Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    አሁንም ሰፊ በረከት

    ትሁትና ገር ስንሆን እግዚአብሔርን ልናይ እንችላለን፡፡ በረከት ሊሰጠን ፈቃደኛ የሚሆን ያለፈውን ምህረቱንና ቸርነቱን ያወቅንለት እንደሆንና ያመሰገነው እንደሆን ነው፡፡ ሙሉ በሙሉ ለሚያምኑበት ሁሉ የፈለጉትን አንድ ሳይቀር ይፈፀምላቸዋል፡፡ እግዚአብሔር እኛ ልጆቹ ምን ያህል ርዳታ እንደሚያስፈልገንና ሰበአዊን ፍጡር ለመጥቀም ምን ያህል በረከት እንደሚያሻን ያውቃል፡፡CLAmh 212.4

    የራሳችን ጠባይ ለማሳመርና ሌሎችንም እንዲባርኩ ለማድረግ የሚያስፈልገንን ኃይል ያድለናል፡፡ ለእኛና በእኛ በኩል የሚፈፀመውን ሥራ ለእግዚአብሔር መተው ነው እንጂ በራሳችን መመካት የለብንም፡፡ የምትሠሩት ሥራ የራሳችሁ ሥራ አይደለም ፤ ግን የጌታን ሥራ ታከናውናላችሁ፡፡ ፈቃዳችሁን ለእርሱ አስገዙ ፤ ከራሳችሁ ምንም አትቆጥቡ ፤ ምንም አታመንቱ፡፡ በክርስቶስ ነፃ መሆን ምን ማለት እንደሆነ ዕወቁ፡፡CLAmh 212.5

    ያወቅነውን እውነት በሥራ ካላሳየን በቀር በየሰንበቱ ቃለ እግዚአብሔርን ማዳመጥ፤ መጽሐፍ ቅዱስን ከገበታ እስከ ገበታ ማንበብ ፤ እያንዳንዱን ቁጥር ቃል በቃል ማብራራት ለእኛም ሆነ ለሌሎች አይጠቅመንም፡፡ አስተሳሰባችን፤ ፈቃዳችን፤ ፍላጎታችን በእግዚአብሔር ቃል የተገታ መሆን አለበት፡፡ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የእግዚአብሔር ቃል የኑሮአችን መመሪያ ይሆናል፡፡CLAmh 212.6

    አምላክን ርዳን ብላችሁ ስትለምኑት በረከቱን ከመድኀን እንደምትቀበሉ በማመናችሁ እርሱን ማክበራችሁ ነው፡፡ ከጠየቅን ኃይልና ጥበብ እናገኛለን፡፡CLAmh 212.7

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents