Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የኑሮ አላማ

    ስንበደል ወይም የተበደልን ሲመስለን ነገሩን ነክሰን መያዝ የለብንም፡፡ ከሁሉ አብልጠን መፍራት የሚገባን ራሳችንን ነው፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ካልተጋራ አጉል ሥጋዊ ፍላጎት የበለጠ ጠባይን የሚበክል ነገር የለም፡፡ ራሳችንን ከማሸነፍ የላቀ ታላቅ ድል የትም አይገኝም፡፡ ስሜታችን በቀላሉ ሊጎዳ አያስፈልግም፡፡ ዋና አሳባችን ስሜታችን ወይም ስማችን መንከባከብ ሳይሆን ነፍሳትን ማዳን መሆን ይገባዋል፡፡ ነፍሳትን ለመመለስ ታጥቀን ከተነሣን በእኛና በሌሎች መካከል ያለውን መጠነኛ አለመግባባት ዋጋ አንሰጠውም፡፡ ሌሎች ስለ እኛ የፈለጉትን ቢያስቡ፤ ያደረጉትን ቢያደርጉብን ከክርስቶስ ጋር ያለንን አንድነት ማቃወስ የለበትም፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ መሆናችንንም መዘንጋት አይገባንም፡፡CLAmh 200.5

    “ኃጢያት አድርጋችሁ ስትጎስሙ ብትታገሱ ምን ክብር አለበት? ነገር ግን መልካም አድርጋችሁ መከራ ስትቀበሉ ብትታገሱ ይህ ነገር በእግዚአብሔር ዘንድ ምስጋና ይገባዋል፡፡” (1ኛ ጴጥሮስ 2፡20) ፡፡CLAmh 200.6

    አትበቀሉ፡፡ እንደተቻላችሁ መጠን መግባባትን የሚያስወግደውን ነገር ሁሉ አርቁ፡፡ ክፉን ሁሉ አስወግዱ፡፡ ከሌሎች ጋር ለመስማማት ብላችሁ ለኀሊናችሁ ያልመሰላችሁን አትሥሩ እንጂ የቻላችሁትን ያህል ሥሩ፡፡CLAmh 200.7

    “እንግዲ መባህን በመሠውያው ላይ ብታቀርብ በዚያም ወንድምህ በአንተ ላይ አንዳች እንዳለ ብታስብ፤ በዚያ በመሠውያው ፊት መባህን ትተህ ሂድ አስቀድመህም ከወንድምህ ጋር ታረቅ፤ በኋላም መጥተህ መባህን አቅርብ፡፡” (ማቴዎስ 5፡23-24) ፡፡CLAmh 201.1

    መጥፎ ቃላት ቢሰነዘርባችሁ አጻፋውን አትመልሱ፡፡ “የለዘበች ምላስ ቁጣን ታበርዳለች” የሚለውን አትርሱ፡፡ (ምሳሌ 15፡1) ፡፡ “ዝምታ ወርቅ ነው” ይባል የለ! ለተቆጣ ሰው መልስ መስጠት ቁጣውን ማባባስ የሚሆንበት ጊዜ አለ፡፡ ግን ቁጣውን ማባባስ በዝምታና በለሰለሰ መንፈስ ሲቀበሉት ቶሎ ይበርዳል፡፡CLAmh 201.2

    የስድብ ናዳ ሲውርድባችሁ ቃለ እግዚአብሔርን አስታውሱ፡፡ የእግዚአብሔርን ተስፋ በልባችሁና በአእምሮአችሁ አኑሩት፡፡ ስማችሁን ሰው ቢያጠፋው ወይም በሐሰት ብትከሰሱ ቁጣን በቁጣ በመመለስ ፋንታ “ክፉ አያሸንፋችሁ ፤ ክፉን በበጎ አሸንፉ እንጂ” የሚለውን መልካም ቅዱስ ምክር አስታውሱ፡፡ (ሮሜ 12፡21) ፡፡CLAmh 201.3

    “መንገድህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ፤ በእርሱም ታመን እርሱም ያደርግልሃል፡፡ ጽድቅህን እንደ ብርሃን ፍርድህንም እንደ ቀትር ያመጣል፡፡” (መዝሙር 37፡5፣6) ።CLAmh 201.4

    “ነገር ግን የማይገለጥ የተከደነ፤ የማይታወቅም የተሠወረ ምንም የለም፡፡” (ሉቃስ 12፡2) ፡፡CLAmh 201.5

    “በራሳችን ላይ ሰውን አስረገጥኸን፡፡ በእሳትና በውኃ መካከል አለፍን፤ ወደ ዕረፍት አውጣኸን፡፡” (መዝሙር 66፡12) ፡፡CLAmh 201.6

    ወደ ክርስቶስ በመመልከት ፈንታ አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች እንዲያዝኑልንና እንዲረዱን እንማጸናለን፡፡ ግን አምላክ በጥበቡ የተመካንባቸው ሰዎች እንዲተውን ያደርጋል፡፡ ይህን የሚያደርግበት ምክንያት በሰው መመካትና ስጋ በለበሰ ላይ መተማመን ከንቱ መሆኑን ሊያስረዳን ነው፡፡ በፍጹም ልባችን በእግዚአብሔር አምላክ እንመን፡፡ አምላካችን ልንገልጠው የማንችለውን የልባችን ትካዜ ያውቀዋል፡፡CLAmh 201.7

    ዙሪያ ሲጨልምብንና ግራ ሲገባን “እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም ፤ በኋላ ግን ታስተውለዋለህ” ያለውን የጌታ ቃል እናስታውስ፡፡ (ዮሐ 13፡7) ፡፡CLAmh 201.8

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents