Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ተዛዘኑ!

    እግዚአብሔር ምድርን በባለጸግነቱ ሞልቷታል፡፡ የምድርን መዛግብት ለሰው ልጆች ድሎት በሚሰጡ ነገሮች አትረፍርፏል፤ የመዳንን መንገድ በነፃ ከፈተልን፤ ታድይ ይህ ሆኖልን ሳለ ባል የሌላቸውን፣ የድሐ አደጎችን ፣ የበሽተኞችንና የችግረኞችን፣ የመሃይማንንና ያልዳኑትን ጩኸት ወደ ሰማይ እንዳይደርስ የምንከለክልበት ምን ምክንያት አለን?CLAmh 70.4

    ዛሬ ገንዘባቸውንና ጊዜያቸውን አምላክ በከለከለው መንገድ የሚያባክኑ ሁሉ በእግዚአብሔር ቀን ከሞተላቸው ከየሱስ ጋር ፊት ለፊት ሲተያዩ ምን ይመስሉ ይሆን? ክርስቶስ “ተርቤ ነበር አበላችሁኝም፤ ተጠምቼ ነገር አጠጣችሁኝም፤ ታረዝሁ አለበሳችሁኝም፤ ታሠርሁ፤ ታመምሁ ግን አልጠየቃችሁኝም” የሚለው እንዲህ ላሉት ሰዎች አይደለም እንዴ? (ማቴዎስ 25፡42-42)CLAmh 70.5

    ልብሳችን ውድ ያልሆነና ቀላል ቢሆንም ጥሩ ዓይነት፤ ተስማሚ ቀለም ያለው፤ ለሥራ የሚያመች መሆን ይገባዋል፡፡ ከጌጥ ይልቅ አገልግሎቱ ሊታሰብበት ይገባል፡፡ ሙቀት የሚሰጥና አካልን በሚገባ የሚከላከል ይሁን፡፡ ሰሎሞን የሚተርክላት ሴት “ለቤቷ ሰዎች ከበረዶ ብርድ አትፈራም፤ የቤትዋ ሰዎች እጥፍ ድርብ የለበሱ ናቸውና፡፡”CLAmh 70.6

    ልብሶቻችን በንጽሕና መጠበቅ አለባቸው፡፡ ቆሻሻ ልብስ ለጤና ጠንቅ ስለሆነ አካልንና ነፍስን ያጐሳቁላል፡፡CLAmh 71.1

    እላንት የእግዚአብሔር መቅደስ ናችሁ፤ ማንም የእግዚአብሔርን መቅደስ ቢያረክስ ሳይጠፋ አይተወውም፡፡” 1ኛ ቆሮ 3፡16-17CLAmh 71.2

    በምንም በኩል ቢሆን ልብስ ለጤና ተስማሚ መሆን አለበት፡፡CLAmh 71.3

    “ከሁሉም በላይ” እግዚአብሔር “ጤነኞች” እንድንሆን ይፈልጋል፡፡ ጤንነታችንም በአካል በመንፈስም የተሟላ ይሁን፡፡ ጤናችን በልብስ አለባበሳችን ሊሟላ ይችላል፡፡CLAmh 71.4

    አለባበሳችን ውበት፣ ግርማ ሞገስና ገጣሚነት ሊኖረው ይገባል፡፡ ክርስቶስ በኑሯችን እንዳንኮራና እንዳንመካ ከለከለ እንጂ የተፈጥሮን ውበት እንድንደሰትበት አደፋፍሮናል፡፡CLAmh 71.5

    ስለ መስክና ስለ አበባዎች ሲናገር የአበባን ውበት በማድነቅ “ሰሎሞን እንኳ በዚያ ሁሉ ክብሩና ባለጸግነቱ የአንዷን አበባ ያህል አላጌጠም አለ፡፡” (ማቴ 6፡29)CLAmh 71.6

    ክርስቶስ በተፈጥሮ አማካይነት የውበትን ለዛ፤ በሰማይ ዘንድ የሚሰጠውን ከፍተኛ ግምትና አድናቆት ሲገልጥ አለባበሳችንም እንደሚያስደስተው ያመለክታል፡፡CLAmh 71.7

    ከሁሉ ያጌጠውን ልብስ እንድንጎናጸፈው የሚፈልግ በመንፈሳዊ ኑሯችን ላይ ነው፡፡ “በእርሱ ዘንድ ታላቅ ግምት የሚሰጠውን” “ትሁትንና ገርን መንፈስ” የሚስተካከል ውጫዊ ጌጥና ልብስ ከየትም አይገኝ፡፡ (1ኛ ጴጥሮስ 3፡4)CLAmh 71.8

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents