Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    11—ቤተሰብን መመገብ

    ሰውነታችን የተሠራው ከምንበላው ምግብ ነው፡፡ ከሰውነት መገንቢያ ሕዋሶቻችን በየጊዜው የሚበላሹ አሉ፤ የእያንዳንዱ ብልት እንቅስቃሴ አንድ ዓይነት ቆሻሻ ይፈጥራል፤ በቆሻሻ መልክ ለሚጣለው መተኪያ የሚገኘው ከምግባችን ነው፡፡ እያንዳንዱ የሰውነት ብልት ምግብ ያስፈልገዋል፡፡ አንጎል፣ አጥንቶች፣ ሥጋና የስሜት ሥሮች (ነርቮች) ሁሉ ምግብ ያሻቸዋል፡፡ ከምግብነት ወደ ደምነት የሚደረገው ለውጥ እጅግ አስገራሚ ነው፤ ልዩ ልዩ የሆኑት የሰውነት ብልቶችም የሚገነቡት በደም አማካይነት ነው፤ ለእያንዳንዱ ነርቭ፤ ሥጋና ሕዋስ ሕይወትና ጥንካሬ የሚሰጠው መለወጥ ዘወትር ይቀጥላል፡፡CLAmh 52.5

    ለሰውነት መገንቢያ የሚያስፈልጉት ነገሮች በበለጠ የሚገኙባቸው ምግቦች መመረጥ አለባቸው፡፡ ምግብ በሚመረጥበትም ጊዜ በምግብ አምሮት መመራት አያስፈልግም፡፡ በተሳሳተ የመመገብ ልምድ ምክንያት የምግብ አምሮታችን ተበላሽቷል፡፡ ብዙውን ጊዜ ጉልበት በሚሰጥ ምግብ ፋንታ ጤና የሚያጓድልና ድካምን የሚያስከትል ምግብ እንመኛለን፡፡ በኅብረተሰብ ልምድ መመራትም ዋስትና የለውም፡፡ በየትም ቦታ የምናየው ሥቃይና ሕመም አብዛኛውን ጊዜ የሚመጣው ስለምግብ ባለው የስሕተት አስተያየት ነው፡፡CLAmh 53.1

    የተሻለ ምግብ ምን እደሆነ ለማወቅ ከተፈለገ እግዚአብሔር መጀመሪያ ለሰው የሰጠውን የምግብ ዓይነት ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ሰውን የፈጠረና ፍላጐቱንም የሚውቅ አምላክ ለአዳም የሚበላውን ዓይነት ምግብ ወሰነለት፡፡ “እነሆ መብል ይሆናችሁ ዘንድ…. ዘሩ በእርሱ ያለውን ሐመልማል ሁሉ፣ የዛፍንም ፍሬ የሚያፈራውንና ዘር ያለውንም ዛፍ ሁሉ ሰጠኋችሁ፡፡ (ዘፍ 1፡29)CLAmh 53.2

    ሰው በኃጢአቱ ምክንያት ከተድላ ገነት ወጥቶ እያረሰ መብላት በሆነበት ጊዜ “የምድርንም ቡቃያ ትበላለህ” ዘፍ 3፡18 የሚል ፈቃድ ተሰጠው፡፡CLAmh 53.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents