Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ለአንባቢያን

    ኑሮ ብዙ ነገሮችን ያጠቃልላል፡፡ ከነዚህም ዋና ዋናዎቹ ጤና፣ መልካም ቤተሰብ፣ የልብ ጓደኞ፣ የአዕምሮ ሰላምና ከእግዚአብሄር ጋር መስማማት ናቸው፡፡ የኑሮአችሁ ደረጃ ምንም ዓይነት ቢሆን እነዚህን የኑሮ ጸጋዎች ማግኘት፤ ኑሮን ልትደሰቱበት፤ የተሟላ ኑሮ ልትኖሩ ትችላላችሁ፡፡CLAmh 2.1

    ግን ሊታሰብባቸው የሚገባ ነገሮች አሉ፡፡ ኑሮ የሚያስገኛቸውን መልካም ነገሮች ለማግኘት የፈለገ ሰው ሊከተላቸው የሚገባው መሠረታዊ ደንቦች አሉ፡፡ እነዚህ በዚህ መጽሐፍ ቅስጥ የተብራሩት የኑሮ ደንቦች በልዩ ልዩ ቋንቋዎች ለልዩ ልዩ ሕዝብ በቃልም በጽሑፍም አማካይነት ተዳርሰዋል፡፡ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ተጠቅመውባቸዋል፡፡CLAmh 2.2

    “የተሟላ ኑሮ” “የፈውስ አገልግለት” ከተባለ ከፍተኛ መጽሐፍ ተውጣጥቶ የተጻፈ ምርጥ መጽሐፍ ነው፡፡ ይህ መጽሐፍ ከተጠቀሰው ትልቅ መጽሐፍ የተውጣጣ እነጂ የፊተኛው መጽሐፍ ግልባጭ አይደለም፡፡CLAmh 2.3

    በደራሲዋ መልዕክት የተጠቀሱት ምርጥ ምክሮች ምን ጊዜም ቢሆን ተፈላጊነታቸው ጊዜ የማይሽረው ነው፡፡ ደራሲዋ ስለ አልኮሆልና ስለትንባሆ፤ የወላጅ ተሰሚነት፤ ስለልጅ አስተዳደግ የሰነዘረችው አስተያየት በአሁኑ ዘመን የሳይንስና የትምህርት አቋም ሊቃውነት ከደረሱበት ምርምር ጋር የሚስማማ ነው፡፡CLAmh 2.4

    የዚህ መጽሐፍ አንባብያን ይህን መጽሐፍ በማንበባቸው የኑሮን ምርጥ ነገሮች ቁልፍ አግኝተው የተሟላ ኑሮ እንደሚኖሩ ተስፋ እናደርጋለን፡፡CLAmh 2.5

    አሳታሚዎቹCLAmh 2.6

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents