Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የፀሎት ሰዎች

    ብዙ ሰዎች ከፈተና ላይ የሚወድቁት እግዚአብሔርን መሪያቸው ስለማያደርጉ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነታችን ከተቋረጠ ተጋለጥን ማለት ነው፡፡ የራሳችሁ መልካም አስተሳሰብና ቅን ፍላጎት ክፉን እንድትቋቋሙ አያስችላችሁም፡፡ የፀሎት ሰዎች መሆን አለባችሁ፡፡ ፀሎታችሁ እንደነገሩ፤ አልፎ አልፎ ሲያጋጥም የሚፀለይ ብቻ ሳይሆን ልባዊ፤ የዘወትር፤ የማያቋርጥ መሆን አለበት፡፡CLAmh 210.2

    ለፀሎት ሁል ጊዜ መንበርከክ አያስፈልግም ብቻችሁን ስትራመዱ፤ የዕለት ሥራችሁን ስታካሄዱ ከአምላክ ጋር መነጋገርን ልመዱ፡፡ ብርታት እንድታገኙ፤ እውቀት እንዲገለጥላችሁና ብርሃን እንዲበራላችሁ ሁል ጊዜ የህሊና ፀሎት አድርሱ፡፡ ንግግራችሁና እስትንፋሳችሁ ሁሉ ፀሎት ይሁን፡፡CLAmh 210.3

    በእግዚአብሔር ከማመን ፈጽሞ አናፍርም፡፡ በልባችንና በኑሮአችን ክርስቶስ ካለ አያሰጋም፡፡ ክርስቶስ ከእኛ ጋር ከሆነ ክፉ ነገር ሁሉ ከአጠገባችን ይሸሻል፡፡ መንፈሳችን መንፈሱን ሲመስል በአሳብና በዓላማ አንድ እንሆናለን፡CLAmh 211.1

    ያዕቆብ ከኃጢአትና ከደካማነት ተነስቶ የእግዚአብሐርን ልዑል ሊሆን የቻለው በፀሎት አማካይነት ነው፡፡ እናንተም አሳባችሁ የፀና፤ ዓለማችሁ ከፍ ያለ ከሆነ የመጣ ቢመጣ ለእውነት የምትቆሙ ሰዎች ልትሆኑ የምትችሉት በዚሁ መንገድ ነው፡፡CLAmh 211.2

    ችግር፤ ጭንቀትና ሥራ የሌለው አይገኝም፤ ግን ሥልጣን እንደገና ኃላፊነት እንደከበደ መጠን የየሱስ ተፈላጊነት በዚያው ልክ ይጨምራል፡፡CLAmh 211.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents