Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በሚገባ ምግብን ማዘጋጀት

    ብዙ ለመብላት ስለሚያደፋፍርና የምግብ አለመስማማት ስለሚያስከትል በአንድ ጊዜ ብዙ መግብ ማቅረብ ጥሩ አይደለም፡፡CLAmh 55.4

    በአንድ ማዕድ ላይ ፍራፍሬና አትክልት መብላት አይበጅም፡፡ ጨጓራና አንጀት በደንብ የማይፈጩ የሆና እንደሆነ በነዚህ ሁለት ምግቦች ምክንያት መፍዘዝና የአእምሮ ድካም ሊከተል ይችላል፡፡ ፍሬውን ለአንድ ማዕድ አትክልቱን ደግሞ ለሌላ ማዕድ ማቅረብ ይሻላል፡፡CLAmh 55.5

    ምግብ የተለያየ መሆን አለበት፡፡ በአንድ ዓይነት አኳኋን የተዘጋጀ አንድ ዓይነት ምግብ በየቀኑ መቅረብ የለበትም፡፡ ምግቡ የተለያየ የሆነ እንደሆን እየጣፈጠ ከመበላቱም በላይ ለሰውነት ተስማሚ ይሆናል፡፡CLAmh 55.6

    የምግብን አምሮት ብቻ ለማርካት መብላት ስሕተት ነው፤ ሆኖም ስለምግብ ዓይነትና ስለማዘጋጀቱ ጉዳይ ቸልተኛ መሆን አያሻም፡፡ የሚበላው ምግብ የማያስደስት ከሆነ አካላችን አይፋፋም፡፡ ምግብ በጥንቃቄ መመረጥና በብልሃት መዘጋጀት አለበት፡፡CLAmh 55.7

    ለዳቦ በጣም ተስማሚው ነጭ ስንዴ አይደለም፡፡ ውድ ከመሆኑም በላይ ለጤና ተስማሚ አይደለም፡፡ ከቀይ ስንዴ የሚገኘው ጠቃሚ ምግብነት ከነጭ ስንዴ አይገኝም፡፡ ቁርጠትንና ሌላም የጤና መጓደልን ያስከትላል፡፡CLAmh 55.8

    ሁለት ጊዜ የበሰለ ዳቦ (ዝዊባክ) በሆድ ውስጥ በቀላሉ የሚፈጭ ከመሆኑም በላይ ጣዕሙ እንዲህ አይደለም፡፡ ዳቦውን ሸንሽኖ መጠጥ እስቲል ድረስ ሞቅ ባለ ምድጃ ውስጥ ማስቀመጥ፡፡ ከዚያ በኋላ ጠየም እስቲል ድረስ በደረቅ ቦታ ማቆየት፤ ከሌላ ዳቦ ይልቅ የዚህ ዓይነት ዳቦ ሳይበላሽ ብዙ ጊዜ ሊቆይ ይችላል፡፡ ከመበላቱ በፊት ትንሽ ሞቅ ቢደረግ ጣዕሙ እንዳዲስነቱ ይሆናል፡፡CLAmh 55.9

    ባሁኑ ጊዜ ከምግብ ጋር የሚቀላቀለው ስኳር ልክ የለውም፡፡ የምግብ አለመስማማት ዋና ምክንያቱ ኬክና መሰሎቹ ናቸው፡፡ ከወተት፣ ከእንቁላልና ከስኳር ቅይጥ የሚሰሩ ምግቦች በበለጠ ጎጂዎች ናቸው፡፡ ወተትንና ስኳርን በቀጥታ አቀላቅሎ አለመጠቀም ነው፡፡CLAmh 56.1

    እንደሚገባ ያልበሰለና በቂ ያልሆነ ምግብ ደም የሚሠሩትን ብልቶች ስለሚያዳክም ደምን ያሳንሳል፡፡ መላውን የአካል ሥርዓት በማቃወስ ሕመምን፣ የነርቭ መታወክንና ቁጡነትን ያስከትላል፡፡ እንደሚገባ ባለበሰለ ምግብ ምክንያት የሚሰቃዩ ሰዎች በሺህ ይቆጠራሉ፡፡ በብዙ የመቃብር ደንጊያዎች ላይ የሚከተሉት ቃላት ሊጻፉ ይቻላል፡፡ “እንደሚገባ ባልበሰለ ምግብ ምክንያት ሞተ!” “በጨጓራው ላይ ግፍ በመስራቱ ሞተ”CLAmh 56.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents