Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ሌሎችን የሚያበረታታ ተግባር

    ሌሎችን በመተቸትና በመኮነን ፋንታ “እንድድን ራሴ መጣር አለብኝ፤ ሊያድነኝ ከሚፈልገው ጋር ተባብሬ በትጋት መሥራት ይገባኛል፡፡ ከሰውነቴ ክፋትን ማስወገድ ይኖርብኛል፡፡ በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት መሆን አለብኝ፤ ስህተትን ድል መንሣት ይገባኛል፡፡ ስለዚህ የተሳሳቱትን ተስፋ በማስቆረጥ ፋንታ አጽናናቸዋለሁ” በል፡፡CLAmh 206.4

    እርስ በእርሳችን መረዳዳትን ችላ እንላለን፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የሥራ ባልደረቦቻችን ርዳታና ማበረታቻ እንደሚያስፈልጋቸው እንረሣለን፡፡ እንደማትተውዋቸውና እንደምታዝኑላቸው አረጋግጡላቸው፡፡ በፀሎታችሁ ርዷቸው፡፡ እንደምትረዷቸው ይወቁ፡፡CLAmh 206.5

    የእግዚአብሔር ልጆች ነን የሚሉ ሁሉ ወንጌላዊያን መሆናቸውን አውቀው ሰው ሳይመርጡ ማንንም ማነጋገር እንዳለባቸው አይርሱ፤ ጨዋና ባለጌ፤ ትሁትና ኩሩ፤ አማኝና ከሃዲ፤ የተማረና መሃይም፤ ድሃና ሀብታም መኖሩ አይጠረጠርም ፡፡ በዚህ ዓይነት የተለያዩትን ሰዎች ሁሉ በአንድ ዓይነት አቀራረብ ብቻ መቅረብ አይቻልም፡፡ ግን ሁሉም ርኀራኄና ፍቅር ያሻቸዋል፡፡ እርስ በእርስ በመወያየት አስተሳሰባችን ይስላል፡፡ በሰብአዊ ወንድማማችነት በመዛመዳችን አንዱ የሌላውን ድጋፍ እንፈልጋለን፡፡CLAmh 206.6

    ክርስትና በዓለም ውስጥ የሚሠራጨው በማኀበራዊ ኑሮ አማካይነት ነው፡፡ መለኮታዊ ብርሃን የተገለጠለት ሁሉ ወንድም ቢሆን ሴት መንገዳቸው ለጨለመባቸው ማብራት አለበት፡፡ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የሚካሄድ የማህበራዊ ኑሮአችን ነፍሳትን ወደ ክርስቶስ መመለስ አለበት፡፡ ክርስቶስን የተቀበለ ሰው ብቻ ለግሉ የሚደሰትበት የተቀበረ መዝገብ መሆን የለበትም፡፡ ክርስቶስ በውስጣችን እንደሚፈለፍል ምንጭ ሆኖ ወደ እኛ የሚመጡትን ሁሉ ማርካት አለበት፡፡CLAmh 207.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents