Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የተሟላ ኑሮ - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ብዙ የገንዘብ ኪሣራ

    ፈቃድ የሚሰጠው የመንግስት ገቢ ያዳብራል በሚል አስተሳሰብ ነው፡፡ ግን የአልኮሆል መጠጥ ጠንቅ ላፈራቸው ወንጀለኞች፣ ወፈፌዎች፣ ሥራ ፈቶች የሚደረገው ወጭ ሲታሰብ ትርፉ የር ላይ ነው! በመጠጥ ኃይል የተሸነፈ ሰው አንድ ወንጀል ይፈጽማል፤ በወንጀሉ ተይዞ ፍርድ ቤት ሲቀርብ አደጋው እንዲፈጸም በሕግ የፈቀዱት ሰዎች ነገሩን በማውጣት በማውረድ ይደክማሉ፡፤ ወፈፌን ሰው ጨርሶ ሊያሳብድ የሚችል ነገር በሕግ ፈቀዱ፡፡ አሁን የተያዘውን ወንጀለኛ ግዞት ሲጨምሩት ሚስቱና ልጆቹ የአገር ሸክም ሆኑ ማለት ነው፡፤CLAmh 85.4

    በገንዘብ በኩል ብቻ የሚደርሰው ኪሣራ እንኳ ሲገመት የዚህን ዓይነት ንግድ መፍቀድ እንዴት ከባድ ስህተት ነው! ገንዘብስ ቢተርፍ ቢሞላ የሰብዓዊ ፍጡር የማሰብና የማመዛዘን ችሎታ፤ በአርኣያ ሥላሴ የተፈጠረው ሰው አካል፤ የሚያድጉት ልጆች ጉዳይ፤ የሰው ክብርና ደረጃ፤ ልጆች ከወላጆቻቸው ሊወርሱት የሚገባ ንጹሕ የጠባይ ቅርስ በገንዘብ ይለወጣል?CLAmh 85.5

    በአስካሪ መጠጥ ሱስ የተለከፈ ሰው ሁኔታ በጣም አሳዛኝ ነው፡፡ አእምሮው ተመርዟል፤ ሃሳቡ ተደክሟል፡፡ የምግብና የመጠጥ ፍላጎቱን የሚቈጣጠርበት በቂ ኃይል የለውም፡፡ የሥጋ ፈቃዱን እንዲገታ ቢመክሩትና ቢዘክሩት አይሰማም፡፡CLAmh 86.1

    በክፋት አዘቅት ስለተዋጠ መጠጥ ለመተው ቢወስንም ዘሎ የብርሌ አንገት ያንቃል፡፡ አንድ መለኪያ እንደቀመሰ የመወሰን ኃይሉ ድራሹ ይጠፋል፤ መጥፎው መልካም፣ ጨለማው ብርሃን መስሎ ይታየዋል፡፡ የዕብደት መርዝ ሲቀምስ የሚከተለው ጉዳት ትዝ አይለውም፡፡ ያዘነችው ሚስቱ አትታወሰውም፡፡ ኃላፊነቱን የዘነጋው አባት ለታረዙትና ለተራቡት ልጆቹ ግድ የለውም፡፡ ፈቃድ በመስጠቱ ሕግ የሰውን ጥፋት ደገፈ ማለት ነው፡፡ ዓለም በጥፋት ስትጥለቀለቅ እጁን አጣምሮ በመቀመጥ አጥፊዋ የሆነውን ንግድ አያግድም፡፡CLAmh 86.2

    የአልኮሆል ይዞታ ማንንም ያሠጋል፡፡ ሰው ሁሉ ለደኅንነቱ ሲል ይህን አደገኛ ጠላት ማጥፋት አለበት፡፡ ከሁሉም በላይ የፍርድ አደባባዮና ችሎቶች መሻትን መግዛት የሰፈነባቸው ሊሆኑ ይገባል፡፡CLAmh 86.3

    አገረ ገዥዎች፤ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባሎች፤ የሕግ መምሪያ ምክር ቤት አባሎች፤ ዳኞች፣ የሕግ ባላደራዎች ስለሆኑና የሕዝብ ዝና፣ ሐብት፣ ሕይወት በእጃቸው ስለሆነ መሻትን መግዛት የሚያውቁ ይሁኑ፡፡ እውነትንና ሐሰትን ለይተው ማወቅ የሚችሉ እንደዚህ ያደረጉ እንደሆን ብቻ ነው፡፡ በዚህ መምሪያ የሠሩ እንደሆን በሕግ የጸኑ በብልሃት የሚያስተዳድሩና ምሕረት የሚያሳዩ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡CLAmh 86.4

    ግን እነዚህ ከባድ ኃላፊነት ያለባቸው ሰዎች ይዞታቸው እንዴት ነው? በከባድ መጠጥ ምክንያት ከእነዚህ ሰዎች መካከል አእምሮአቸው የደነዘ፤ እውነትንና ሐሰትን ለይቶ ማወቅ ያቃታቸው ስንት ናቸው!CLAmh 86.5

    ለእግዚአብሔር ክብር፣ ለአገር ደኅንነት፣ ለኅብረተሰብ ብልጽግና፣ ለቤተሰብና ለግለሰብ ጤንነት ሲባል መሻትን ባለመግዛት የሚመጣውን መዘዝ ለሕዝብ ማስተዋወቅ ተገቢ ነው፡፡ አሁን ብንገነዘበውም ጎጂነቱን ቆይተን እናየዋለን፡፡CLAmh 86.6

    የጥፋትን ሥራ ለማገድ ቆርጦ የሚሰለፍ ማነው? ሥራው ገና አልተጀመረም፡፡ ሰዎችን የሚያሳብደው የአልኮሆል መጠጥ እንዳይሸጥ የሚከላከል አንድ ሠራዊት ይቋቋም፡፡ አደገኛነቱ በሚገባ ይገለጥና ሕዝቡ ለመከላከል የሚያስችል በቂ ዕውቀት እንዲኖረው ይደረግ፡፡ በመጠጥ ምክንያት ያበዱት ሰዎች ከዚህ አሰቃቂ ወጥመድ የሚያመልጡበት ዘዴ ይፈለግላቸው፡፤CLAmh 87.1

    ሕዝቡ ሕግ አውጭውን ክፍል ይህን ሕገ ወጥ ንግድ የሚያስቀር ደንብ እንዲደነገግ ይወትውት፡፡CLAmh 87.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents