Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በሥርአት ለመመራት ጠቃሚ ዘዴዎች

    ይህ ሁሉ የሚደርስባቸው እግዚአብሔር ስለሚመራቸው ነው፡፡ ሰውን በሥርአት ለመምራት የእግዚአብሔር ምርጥ መሣሪዎች ፈተናና እንቅፋት ናቸው፡፡ እነዚህን አሸንፎ ያለፈ ሰው ተከናወነለት ይባላል፡፡ የሰዎችን ልቦና የሚያውቀው አምላክ ጠባያቸውን ራሳቸው ከሚያውቁት አብልጦ ያውቀዋል፡፡ አንዳንዶች በደንብ ከተመሩ ለሥራው ገጣሚ የሆነ ኃይልና ችሎታ እንዳላቸው ያውቃል፡፡CLAmh 190.3

    እነዚህን ሰዎች በጥበቡ በልዩ ልዩ አጋጣሚና ቦታ በማቅረብ ያላውቁትን ስህተታቸውን እንዲያውቁ ያደርጋቸዋል፡፡CLAmh 190.4

    ጉድለታቸውን አርመው ለስራው ገጣሚ እንዲሆኑ ዕድል ይሰጣቸዋል፡፡ አብዛኛው ጊዜ እንዲነጹ በፈተና እሳት ይገርፋቸዋል፡፡CLAmh 190.5

    በፈተና እንድንጋፈጥ መደረጉ ራሱ እግዚአብሔር ከጥቅም ሊውል የሚችል ጠቃሚ ነገር በእኛ ውስጥ ማየቱን ያመለክታል፡፡ ስሙን የሚያስከብር ጠቃሚ ነገር በእኛ ውስጥ ካላየ እኛን ለምን ይፈልጋል? ወደ ማጣሪያው ምድጃ ዋጋ የሌለው ድንጋይ አይጨምርም፡፡ የሚያጠራውን ዋጋ ያለውን ማዕድን ነው፡፡ አንጥረኛው (ቀጥቃጭ) አይነቱን ለይቶ ለማወቅ ብረቱን ወደ ምድጃው ይጨምረዋል፡፡ አምላክም ስዎችን በፈተና እሳት ውስጥ የሚጨምራቸው ማንነታቸውን ለይቶ ለስራው ገጣሚ አድርጎ ለማዘጋጀት ነው፡፡CLAmh 190.6

    ሸክላ ሰሪ ሸክላውን በፈለገው ቅርጽ ይሰራዋል፡፡ በደንብ አሽቶ ይሰራዋል፡፡ አፈራርሶ ይፈጨዋል፡፡ ያርሰዋል፤ ያደርቀውማል፡፡ ሳይነካ ለተወሰነ ጊዜ ይተወዋል፡፡ ለስራ ከተዘጋጀ በኃላ የፈለገውን እቃ ይሰራበታል፡፡ ቅርጽ ይሰጠዋል፤ ይከረክመዋል፤ ይወለውለውማል፡፡ በፀሀይ ያደርቀዋል፤ በእሳትም ይተኩሰዋል፡፡ ከዚያ በኃላ ሸክላው አገልግሎት ሊሰጥ የሚችል ዕቃ ይሆናል፡፡CLAmh 190.7

    ታላቁ ጥበበኛም እኛን ይሠራናል፡፡ ሸክላ ሰሪው በሸክላው ላይ ሙሉ ሥልጣን እንዳለው ሁሉ እርሱም በእኛ ላይ ሙሉ ባለሥልጣን ነው፡፡ የሸክላ ሰሪው የስራውን ድርሻ መስራት መሞከር አያስፈልገንም፡፡ የእኛ ድርሻ ታላቁ ሰራተኛ እንደፈቃዱ እንዲሠራን ፈቃደኛ መሆን ብቻ ነው፡፡CLAmh 191.1

    “ወዳጆች ሆይ፤ በእናንተ መካከል እንደ እሳት ሊፈትናችሁ ስለሚሆነው መከራ ድንቅ ነገር እንደመጣባችሁ አትደነቁ፡፡ ነገር ግን ክብሩን ሲገልጥ ደግሞ ሐሴት እያደረጋችሁ ድስ እንዲላችሁ በክርስቶስ መከራ በምትካፈሉበት ልክ ድስ ይበላችሁ፡፡” (1ጴጥሮስ 4፡12-13) ፡፡CLAmh 191.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents