Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የእግዚአብሔርን አምሳል ማደስ

    ክርስቶስ የሥራውን ውጤት በቅድሚያ አውቆት ነበር፡፡ ምድራዊ ኑሮው በችግርና በፈተና የተሞላ ቢሆንም ድካሙ በከንቱ አለመሆኑን ስላወቀ ተጽናና፡፡ ህይወቱን ለሰው ዘር አሳልፎ በመስጠት የእግዚአብሔርን አምሳል በሰው ዘንድ እንደሚያድስ አወቀ፡፡ ከትቢያ አንስቶ፤ ጠባያችንን በጠባዩ ልክ አርሞ (አርቆ) በክብሩ አስዋበልን፡፡CLAmh 208.3

    ክርስቶስ የድካሙን ዋጋ ስለተመለከት ተደሰተ። የዘለዓምን ርዝመት አማካይነት የኃጢአት ስረየት ያገኙትን የማያቋርጥ ደስታ ተመለከተ። እርሱ ስለ ኃጢአታቸው ቋሰለ፤ ስለ አመጻቸውም ተቀጠቀጠ።CLAmh 208.4

    የመዳናቸው ተስፋ በእርሱ ላይ ነበር፤ በእርሱ ቁስል እነርሱ ተፈወሱ። የዳኑት የበጉና የሙሴን መዝሙር ሲዘምሩ ስማ። መጀመሪያ የደም ጥምቀት መሆን ቢገባውም፤ የኃጢአት ሽክም በንጽሑ ላይ መጫን ቢኖርበትም፤ የሞት ጥላ ቢያንዣብበትም፤ በፊቱ ስለ ተደነቀነው ደስታ መስቀልን ሊሽከምና ውርደትን ሊንቅ ቻለ።CLAmh 208.5

    ይህን ደስታ ተከታዮቹ ሁሉ ይካፍሉታል። የዘለዓለም ደሰታ ክብሩ የላቀ ቢሆንም ዋጋችን ለፍርድ ቀን ብቻ የተቆጠበ አይደለም። ዛሬም በዚህ ኑሮአችን በሃይማኖት በአዳኛችን እንደሰታለን። እንደ ሙሴ የማታየውን መታገሰ አለብን።CLAmh 208.6

    አሁን ቤተ ክርስቲያን ታጥቃ ተነስታለች። በጣዖታት በወደቀ በጨለማ ዓለም ውሰጥ እንገኛለን፤ ከጦርነት በኃላ ድል የምንቀዳጅበት ቀን ይደረሳል።CLAmh 208.7

    የእግዚአብሔር ፈቃድ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁ በምድር መሆን አለበት። የዳኑት ወገኖች ከሰማይ ሕግ በቀር ሌላ ሕግ አያውቁም። ሁሉም የደስታንና የምስጋና ልብስ ለብሰው የክርስቶስን ጽድቅ ተጎናጽፈው አንድ ቤተስብ ይሆናሉ። ተፈጥሮ ሁሉ በሙሉ ለአምላኩ ይስግዳል፤ ጌታን ያመልካል። በአለም ላይ የሰማይ ብርሃን ያንጸባርቃል። የጨረቃ ብርሃን እንደ ፀሐይ ብርሃን ይሆናል ። የፀሐይ ብርሃን ደግሞ ከአሁን ሰባት እጥፍ ይሆናል። ዓመታት በደስታ ያልፋሉ። አብና ወልድ ከእግዲህ ኃጢአት የለም፤ ሞትም ከእግዲህ አይሆንም ብለው ሲያውጁ የጧት ከዋክብት ይዘምራሉ፤ የእግዚአብሔር ልጆችም ከደስታ የተነሳ ይጮሃሉ።CLAmh 208.8

    እነዚህን ያልታዩ ታሪካዊ ነገሮች ለማየት መሞከር ያስፈልገናል፡፡ የጊዜንና የዘለዓለማዊነትን ጠቃሚነት የምናውቀው እንዲህ ሲሆን ነው፡፡ ሌሎች ከፍተኛ ኑሮ እንዲኖሩ ልናግባባቸው የምንችለው በዚህ መንገድ ብቻ ነው፡፡CLAmh 209.1

    እግዚአብሔር “ከእኔ ጋር ወደ ተራራው ኑ” ይለናል፡፡ ሙሴ እሥራኤሎችን በመምራት የአምላክ መሣሪያ ከመሆኑ በፊት ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር በተራራው አጠገብ ብዙ ዓመታት ቆይቷል፡፡ መልእክቱን ወደ ፈርዖን ከማድረሱ በፊት በሚነደው ቁጥቋጦ ውስጥ ከመልአኩ ጋር መነጋገር ነበረበት፡፡ በሕዝቡ ስም የእግዚአብሔር ሕግ ከመረከቡ በፊት ክብሩን እንዲያይ ወደ ተራራው ጠራው፡፡ በጣዖት አምላኪዎች ላይ ከመፍረዱ በፊት በአለት ላይ ቆሞ እግዚአብሔር “መሐሪ፤ ሞገስ ያለው፤ ባለ ብዙ ቸርነትና እውነት፤ በደለኛው ከቶ የማያነጻ ብዬ እግዚአብሔር ስም በፊትህ አውጃለው፡፡” (ዘፀዓት 34፡6-7) አለው፡፡ (ዘፀዓት 30፡19)CLAmh 209.2

    በእሥራኤል ላይ የነበረበትን የኃላፊነት ቀንበር ከትከሻው አውርዶ ከመሞቱ በፊት ፤ እግዚአብሔር ወደ ጲስጋ ተራራ ወስዶ የተስፋይቱን ምድር ክብር አሳየው፡፡CLAmh 209.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents