Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የትንባሆ ዝግተኛ መርዝ

    ትንባሆ ዝግተኛና የማይታወቅበት በጣም አደገኛ መርዝ ነው፡፡ በማንኛውም መልክ ቢወሰድ ለአካል ጠንቅ መሆኑ አይቀርም፡፡CLAmh 76.1

    ጉዳቱ ቀስ በቀስ በመሆኑና በመጀመሪያ ስለማይታወቅ አደገኛነቱ የላቀ ነው፡፡ መጀመሪያ ነርቮችን ይረብሽና በኋላ ያበድናቸዋል፡፡ አእምሮን ያደንዛል፣ ከአስካሪ መጠጥ ይልቅ ነርቮችን ይጎዳል፡፡ ጉዳት ሲጀምር ሳያስታውቅ ስለሆነ ጠንቁን ከአካል ለማስወገድ አዳጋች ነው፡፤ ከተዘወተረ የጠንካራ መጠጥን ሱስ ይተክላል፡፡ ስለዚህ የጠጭነት መሠረቱና መነሻው ትንባሆ ማጨስ ነው፡፡CLAmh 76.2

    ትንባሆ ማጨስ የማይመች፣ ውድቅ፣ ቆሻሻ፣ ራስን አርክሶ ሌሎችን የሚያስቀይም ነው፡፡ የትንባሆ ተገዥ የሆኑ ሁሉ የትም ተቃውሞ ይገጥማቸዋል፡፤ በሕዝብ መካከል ስታልፉ አንድ ሰው የተመረዘ የትንባሆ ጭሱን ሲተነፍስበችሁ ምን ይሰማችኋል? በአልኮሆልና በትንባሆ ሽታ በተበከለ የሕዝብ መኪና ውስጥ ወይም ክፍል ውስጥ መቀመጥ አያስደስትም፤ ለጤናም አይስማማም፡፡ ሰዎች በትንባሆና በአልኮሆል ራሳቸውን ቢጎዱ አንሷቸው ሌላው ሕዝብ የሚስበውን አየር ለመበከል ምን መብት አላቸው?CLAmh 76.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents