Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ሊታወቅ የሚገባው ሳይንስ

    ሊታወቅ የሚገባው የክርስትና ሳይንስ አለ፡፡ ይህ ሳይንስ መሬትና ሰማይ የሚራራቁትን ያህል ፤ስፋቱ፤ጢልቀቱ ከፍታው ከተራው ሳይንስ የራቀ ነው፡፡ አእምሮአችን መገራት ፤ መማረና መሠልጠን አለበት፡፡ ምክንያቱም ለእግዚአብሔር የምንፈጽመው ተግባር በተፈጥሮ ዝንባሌያችን ልንፈጽመው የምንችለው አይደለም፡፡CLAmh 180.6

    በውርስና ባስተዳደግ የሸመትነው ክፋት መወገድ አለበት፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የክርስቶስ ደቀመዝሙር ለመሆን ዕድሜ ልክ የተማሩትን ትምህርት እርግፍ አድርጎ መተው አሰፈላጊ ይሆናል፡፡ ልቦናችን ከክርስቶስ ጋር የተሣሠረ እንዲሆን መማር አለብን፡ ፡ፈተናን ለመቋቋም የሚያስችል ልምድ ሊኖርን ይገባናል፡፡ ወደ ላይ መመልከት እንማር፡፡CLAmh 180.7

    እንደ ሰማይ የመጠቀውና ዘለዓለማዊ የሆነው የእግዚአብሔር ሥርዓት በኑሮአችን ላይ ያለውን ተፈላጊነት ማስተዋል ያስፈልገናል፡፡CLAmh 181.1

    ሥራችን፤ አነጋገራችን፤ አስተሳሰባችን ክዚህ ስርዓት ጋር የሚስማማ መሆን አለበት፡፡ ሁሉም ክርስቶስ እንደሚቀበለው ሆኖ ለእርሱ መገዛት አለበት፡፡ የከበረው የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ በአንድ ጊዜ ደርሶ አይገኝም፡፡ ድፍረት፣ ጽናት፣ ትህትና፣ ዕምንት፣ እግዚአብሔር የማዳን ኃይል መተማምን በብዙ ዘመን ልምድ የሚገኙ በረክቶች ናችው ፡፡CLAmh 181.2

    የእግዘአብሔር ልጆች ከአላማቸው መድረስ የሚችሉት በተቀደሰ ኑሮ በጸና ትጋት ነው፡፡ የሚናባክነው ጊዜ የለንም፡፡ የምህረት ደጅ መቼ እንደሚዘጋ አናውቅም፡፡ በፊታችን ዘለዓለም ተዘርግቶልናል፡፡ መጋረጃው ሊከፈት ነው ፡፡CLAmh 181.3

    ከጥቂት ጊዜ በኋላ የሚከተለው አዋጅ ይታወጃል፡፡” ዐመፀኛው ወደፊት ያምፅ፤ ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ፤ ቅዱሱም ወደ ፊት ይቀደስ፡፡ “(ራዕይ 22፡1)CLAmh 181.4

    ተዘጋጅተናል? ከሰማይ ገዢ ፤ ከህግ ሰጪው ወልድን ወደዚህ አለም ከላከው ከአብ ጋር ተዋውቀናል? የሕይወት ተግባራችንን ስንጨርስ ክርስቶስ ምሳሌያችን እንዳለው “እኔ ላደርገው የሰጠኀኝን ስራ ፈጽሜ በምድር አከበሩህ፤ ከአለም ለሰጠኀኝ ሰዎች ስምህን ገልጥሁላቸው” ማለት እንችል ይሆን? (ዮሐንስ 17 ፡ 4 - 6) ፡፡CLAmh 181.5

    የእግዚአብሔር መላእክት ከራሳችን ምኞትና ከዚህች ዓለም ሊገላግሉን ይሞክራሉ፡፡ ድካማቸውን በከንቱ አናስቀረው፡፡CLAmh 181.6

    የዘነጉ ሰዎች አስተሳሰባቸውን ይለውጡ፡፡CLAmh 181.7

    “ስለዚህ የልቡናችሀን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኖራችሁ የሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ፡፡ እንደሚታዘዙ ልጆች አስቀድማችሁ ባለማወቅ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ” ዳሩ ግን እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ብሎ ስለተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደሆነ እናንተም ደግሞ በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ፡፡” (1ኛ ጴጥሮስ 1፡ 13-16) ፡፡CLAmh 181.8

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents