Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    እግዚአብሔርና ታሪክ

    ሊነወር የማይገባው የታሪክ ትምህርት አለ፡፡ በነቢያት ትምህርት ቤት ይሰጡ ከነበሩት ትምህርቶች አንዱ መንፈሳዊ ታሪክ ነበር፡፡ እግዚአብሔር የምድርን ነገሥታት እንዴት ይቆጣጠር እንደነበር ያጠኑ ነበር፡፡ ዛሬም እግዚአብሔር የዓለም መንግስታት እንዴት እንደሚቆጣጠር ማጥናት ይገባናል፡፡ በታሪክ የትንቢትን መፈጸም ማየትና በመሻሻል እንቅስቃሴዎች እግዚአብሔር እንዴት እንደረዳና ነገሥታትም ለመጨረሻው ተጋድሎ በመዘጋጀት ላይ እንዳሉ ማጥናት አለብን፡፡CLAmh 44.3

    የዚህ ዓይነት ጥናት ስለ ሕይወት ጠለቅና ሰፋ ያለ አስተያየት ይሰጣል፡፡ በሕይወት ውስጥ ስላለው ግንኙነትና ተደጋጋፊነት፤ በኅብረተሰብና በወገን ወንድማማችነት እንዴት በሚያስገርም አኳኋን እንደተሳሰርንና ከኅብረተሰብ የአንዱ አባል መዋረድ ወይም መጨቆን የሁሉ ጉዳት መሆኑን እንድናስተውን ይረዳናል፡፡CLAmh 44.4

    ዘወትር የሚጠናው ታሪክ ግን ስለ ሰው ድርጊት፤ በጦርነት ስላገኘው ድልና ለማግኘት እንዴት እንደተከናወነለት ነው፡፡ በሰው ድርጊት እግዚአብሔር ያለው ኃላፊነት ፈጽሞ ተረስቷል፡፡ በነገሥታት መነሣትና መውደቅ እግዚአብሔር እንዳለበት የሚገባቸው ጥቂቶች ናቸው፡፡CLAmh 45.1

    በአሁኑ ጊዜ በጣም የታወቁት እትሞች ወጣቶችን ወደ ጥፋት በሚመሩ ታሪኮች ተሞልተዋል፡፡ በዕድሜ ሕፃን የሆኑ በወንጀል ሥራ እውቀት ጎልምሰዋል፡፡ በሚያነቧቸው ታሪኮች መጥፎ ነገር ወደ መሥራት ይመራሉ፡፡ የሚያነቡትን ታሪክ በሐሳባቸው ስለሚፈጽሙት ወንጀል የመሥራትና ከቅጣት የማምለጥ ምኞት ይነሳሳባቸዋል፡፡CLAmh 45.2

    በልብ ወለድ ታሪክ ስለ መጪው ጊዜ የሚጻፈው ሁሉ ለሕፃናትና ለወጣቶች እውነት ይመስላቸዋል፡፡ አንድ ዓይነት የግዳጅ መለዋወጥ በሚተችበት ጊዜ ነፃነትን ለማግኘት ሕግን እንዴት ለማስወገድ እንደሚቻል የሚሰጠውን ልብ ወለድ መግለጫ ሲያነቡ ይህንኑ ዓይነት ድርጊት የመፈጸም ምኞት የሚያድርበባቸው ብዙ ናቸው፡፡ የሚያመቻቸው ከሆነ በልብ ወለድ ታሪኮቹ ከተጻፉት ወንጀሎች የበለጠ ለመሥራት ይመኛሉ፡፡ መጥፎ ነገር ለማድረግ በሚያደፋፍሩ ነገሮች ምክንያት ኅብረተሰብ የሞራል ውድቀት ደርሶበታል፡፡ የሕገ ወጥነት ዘር በሰፊው እየተዘራ ነው፡፡ ውጤቱ ወንጀል በመሆኑ መደነቅ የለብንም፡፡CLAmh 45.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents