Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    31—እውነትን መሻት

    ምን ያህል ትግል እንዳለብን ከአሁኑ አብልጠን በጥብቅ ማወቅ አለብን፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል ጠቃሚነትና ጠላት አታሎ ከዚህ እውነት ቢያርቀን የሚደርስብንን ጉዳት መገንዘብ አለብን፡፡CLAmh 179.1

    እኛን ለማዳን የተሰዋልን ውድ መስዋዕት የኃጢአትን አደገኝነት ይገልጥልናል፡፡ በኃጢአት ምክንያት የሰው አቋም ይበላሻል፡፡ አእምሮ ይደንዝዛል፤ አሳብ ይጣመማል፡፡ ኃጢአት የሰውነትን ደረጃ ዝቅ አድርጎታል፡፡ ውጫዊ ፈተና አሳባችንን ሲስበው አረማመዳችንን ወደ መጥፎ አቅጣጫ ያዘነብላል፡፡CLAmh 179.2

    የተደረገልን መስዋዕት ፍፁም ነውና ከኃጢአት ፈጽመን መራቅ አለብን፡፡ የእግዚአብሔር ህግ ምንም ዓይነት ክፋት አያልፍም፡፡ ኃጢአትን ችላ አይልም፡፡ የወንጌል ደረጃ ከፍጽምና ሌላ ድርድር አይቀበልም፡፡ የክርስቶስን አኗኗር በህግ ፊት ሊኖር የሚገባው ፍጽምና በግልጥ ያሰየናል፡፡ “እኔ የአባቴን ትዕዛዝ ጠብቄአለሁ፡፡” አለ (ዮሐንስ 15፡10)CLAmh 179.3

    እንድናገለግልና እንድንታዘዝ የእርሱ ኑሮ አርኣያችን ነው፡፡ ልብን ሊያድስ የሚችል እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ “ስለ በጎ ፈቃዱ መፈለግን ማድረግንም በእናንተ የሚሰራ እግዚአብሔር ነው፡፡” ስለዚህ ወዳጃቼ ሆይ ሁል ጊዜ እንደታዘዛችሁትና በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁንስ አሁን ስርቅ በፍርሀትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፡፡ “(ፊልጵስዩስ 2፡12) ፡፡CLAmh 179.4

    በቀላል ጥረት የተጣመመውን ማቃናት ጠባይን ማሻሻል አይቻልም፡፡CLAmh 179.5

    ጠባይን ማሻሻል የዕድሜ ልክ ሥራ እንጂ የአንድ ቀን ወይም የአንድ አመት ብቻ ተግባር አይደለም፡፡ ራስን ለማሸነፍ የሚደረገው ጥረት የዘወትር ትግል ነው፡፡ ቅድስናን ተቀዳጅቶ ሰማይን ለመውረስ የሚያደርገው ትግል ዘለዓለማዊ ነው፡፡CLAmh 179.6

    የማያቋርጥ ጥረትና የዘወትር ትጋት ካልተደረገ በቀር በመለኮታዊ ትዕዛዝ መራመድና የድል አድራጊነት አክሊል መድፋት አይገኝም፡፡CLAmh 179.7

    የሰውን በጣም መዋረድ ለማወቅ የሚቻለው የጥንት ክብር ቦታውን ለማግኘት ትልቅ መስዋዕትነት ማስፈለጉን በመመልከት ነው፡፡ መመለሰ የሚቻለው በየጊዜው ጠንክሮ በመሥራት ነው፡፡ ካልተጠነቀቅንና በችኮላ ከሠራን በአጭር ጊዜ ውስጥ በሰይጣን ወጥመድ ውስጥ ልንገባ እንችላለን፡፡ የታሰርንበትን ሰንሰለት ሰብረን ቅዱስ ኑሮ ለመኖር ግን ረጋ ያለ አስተሳሰብና ሰፋ ያለ ጊዜ ያስፈልገናል፡፡CLAmh 179.8

    አሳቡን ማሰበና ሥራውን መጀመሩ ቀላል ሊሆን ይችላል፡፡ ግን ከፍፃሜ ለማድረስ ጠንክሮ መሥራት፤ ረዥም ጊዜ ፤ አለመሰልቸት ፤ ትዕግስት ፤ መስዋዕትነት ያሻዋል፡፡CLAmh 180.1

    ራሳችን በስሜት እንድንመራ አንፍቀድ ፤ ለአጭር ጊዜም ቢሆን መዘንጋት የለብንም፡፡ ፈተና ደጋግሞ ቢገጥመንም ካልተቋቋምነው መውደቃችን ነው፡፡ ተግባራችን ሳናከናውን ዕድሜአችን ከገፋ ለዘለዓለም መጥፋታችን ነው፡፡CLAmh 180.2

    ጳውሎስ ዕድሜውን ሁሉ ከራሱ ጋር ሲታገል ኖረ፡፡ “በየቀኑ እሞታለሁ” ይላል፡፡ (1ኛ ቆርንቶስ 15፡31) ፈቃዱና ምኞቱን በየዕለቱ ከተግባሩና ከአምላክ ፈቃድ ጋር ይጋጭበት ነበር፡፡ ቢሆንም የራሱን ፈቃድ ችላ ብሎ የእግዚአብሔርን አሟላ፡፡ “መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፤ ሩጫዬን ጨርሻአለሁ፤ ሃይማኖቴን ጠብቄአለሁ ፤ ወደፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፡፡ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፡፡ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱ ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም፡፡” (2ኛ ጢሞቲዎስ 4፡7-8)CLAmh 180.3

    የክርስቲያን ኑሮ ሰልፍና ጦርነት ነው፡፡ ጦርነቱ ማለቂያ የለውም፡፡ ትግሉ የማያቋርጥና ረዥም ነው፡፡ የሠይጣንን ፈተና ድል የሚነሳው የማያቋርጥ ሙከራ ስናደርግ ብቻ ነው፡፡ የክርስትና ጽናት የሚገኘው በማይታጠፍ መቋቋምና በጥብቅ አስተሳሰብ ነው፡፡CLAmh 180.4

    ማንም በበኩሉ ብርቱ ጥረት ካላደረገ ሊያድግ አይችልም፡፡ ሁሉም ለራሱ ካልታገለ በአንዱ ግንባር ሌላውን ሊዋጋለት አይችልም፡፡ ለትግሉ የየግል አላፊነት አለብን ኖህ ፤ ዳንኤልና ኢዮብ በምድር ላይ ቢገኙም የእነርሱ ጽድቅ ልጆቻቸውን ሊያድን አይችልም፡፡CLAmh 180.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents