዚአብሔርን በሚገባ ራሱ ካውቀው ከሌሎች ጋር ሊያስተዋውቀ ይፈልጋል፡፡ የሚያድነውና የሚቀድሰው እውነት ልብን ፈንቅሎ ይወጣል፡፡CLAmh 167.1

    ከሕያው ምንጭ የጠጣ ሁሉ እራሱ የህይወት ፏፏቴ ይሆናል፡፡ የተቀበለውን ይሰጣል፡፡ የክርስቶስ ጸጋ በሕይወት ውሃ ጥማት ሊሞቱ የተቃረቡትን ስለሚፈውስ ዙሪያውን እንደምታለመልምና እንደምታረካ የበረሃ ምንጭ ነው፡፡ ለራሳችን ጥቅም ብቻ ከምንፍጨረጨር ይልቅ ሌሎችን ለመርዳት ብንሞከር የበለጠ እንቀበላለን፡፡CLAmh 167.2

    ወደ መድኃኒታችን በጣም ልንቀርብ የምንችለው የመዳንን የምሰራች ለሌሎች ስናበስር ነው፡፡CLAmh 167.3

    ጸጋውን ስለሚቀበሉት አምላክ እንዲህ ይላል እርሱንና በኮረብታዬ ዙሪያ ያሉትን ሥፍራዎች ለበረከት አደርጋችዋለሁ፡፡ ዝናቡን በጊዜው አወርዳለው፡፡ የበረከት ዝናብ ይሆናል፡፡CLAmh 167.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents