Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ልምድ ጤናን እንዴት እንደሚበድል

    ሴቶችን ብዙ ዓይነት በሽታ እንደሚያጠቃቸው ሲታወቅ በተለይ የአለባበስ ጉድለት በበለጠ ለበሽታ ያጋልጣቸዋል፡፡CLAmh 72.7

    የሚመጣባቸውን ተዘጋጅተው በመቋቋም ፋንታ በተሳሳተ የኑሮ አቋም ጤናቸውን ብቻ ሳይሆን ሕይወታቸውንም ያጣሉ፡፡ ልጆቻቸውንም የተሳሳተ የሕይወት አመራር፤ የተበላሸ የኑሮ ፈለግ አስይዘዋቸው ሮሮና ወዮታ ብቻ አውርሰዋቸው ያልፋሉ፡፡CLAmh 73.1

    አንዱ በልማድ የመጣ አጉል ነገር አካልን አስተካክሎ አለማልበስ ነው፡፡ አንዳንድ የአካል ክፍሎች ከሚገባው በላይ ልብስ ሲደራረብላቸው የቀሩት የአካል ክፍሎች ይራቆታሉ፡፡ እግርና እጅ ከዋናው የአካል ክፍል የራቁ ስለሆኑ በሙቀት መጠበቅ አለባቸው፡፡ እነዚህ የአካል ክፍሎች በሚገባ ካልተጠበቁና በብርድ ከተጠቁ ጤና ይገኛል ማለት ዘበት ነው፡፡ ስለዚህ በእነዚህ የአካል ክፍሎች ውስጥ አነስተኛ ደም ካለ በሌላው የአካል ክፍል ውስጥ ከመጠን ያለፈ ደም አለ ማለት ነው፡፡ የተሟላ ጤና እንዲኖር ከተፈለገ የተስተካከለ የደም መዘዋወር መካሄድ አለበት፡፡ ግን እግርና እጅ ተራቁቶ በሌላው የአካል ክፍል የተደራረበ አለባበስ ካለ የተስተካከለ የደም ዝውውር ይኖራል ማለት አይቻለም፡፡ ብዙ ሴቶች ንጹሕ ደም እንዲኖር የሚያስችል ንጹሕ አየር ስለማያገኙ ደማቸው በደም ሥራቸው እንደልብ ተዘዋውሮ ጤንነትንና ኃልን እንዳይሰጣቸው አካላቸው የተዝናና እንቅስቃሴ ስለማያገኝ ብስጩና ቁጡ ይሆናሉ፡፡ ብዙ ሴቶች ሙሉ ጤና ሊኖራቸው ሲችሉ ድውያን ሆነው ቀርተዋል፡፡ ብዙዎችም ለአካላቸው ተስማሚ ልብስ ለብሰውና በነጻ የሚታደለውን የአየር በረከት በሚገባ ተጠቅመውበት ቢሆን እድሜ ጠግበው በደስታ ሊኖሩ ሲችሉ የሳንባ ነቀርሳን በመሳሰሉ በአደገኛ በሽታዎች ተቀጭተዋል፡፡CLAmh 73.2

    ተስማሚ ልብስ ለመምረጥ እያንዳንዱ የአካል ክፍል የሚያስፈልገው ጥንቃቄ በሚገባ መጠናት አለበት፡፡ የአየሩ ጠባይ፣ አካባቢው፣ የጤናው ሁኔታ፣ ዕድሜ፣ የሥራ ዓይነት ልብስን ለመምረጥ ሊታሰብባቸው ይገባል፡፡ ማንኛውም ልብስ የደምን መዘዋወር ወይም እንደልብ መተንፈስን እንዳያውክ ሆኖ መግጠም አለበት፡፡ ልብሳችን የክንዶቻችን መታጠፍና መዘርጋት እንዳያሰናክል ሆኖ “ቧ” ማለት አለበት፡፡CLAmh 73.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents