Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ከርካሽ ነገር መራቅ

    በሺህ ከሚቆጠሩ ከሚያጓጉ አርዕስተ ጉዳዮች መራቅ ያስፈልገናል፡፡ አንዳንድ ነገሮች ስሜትን ቀስቅሰው ጊዜን በከንቱ ካቃጠሉ በኃላ ጥቅመ - ቢስ ሆነው ይቀራሉ፡፡ በጥብቅ የምንከተላቸውና ለማወቅ የምንሻቸው ብዙ ነገሮች ዋጋ ቢስ ናቸው፡፡ አዲስ ትምህርት - መሠረት መቀበል አዲስ ሕይወት አያስገኝም፡፡ ዕውነተኛ ነገሮችን ማወቁና መረዳቱ ብቻ ያወቁትን ከሥራ ላይ ካላዋሉት ጥቅሙ እምብዛም ነው፡፡CLAmh 182.8

    መንፈሳዊ ሕይወታችን የሚያበለጽግ ምግብ ለነፍሳችን የማቅረብ ኃላፊነት አለብን፡፡CLAmh 182.9

    “እውነት ምንድነው?” እያልን መመራመር ይገባናል፡፡ የሳይንስ ተመራማሪዎች እግዚአብሔር አምላካችን ማግኘት አቅቷቸዋል፡፡ አሁን ሊጠይቁት የሚገባ ጥያቄ “ነፍሳትን ሊያድን የሚችል እውነት ምንድን ነው?” ብለው ነው፡፡ “ስለ ክርስቶስ ምን ትላላችሁ?” የሚለው ጥያቄ መሠረት ያለው ጥያቄ ነው፡፡ የግል አዳኝህ አድርገህ ትቀበለዋለህ? ለሚቀበሉት ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ለመሆን የሚያስችል መብት ይሰጣቸዋል፡፡CLAmh 183.1

    ክርስቶስ አብን ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠላቸው በልባቸው አዲስ ስሜት እንዲፈጥር አድርጎ ነው፡፡ በእኛም ያ ቅዱስ አሳብ እንዲያድርብን ይመኝልናል፡፡ በአፈ-ታሪክ ብቻ ስለሚኖሩ ብዙዎች የክርስቶስን እውነተኛ አርአያነት አያውቁትም፡፡ ትሁት፤ ለራሱ ብቻ የማይል ሠራተኛ መሆኑን አያውቁም፡፡ የሱስን በእውነት መመልከት ያስፈልጋቸዋል፡፡ በየዕለቱ ከእኛ ጋር መሆኑን ማወቅ ያስፍልገናል፡፡CLAmh 183.2

    ራሱን በመካድና በመሥዋዕትነት ያደረገውን አርአያነት መከተል ያስፈልገናል፡፡ ጳውሎስን የሚከተለውን ሊያስጽፈው ያስቻለው አጋጣሚ ሊያገጥመን ይገባል፡፡CLAmh 183.3

    “ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ አሁን ሕያው ሁኜ አልኖርም፤ ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለእኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው፡፡” (ገላትያ 2 ፡ 20)CLAmh 183.4

    አብንና ወልድን ማወቃችን በሥራ ስንገልጥ በሰማይና በምድር በታላቅ ክብር አከበርናቸው ማለት ነው፡፡ ከትምህርት ሁሉ የላቀና የመጠቀ ዕውቀት ነው፡፡ የሰማይን ከተማ በር የሚከፍት ቁልፍ ነው፡፡ ይህን እውቀት ክርስቶስን የለበሱ ሁሉ እንዲገበዩት የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፡፡CLAmh 183.5

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents